የሚያሸንፍ ፍቅር – ሙሃዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
selam sew
Leader
Leader
Posts: 692
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

የሚያሸንፍ ፍቅር – ሙሃዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

Unread post by selam sew »

የሚያሸንፍ ፍቅር – ሙሃዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት


አንድ ሰርግ ውስጥ አንድ ሽማግሌ ሙሽሮቹን ሊመርቁ ቆሙና «አጣልቶ የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር ይስጣችሁ» ብለው ሲመርቁ ሰማሁ፡፡ እስካሁን ብዙ ሠርግ ተገኝቼ ምርቃት ሰምቻለሁ እንዲህ ያለ ምርቃት ሰምቼ አላውቅም፡፡ ምን ማለታቸው ይሆን? እያልኩ በኅሊናዬ ሳብሰለስለው ቆየሁ፡፡

«አጣልቶ የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር? ደጋግሜ አሰብኩት፡፡ ይህንን ሳወጣ እና ሳወርድ እንዳጋጣሚ ሽማግሌው ምርቃታቸውን ፈጽመው እኔ የነበርኩበት ጠረጲዛ ጋ መጡና ተቀመጡ፡፡

መጠየቅ አለብኝ አልኩና አንገቴን በጠረጲዛው ላይ ሰገግ አድርጌ

«ደኅና ዋሉ አባቴ» አልኳቸው፡፡
«ይመስገነው ደኅና ነኝ» አሉኝ፡፡
«ቅድም የመረቁት ምርቃት ሰምቼው ስለማላውቅ ገረመኝ» አልኩ ወሬ ለመወጠን ብዬ፡፡

«አንተ ብቻ አይደለህም ብዙዎች ይገርማቸዋል» አሉ ፈገግ ብለው፡፡
«ምን ማለትዎ ነው ግን»
«መጀመርያ አንድ ታሪክ ልንገርህ» አሉኝ ጃኖአቸውን ወደ ቀኝ መለስ እያደረጉ፡፡ እኔም ወንበር ቀየርኩና አጠገባቸው ተደላድዬ ተቀመጥኩ፡፡

«አንድ ጊዜ አንዲት እኅት ምክር ልትጠይቀኝ መጣች፡፡ እናም እንዲህ ስትል አጫወተችኝ፡፡ እኔ እና ባለቤቴ ከተጋባን ስምንት ዓመታችን ነው ሁለት ልጆችንም ወልደናል፡፡ የራሳችን ቤት እና መኪና አለን፡፡ ሁለታችንም የየራሳችን በቂ ደመወዝ የሚገኝበት ሥራ አለን፡፡

ይህንን ያህል ዓመት በትዳር ስንኖር ተጋጭተን ወይንም ተጣልተን አናውቅም፡፡ እንኳን ለመጣላት ለመፋቀረም ጊዜ አልነበረንም፡፡ ጭቅጨቅ፣ ንዝንዝ፣ በዚህ ወጣ፣ በዚህ ወረደ የሚባል ነገር በቤታችን ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም፡፡ ጎረቤቶቻችን እና የሚያውቁን ሁሉ በኛ ይቀናሉ፡፡

ምን የመሰለች ሚስት አለችህ ይሉታል፤ እኔንም ምን የመሰለ ባል አለሽ ይሉኛል፡፡ አንድ ጊዜ ጓደኛዬን ለማየት እና በዚያውም ለመዝናናት ብዬ ናይሮቢ ሄድኩ፡፡ ባለቤቴ ሥራ ስለነበረው አልሄደም፡፡ ጓደኛዬ ትዳር ከያዘች አምስት ዓመቷ ነው፡፡

ባለቤቷ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ስለሚሠራ ነው ኬንያ የሄዱት፡፡ እነርሱ ቤት አንድ ሳምንት ተቀመጥኩ፡፡ ያን ጊዜ ታድያ የኔን ትዳር ትዳር መሆኑን ተጠራጠርኩት፡፡ ጓደኛዬ ባለቤቷን በስሙ አትጠራውም፤ እርሱም እንዲሁ፡፡ ደክሞት ከመጣ እግሩን ታጥባላች፣ እርሱም እንዲሁ፡፡

