ለምን ይሆን?

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
selam sew
Leader
Leader
Posts: 692
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ለምን ይሆን?

Unread post by selam sew »

📘ለምን ይሆን?

አንተ በውድ ሆስፒታል ተወልደህ ይሆናል፣ እኔ በቤት ውስጥ ተወልጄአለሁ፤ ሁለታችንም በህይወት እየኖርን ነው።

አንተ በግል ትምህርት ቤት ተምረህ ይሆናል፣ እኔ በመንግስት ትምህርት ቤት ተምሬአለሁ፤ ሁለታችንም በአንድ ዩንቨርስቲ ጨርሰናል።

አንተ ከምቹ አልጋ ላይ ከእንቅልፍህ ነቅተህ ይሆናል፣ እኔ ከመሬት ላይ፤ ሁለታችንም የሰላም ሌሊት አሳልፈናል።

አንተ የለበስካቸው ልብሶች ውብና ውድ ይሆናሉ፣ የኔ ቀላልና ርካሽ ናቸው፤ ሁለታችንም ራቁትነታችንን ሸፍነናል።

አንተ ብዙ የምግብ ዐይነቶችን ከጥሩ መስተንግዶ ጋር አማርጠህ በልተህ ይሆናል፣ እኔ ቤት ያፈራውን ወስጄ በልቻለሁ፤ ሁለታችንም ግን የምግብ ፍላጎታችንን ለማርካት ስንል ተመግበናል።

አንተ Land Cruser TurboV8፣ Range Rover፣ Lexus Jeep፣ Hummer Jeep ወይንም G Wagon...መኪና ትነዳ ይሆናል፣ እኔ የህዝብ ትራንስፓርት እጠቀማለሁ፤ ሁለታችንም ግን ወደፈለግንበት መዳረሻ ደርሰናል።

ምናልባት ይሄንን ልጥፍ (post) እያነበብክ ያለኸው፤ በSamsung Galaxy 8Edge፣ በiPhone7s+፣ በSony Xperia፣ በGoldvish Le Million ወይንም በVertu Signature Cobra...ስልክህ ታግዘህ ይሆናል፣ እኔ ይህንን የምፅፈው ስክሪኑ በተሰበረ ስልኬ ቢሆን እንኳ ሁለታችንም መልእክቱ እኩል ይታየናል።

ይሀውልህ፤ ህይወት የፉክክር መድረክ አይደለም። ነገሮችን ለማሳካት ብዙ መንገዶች ቢኖሩ እንኳ ሁሉም የህይወት መስመሮች የሚመሩን ወደ አንድ አቅጣጫ ነው። ይኸውም- ሞት። ደግሞ ደስታ ሁሉንም ነገር በማግኘት ውስጥ አይመጣም፣ ካለህ ነገር ውስጥ መልካሙን በማውጣት እንጂ። ትልቁ ቁምነገር ያለው ራስህን የምታይበት መነጽር ነው። ደስታ ማለት የምትወደውን ማግኘትም አይደለም፣ ደስታ ማለት ያገኘኸውን በቂ ነገር መውደድ ነው። ልብ በል፤ ያንተ በዚህ አለም መኖር የሚያስደስተው ሌላውን ሲሆን አንተን የሚያስደስትህም የሌላው መኖር ነው።

የትላንት ትላንት ምንም አልነበረህም፤ ምንም ሳትይዝ፣ ራቁትህን ነው ይችን ዓለም የተቀላቀልከው፤ ይሁንና ትላንት ያጣኸውን ዛሬ አግኝተሃል፣ ዛሬ ያጣኸውን ነገ ታገኘዋለህ፣ ሁሉንም ደግሞ የነገ ነገ ታጣዋለህ። ባጭሩ አንድ ቀን ሁሉንም ትተህ ትሞታለህ።

ከሞትክ በኋላስ?

ከ3 ቀን በኋላ የጣቶችህ ጥፍሮች መወዳደቅ ይጀምራሉ። ከ4 ቀን በኋላ የራስ ቅልህና ሰውነትህ ላይ ያሉ ጸጉሮች በሙሉ ይረግፋሉ። ከ5 ቀን በኋላ አንጎልህ መርገብ ይጀምራል፣ የሰውነትህ ሥጋ ይጠወልጋል፤ መቀመጫህ፣ ጡትና ኃፍረተ-ስጋህ ይበሰብሳል። ከ6 ቀን በኋላ ቆዳህ መሳሳትና ቀስ በቀስም ከአጥንትህ ላይ መለያየት ይጀምራል። ከ7 ቀን በኋላ ሆድህ ይቀልጣል፣ መጥፎ ጠረንም ማውጣት (radiate ማድረግ) ይጀምራል። ከሞትክ ከ60 ቀን በኋላ መላው የሰውነትህ አካል ወዳልነበር ይለወጥና "አንተ" ማለት "አጥንት" ብቻ ትሆናለህ።

ታዲያ፤
• ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ትእቢት?

• ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ራስ ወዳድነት?

• ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ክርክር፣ ጭቅጭቅና ንትርክ?

• ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ቅናት?

• ለምንስ ይሆን ይሄ ሁሉ ጥላቻ?

• እኮ ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ የክፋት ሥራ?

ጥለህ ለምትሄደው አለም?!። እስኪ ለሞት ሩብ ጉዳይ እንደቀረው ሰው እንኑር። ደሃ ሃብታም እያልክ ሳታደላ፣ የተማረ ያልተማረ ብለህ ሳትለይ፣ መልከ መልካም መልከ ጥፉ ሳትል፣ ባለስልጣን ተራ ሰው ብለህ ሳትመርጥ...ሁሉንም በሰው'ነቱ እኩል- ተመልከት፣ ስማ፣ እርዳ፣ አድንቅ፣ አመስግንም። ምክንያቱም የሁላችንም ፍጻሜ አንድ ሥፍራ- መቃብር ነውና!። በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ። ራስህንም በዚህ ምድር ብቻ አትለካው፣ ከዚህ አለም ወዲያ ያለውን ህይወት አስብ። ሁለቴ የተወለደ አንድን ሞት፣ አንዴ የተወለደ ግን ሁለት ሞት ይሞታልና ቀን ሳለ ወደ ፈጣሪህ ተጠጋ። ሁልጊዜም በርሱ ደስ ይበልህ!!

ምንጭ: ፌስቡክ
Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”