የ አማርኛ ተረት እና ምሳሌ ዝርዝር List of Amharic Proverbs

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
selam sew
Leader
Leader
Posts: 678
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

Re: የ አማርኛ ተረት እና ምሳሌ ዝርዝር List of Amharic Proverbs

Unread post by selam sew »

ተረት ጨ

• ጨረቃ ሲጠፋ ኮከብ አባወራ ይሆናል
• ጨዋነሽ ቢሏት ሳቁ ገደላት
• ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ አለበለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይወረውሩሀል
• ጨጓራ ለመፍጨት አንጀት ለመጎተት በለው ዋተት ዋተት
• ጫማ የለኝም ብለህ አትዘን ካልሲ የሌለው አለና
• ጫማ የለኝም ብለህ አትዘን እግር የሌለው አለና
• ጭድ ይዞ እሳት ሳል ይዞ ስርቆት
• ጭድ ይዞ ወዘት ሳል ይዞ ስርቆት
• ጭለማ ቢመጣ አትፍራ ይነጋልና

ተረት ፈ

• ፈላ ገነፈለ ተሞላ ጎደለ
• ፈረሰኛ ሲሮጥ እግረኛን ምን አቆመው
• ፈረሰኛ ሲሸሽ እግረኛን ምን አመጣው
• ፈረሰኛ የወሰደውን እግረኛ አይመልሰውም
• ፈረሱም ይኸው ሜዳውም ይኸው
• ፈረስ ሲያጠብቅ ልጓም አይለቀቅ
• ፈረስ በራሪ በቅሎ ሰጋሪ
• ፈረስ ቢያነክስ አህያ ታጉዝ
• ፈረስ ቢጠፋው ኮርቻውን ገልቦ አየ
• ፈረስ አውቃለሁ ስገታ እወድቃለሁ
• ፈረስና ገብስ ያጣላል
• ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም
• ፈረስ ጥሎ ይደነግጣል በቅሎ ጥሎ ይረግጣል
• ፈረስ ጥሎ ይደነግጣል አህያ ጥሎ ይረግጣል
• ፈረንጆች እንደመርፌ ይገቡ እንደዋርካ ይሰፉ
• ፈሩ ፈሩ ማጀት አሩ
• ፈሩ ፈሩ ማጀት አደሩ
• ፈሪ ለናቱ
• ፈሪ ለናቱ ይገባል
• ፈሪ ለናቱ ጀግና ለጀግንነቱ
• ፈሪ በገዛ ጠቡ ገላጋይ ይሆናል
• ፈሪ ቢሸፍት እስከ ጓሮ
• ፈሪ እንዳይሉኝ አንድ ገደልሁ ጀግናም እንዳይሉኝ አልደገምሁ
• ፈሪ ከውሀ ውስጥ ያልበዋል
• ፈሪ ካልጋ ላይ ይወድቃል
• ፈሪ ካልጋ ላይ ወድቆ ይሞታል
• ፈሪን ውሀ ውስጥ ያልበዋል
• ፈሪ ውሀ ውስጥ ሆኖ ያልበዋል
• ፈሪ ውሀ ውስጥ ያልበዋል
• ፈሪ የሚያባርረው ሳይኖር ይሸሻል
• ፈሪ የናቱ ልጅ ነው
• ፈሪ ፈራና እጉድባ ቢኛ ጆሮውን በላው ያይጥ ቀበኛ
• ፈሪ ፈራና እጉድባ ቢተኛ ጆሮውን በላው ያይጥ ቀበኛ
• ፈርተው ድንጋይ ሲጥሉ ጅብ ወጣ ከዱሩ
• ፈርተው ድንጋይ ቢጥሉ ጅብ ወጣ ከዱሩ
• ፈርተው ድንጋይ ቢወረውሩ ጅብ ወጣ ከዱሩ
• ፈሷን ፈስታ ቂጧን ጨበጠች
• ፈስ በወረንጦ እየተለቀመ ነው
• ፈስቶ ቂጥን መያዝ
• ፈስ ያለበት ቂጥ ዝላይ አይችልም
• ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም
• ፈትል ሲረዳዳ አንበሳ ያስራል
• ፈትል ሲረዳዳ አንበሳ ያስቀራል
• ፈክሮ መሽሽ ታሪክ ያበላሻል
• ፈዛዛ እያንቀላፋ ይገባል ፈፋ
• ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ እስቲበርድ ይራበኝ
• ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ እስኪበርድ ይራበኝ
• ፈገግታ የልብ አለኝታ
• ፈጣሪን የሚያህል ጌታ ርስትን ያህል ቦታ
• ፈጣሪን የሚያህል ጌታ ገነትን ያህል ቦታ
• ፈጥነው የገመዱት ፈጥኖ ይበጠሳል
• ፈጥኖ መስጠት ኋላ ለመጸጸት
• ፈጥኖ መስጠት ቶሎ ለመጸጸት
• ፈጥኖ መስጠት በኋላ መጸጸት
• ፈጭታ የነበረች ላመልማሎ ኮራች
• ፊት ያሞጠሙጧል ኋላ ያፏጩዋል
• ፍሪክና ጻድቅ አይቀጣጠርም
• ፍሬ በመስጠቱ ባልታወቀ ሾላ የወፎች ዝማሬ ቀደመ አሉ
• ፍቅር ሲጠና ቆሎ ያጓርሳል
• ፍቅርና ጉርሻ ካላስጨነቀ አያምርም
• ፍቅር ካለ ዘጠኝ ቂጣ ለባልና ሚስት ይበቃል
• ፍቅር ፍቅር ሲሉ ደሀ ሆነው ቀሩ
• ፍየል ሁለት ወልዳ አንዱ ለመጽሀፍ አንዱ ለወናፍ
• ፍየል ላምስት ዶሮ ለባልና ለሚስት
• ፍየል መንታ ወልዳ አንዱ ለመጽሀፍ አንዱ ለወናፍ
• ፍየል መንታ ትወልድና አንዱ ለወናፍ አንዱ ለመጽሀፍ
• ፍየል ሲሰባ ሾተል ይልሳል
• ፍየል በልታ በበግ አበሰች
• ፍየል በልታ በበግ አሳበበች
• ፍየል ሲቀናጣ እናቱን ይሰራል
• ፍዬል በግርግር እናቱን ይሰራል
• ፍዬል በግርግር እናቱን ይሰር
• ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ
• ፍየል ከቀዘነ ዲያቆን ከዘፈነ
• ፍየል የለኝ ከነብር ምን አጣላኝ
• ፍየልና ቀበሮ ምጥማጥና ዶሮ
• ፍየሏን እንደበግ
• ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ
• ፍዳ ለሀጥአን እሴት ለጻድቃን
• ፍጥም አያናግር የጎርፍ ሙላት አያሻግር
• ፍጥም አፍራሽ ቤተክርስቲያን ተኳሽ
• ፍጥም ያቆማል እርቅ ይጠቀልላል
• ፍጥም ያዋውላል አቧራ ያስላል
• ፎክሮ መሸሽ ታሪክ ያበላሽ
selam sew
Leader
Leader
Posts: 678
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