ምግብ ሲበሉ እንደተጎራረሱ ነው የሚጨርሱት፡፡ ልጆቹን፣ቤቱን ሌላውንም አብረው ነው የሚያደርጉት፡፡ አንዳንድ ጊዜ በኃይል ይከራከራሉ፤ ሊደባደቡ ነው ብዬ ስፈራ ለጥቂት ጊዜ ይኳረፉና ግን መልሰው ይፋቀራሉ፡፡ አንድ ቀን ታድያ ጓደኛዬን «ለመሆኑ ተጣልታችሁ ታውቃላችሁ?» ስል ጠየቅኳት፡፡

«በጣም እንጂ እኛ መጣላትንም መፋቀርንም እናውቅበታለን፡፡ ተጣልተን ተጣልተን ወጥቶልናል፡፡ ከጠብ በኋላ የሚኖረን ፍቅር ሁልጊዜ ምነው በተጣላን ያሰኘኛል» አለችኝ፡፡ ከዚያም ወደራሴ ተመልሼ አሰብኩ፡፡ እኔ እና ባለቤቴ ተጣልተን አናውቅም፡፡

አያድርሰውና አንድ ቀን ብንጣላ እንዴት እንደ ምንታረቅ የምናውቅበት አይመስለኝም፡፡ ክፉን አርቅ አልኩ ለራሴ፡፡ ግን እኛ ተጠባብቀን ነው ወይስ ተፈቃቅረን ነው የምንኖረው ብዬም ራሴን ጠይቄዋለሁ፡፡ ሳስበው ግን በመጠባበቀ እንጂ በመነፋፈቅ የምንኖር አይመስለኝም፡፡ እናም ትዳሬን ጠላሁት» አለችኝ፡፡ ችግሯ ገብቶኛል፡፡ አንድ ጥያቄ ጠየቅኳት፡፡

«ላንቺ ፍቅር ማለት የጠብ አለመኖር ነው? ወይስ ጠብን ማሸነፍ? አልኳት፡፡ ቀና ብላ አየችኝ፡፡ አልመለሰችልኝም፡፡ ዝም ብላ አሰበች፡፡
«ለመሆኑ ለምን እንደማትጣሉ ታውቂያለሽ?» አልኳት፡፡

«ለምን ይመስልዎታል?» ብላ እኔኑ መልሳ ጠየቀችኝ፡፡
«የማትጣሉት ስለማትገናኙ ይመስለኛል፡፡ የት ተገናኝታችሁ፣ የት ተነጋግራችሁ፣ የት ተከራክራችሁ፣ የት ተቀራርባችሁ ትጣላላችሁ፡፡ መጋጨትኮ ከመቀራረብ የሚመጣ ነው፡፡ እናንተ ጠብን አይደለም ያሸነፋችሁት፤ ጠብን ነው የሸሻችሁት፡፡ አለመሞት እና ሞትን ማሸነፍ ይለያያል፡፡

አለመጣላትና ጠብን ማሸነፍም እንዲሁ፡፡ «ሐኪሞች ለምን ክትባት እንደሚወጉን ታውቂያለሽ አይደል፡፡ ክትባቱ የሚሠራው ከሞተ ቫይረስ ነው፡፡ ለምን? ያ የተዳከመ ቫይረስ ወደ ሰውነታችን ሲገባ ሰውነታችን ጦርነት ተከፈተብኝ ብሎ ራሱን ያዘጋጃል፡፡ መድኃኒት ያመረታል፡፡

ራሱን በሽታ ለመከላከል ዝግጁ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ ልምድ አዳበረ፤ በሽታውን እንዴት እንደ ሚያሸንፍ ኃይል እና ዐቅም ገንዘብ አደረገ ማለት ነው፡፡ ትዳርም ይኼ ክትባት ያስፈልገዋል፡፡ ወደፊት ከባዱ የትዳር ቫይረስ መጥቶ በበሽታ እናንተን ጠራርጎ ከመውሰዱ በፊት ደካማውን ቫይረስ መከተብ ያስፈልጋችኋል፡፡

ኃይል እና ዐቅም መፍጠር ያስፈልጋችኋል፡፡ ያልተከተበ ልጅ እና የተከተበ ልጅ ልዩነታቸው የሚታወቀው በሰላሙ ጊዜ አይደለም፡፡ ወረርሽኙ ሲገባ ነው፡፡ ያን ጊዜ ማን መቋቋም እንደሚችል ይታያል፡፡ ሁለታችሁም በየፊናችሁ ትውላላችሁ፡፡ ከዚያ ወደቤት ትገባላችሁ፡፡ ራት ትበላላችሁ፡፡ ይቀጥላል፡፡

ቤትም ውስጥ ብትሆኑ አንቺ ጓዳ ነሽ፤ እርሱም ቴሌቭዥን እያየ ነው፡፡ ልቅሶ ስትሄዱ እርሱ ከወንዶች ጋር ነው አንቺ ከሴቶች ጋር ነሽ፡፡ ዓመት በዓል ሲመጣ እርሱ በግ ይገዛል፣ አንቺ ዶሮ ትገዣለሽ፡፡ እርሱ በቱታ ጎምለል ጎምለል ይላል፤ አንቺ በሐበሻ ቀሚስ ጉድጉድ ትያለሽ፡፡ ይቀርባል ትበላላችሁ፡፡ በቃ፡፡

ወዳጄ የማይፈስ ውኃ ከድንጋይ ጋር አይጋጭም፡፡ የረጋ ውኃ ይሻግታል እንጂ ግጭት የለበትም፡፡ ወንዝ ሆኖ ሲወርድ ግን አረኹ ገደሉ፣ ዐለቱ ቋጥኙ ይላተመዋል፡፡ ለመላተም አይሄድም፡፡ ሲሄድ ግን ይላተማል፡፡ ከመኖር ብዛት ታድያ ፈለግ ይሠራል፡፡ ከዚህ ብኋላ ኩልል ብሎ መፍሰስ ነው፡፡

እዚያ ደረጃ ለመድረስ ግን ስንት ትግል፣ ስንት ልትሚያ፣ ስንት ውጣ ውረድ አለ፡፡ ይኼ ሁሉ ወንዝ ማን ቦይ ቀድዶለት መሰለሽ የሚፈስሰው፡፡ በዘመናት እየታገለ በጠረገው መንገድ እኮ ነው እንዲህ አምሮ ሲፈስስ የምታይው፡፡ ትዳርም እንዲሁ ነው፡፡ እድገት ካለው፡፡ ሕይወት ካለው ይፈስሳል፡፡

ሲፈስስ ታድያ መላተም፣ መጋጨት ያጋጥማል፡፡ ይህ ግን እየተፈታ ይሄድና በኋላ የትዳር ፈለግ ይሠራል፡፡ ከዚያ በኋላ ኩልል እያለ መውረድ ነው፡፡ ፏፏቴ ይኖረዋል፡፡ ዳግላስ የሚወርድ ውኃ ይኖረዋል፡፡ ከዐለቱ ጋር ሲጋጭ ሕመም መሆኑ ቀርቶ ውበት ይሆነዋል፡፡ አንዳንዶቹኮ ከተጋቡ በኋላ ወንድም እና እኅት ብቻ ሆነዋል፡፡

አንዳንዶቹ አብሮ ሠሪ «ባለ አክሲዮን»፡፡ አንዳንዱ ባል ገንዘብ መስጠት አይቸግረውም፤ ሃሳብ መስጠት ግን አይሆንለትም፡፡ አንዳንዷ ሚስት ቤቷን ማስተዳደር አያቅታትም፤ ባሏን ማስተዳደር ግን አይሆንላትም፡፡ ብዙዎቹ «እኛኮ አንድ ነን» ብለው የሚፎክሩት ልዩነቶቻቸውን የሚያዩበት አጋጣሚ ስለሌላቸው ነው፡፡ መች ተወያይተው፣ መች ተከራክረው፣ መች ተገዳድረው ያውቃሉ፡፡