Re: የ አማርኛ ተረት እና ምሳሌ ዝርዝር List of Amharic Proverbs

Unread post by selam sew »

ተረት ቸ

• ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ
• ቸርን ቢያጠቁት ቢስ ይሆናል
• ቸር ይመጸውታል ጠላት ያጠፋል
• ቸኩለው ያፈሱታል ተቀምጠው ይለቅሙታል
• ቸኩሎ ከተጠቀመ ዝግ ብሎ የተጎዳ ይሻላል
• ቻቻታ የለመደ ሰው አባይ ዳር ቅበሩኝ ይላል
• ችኩል ሰው ጠንቋይ ይጠይቃል
• ችኩል ቅቤ ያንቀዋል
• ችኩል አደንጓሬ ሳይበሉት ሆድ ያማል
• ችኩል አፍ ሞትን ይጠራል
• ችኩል እግር ከዘንዶ ጉድጓድ ይገባል
• ችኮ የጦም ስጋ
• ችግረኛ ሲናገር ውሸት ሲደነፋ እውነት
• ችግር ለወዳጅ ሲያዋዩት ይቀላል
• ችግር በቅቤ ያስበላል አለች ዉሻ
• ችግር ነው ጌትነት
• ችግር የገረፈው ውጤቱ ያማረ ካልተንቀባረረ