ሦስት ዓይነት ባል እና ሚስት አሉ፡፡ የሚገጥሙ፣ የሚገጥሙ የሚመስላቸው ግን የማይገጥሙ፤ ፈጽመው የማይገጥሙ፡፡ የሚገጥሙ ባል እና ሚስት እየተገዳደሩ፣ እየተጋጩ፣ እየተስማሙ፤ እየተቸገሩ፣ ችግር እየፈቱ፤ በሃሳብ እየተለያዩ፣ እየተቀራረቡ፤ እየተዋወቁ ሄደው በሂደት አንድ የሚሆኑ ናቸው፡፡

የሚገጥሙ የሚመስላቸው የማይገጥሙ የሚባሉት ደግሞ ሲታዩ የተስማሙ፣ የተፋቀሩ፣ አንድ የሆኑ፣ ጠብ እና ልዩነት የሌለባቸው የሚመስሉ፤ በውስጥ ግን የተከደኑ፣ በጊዜ የሚፈነዱ፣ ያልተዳሰሱ ቁስሎች ያሉባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ በአማርኛ «ይጠጌ አይነኬ» ይባላሉ፡፡

በሂሳብ asymptote የሚባሉት ናቸው፡፡ የሚገጥሙ የሚመስላቸው፤ ሰውም ሲያያቸው የሚገጥሙ የሚመስሉ፤ በእውነታው ግን መቼም የማይገጥሙ ናቸው፡፡ ሦስተኛዎቹ ጎን ለጎን የሚሄዱ ናቸው፡፡ parallelÝÝ ምናቸውም የማይገጥም፡፡ አለመግጠማቸውም የሚታወቅ፡፡ ያልተፋቱት ለልጆቻቸው፣ ለሕግ ጉዳዮች፣ ለቤተሰቦቻቸው ሲሉ እንጂ በጋብቻ ውስጥ በፍቺ የሞኖሩ ናቸው፡፡

አሁን ልጄ ራሳችሁን እዩ፡፡ መጣላት ለጋብቻ አስፈላጊ ነው እያልኩሽ አይደለም፡፡ በትዳር ውስጥ መጋጨት ብቻውን የመጠላላት ምልክት እንዳልሆነ ሁሉ፣ አለመጋጨት ብቻውንም ግን የፍቅር ምልክት አይደለም ነው የምልሽ፡፡ ለመሆኑ ለመጣላት ጊዜ አላችሁ? አንድ ወንበር ላይ መቀመጥና አብሮ መቀመጥ፤ አንድ አልጋ ላይ መተኛትና አብሮ መተኛት፤ አንድ ቤት ውስጥ መኖርና አብሮ መኖርኮ ይለያያሉ፡፡»

ከዚህ ውይይታችን በኋላ ወደ ባልዋ ሄዳ ለትዳር ጊዜ ስለመስጠት፤ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ስለመነጋገር፤ የቤት ሥራን ለሥራነቱ ብቻ ሳይሆን ለደስታ መፍጠርያነቱ አብሮ ስለ መሥራት ማንሣት ስትጀምር ነገር መጣ፡፡ ጭቅጭቅ ጀመርሽ ይላት ጀመር፡፡

የማይስማሙባቸው ነገሮች እየታወቁ መጡ፡፡ ይገርምሃል፡፡ በልቶ የማያውቅ ሰው ሲበላ እንደሚያመው ሁሉ፣ ተጋጭቶ የማያውቅ ሰው ሲጋጭ አያድርስብህ፡፡ አንድ ጋሪ ጠጠር በየቅንጣቱ ቢወረወር ከሚጎዳህ በላይ ጋሪውን እንደሞላ ቢደፋብህ የሚጎዳህ ይበልጣል፡፡

«ተጋጭተን አናውቅም» የሚሉ ሰዎችም ሲጋጩ እንደዚያው ነው፡፡ ለዚህ ነው «አጣልቶ የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር ይስጣችሁ» ብዬ መመረቅ የጀመርኩት፡፡

ጠብን የሚያሸንፍ ፍቅር፣ ጦርነትን የሚያሸንፍ ሰላም፣ ጨለማን የሚያሸንፍ ብርሃን ነው የሚያስፈልገን ብዬ፡፡
ጉልበት ስሜ ተነሣሁ፡፡
Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”