ተረት ገ

• ገላጋይ አጥቼ ግልገሌን በላኋት
• ገለፈንት የሴት ጋለሞታ
• ጉድ ነሽ ያንኮበር ቅጠል በየሄድሽበት ነገር ማንጠልጠል
• ጋን በጠጠር ይደገፋል
• ግም ለግም አብረህ አዝግም

ተረት ጠ

• ጠላትህን ውሀ ሲወስደው እንትፍ ብለህ ጨምርበት
• ጠርጥር በገንፎ ውስጥ እንዳለ ስንጥር
• ጠበንጃ ራሱ መቶ ራሱ ይጮሀል
• ጠንቋይ ለራሱ አያቅም
• ጡጥም ከፈስ ተቆጠረች
• ጤፍ ከአቅሙ እንክርዳድ ከፈለ
• ጤፍ ከዘመዷ ጎታ ትሞላ
• ጥልቅ ብዬን ውሀ ወሰዳት
• ጥርሴስ ልማዱ ነው አይኔን አታስቀው
• ጥርስና ከንፈር ሲደጋገፍ ያምር
• ጥርስ የሌላት ጥርስ ያላትን ነክሳ አነካከስ ታስተምራለች
• ጥቂት ያለው ሁሉ ብርቁ ነው
• ጥንቸል ጥላው ጠላት ይመስለዋ
• ጥንቸልም ለሆዷ ዝሆንም ለሆዱ አብረው ውሀ ወረዱ
• ጥይትና ማጣትን ተኝቶ ማሳለፍ ነው
• ጥጃ ቢፈነጭ በሜዳ ውሀ ቢሄድ በጎድጓዳ
• ጥጃ ቢፈነጭ በሜዳ ውሀ ቢሮጥ በጎድጓዳ
• ጥጋበኛ ከርከሮ የነፍጠኛ ጎጆ ይታከካል
• ጥጋበኛንና ውሀ ሙላትን ቁመህ አሳልፈው
• ጦር ሲመጣ ዛቢያ ቆረጣ
• ጦጣ መጀመሪያ የመቀመጫዬን አለች አሉ
• ጦጣ ባለቤቱን ታስወጣ

ተረት ጰ

• ጳጉሜ ሲወልስ ጎተራህን አብስ
• ጳጉሜ ሲወልስ ገበሬ ጎተራህን አብስ
• ጳጉሜ ቢለግስ ጎታህን አብስ

ተረት ጸ

• ጸሀይ ሳለ ሩጥ አባት ሳለ አጊጥ
• ጸሀይ ብልጭ ወፍ ጭጭ ሲል
• ጸሀይ ካልወጣ ከሰፈረበት አይነሳ አንበጣ ሴት ምክንያት አታጣ
• ጸሀይ የጠዋት አዱኛ የሽበት
• ጸሀይ ያየውን ሰው ሳያየው አይቀርም
• ጸሀይና ንጉስ ሳለ ሁሉም አለ
• ጸሎት በጽሞና ነገር በደመና
• ጸሎት በፍቅር ሀይማኖት በምግባር
• ጸሎት ከፍቅር ሀይማኖት ከምግባር ይበጃል
• ጸሎት ከፍቅር ሀይማኖት ከግብር
• ጸሎት ያለፍቅር ሀይማኖት ያለግብር አይረባም
• ጸጸት እያደር ይመሰረት
• ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ
• ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ ሀጥአን ግን በተቃጠሩበት ይተጣጣሉ
• ጽዋ በተርታ ስጋ በገበታ
• ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ
• ጽድቁ ቀርቶብኝ በውሉ በኮነነኝ
• ጽድቅ ለመንኳሽ ቀኝ ለከሳሽ
• ጽድቅ እንደ ላሊበላ እድሜ እንደ ማቱሳላ ይስጥህ
• ጽህፈት በብራና ዘፈን በበገና
• ጾማ ጾማ ለጸሎተ ሀሙስ እርጎ ትልስ
• ጾም ገዳፊና ሰው ጠባቂ ለጥቂት ይሳሳታል
Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”