አፍሪካ አሜሪካዊው አርበኛ ኮ/ል ጆን ሮቢሰን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
User avatar
nebex
Leader
Leader
Posts: 283
Joined: 29 Oct 2009 10:32
Contact:

አፍሪካ አሜሪካዊው አርበኛ ኮ/ል ጆን ሮቢሰን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ

Unread post by nebex »

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ አፍሪካ አሜሪካዊው አርበኛ ኮ/ል ጆን ሮቢሰን

--በተረፈ ወርቁ -እንደ መንደርደሪያ

Image

THE LION AND THE CONDOR: The Untold Story of
Col. John C. Robinson and the Crippling of Ethiopia


በቅርቡ ዮሹዋ እስራኤል የተባለ አፍሪካ አሜሪካዊ ምሁርና የታሪክ ተመራማሪ በአምስቱ ዓመት የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ
ዓመታት ከአገሩ ከአሜሪካ መጥቶ የአየር ኃይልን በማቋቋምና ባልደረባ በመኾን ለአገራችን የነጻነት ጋድሎ ትልቅ
መሥዋዕትነት ስለከፈለ አፍሪካ አሜሪካዊው ኮ/ል ጆን ሮቢንሰን በእንግሊዝኛ ቋንቋ አንድ ድንቅ የኾነ መጽሐፍ
አበርክቶልናል፡፡ ይኸው ማጣቀሻዎቹንና መዘርዝሩን/ኢንዴክሱን ጨምሮ በ 294 ገጾች የተቀነበበውና ታሪኩን በሚያጎለብቱ
በርካታ ምስሎችና መረጃዎች የተካተቱበት መፅሐፍ ነው።

1- የኢትዮጵ ባለውለታ አርበኛው ኮ/ል ጆን ሮቢንሰን ማን ነው?!
ኮ/ል ጆን ሮቢንሰን አፍሪካዊ ዝርያ ያለው ጥቁር አሜሪካዊ ነው፡፡ ይኸው ሰው የልጅነት ብርቱ ምኞቱ የነበረውን አውሮፕላን የማብረር ትምህርት መማር እንዳይችል በቆዳው መጥቆር ምክንያት ዕገዳ ተጥሎበት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ሮቢንሰን በአቬዬሽን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የጽዳት ሠራተኛ አድርገው እንዲቀጥሩት ጠየቀ፡፡ በዚህ ሥራ ላይም
እያለ ለበረራ ትምህርት ብርቱ ናፍቆት የነበረው ወጣቱ ሮቢንሰን በክፍሉ ውስጥ ሌክቸር ሲሰጥ እየተደበቀ መከታተል፣ከትምህርት በኋላም በማስተማሪየ ሰሌዳው ላይ የቀረውን ኖት
እየገለበጠና ተማሪዎች የሚጥሉትን የማስተማሪያ ኖቶች በማሰባሰብ የበረራ ትምህርት በራሱ መማር ጀመረ፡፡
የበረራ ማስተማሪያ መጻሕፍትንና ማኑዋሎችን በማንበብ እውቀቱን ያጠናከረው ሮቢንሰን በአንድ አጋጣሚ ከጓደኛው ጋር ለበረራ ሥልጠና የምትሆን አወውሮፕላን ገጣጥሞ ያቀረበበት ኢግዚቢሽን ትልቅ የመነጋገሪ ርእስ እንዲኾን አደረገው፡፡
በሮቢንሰን ልዩ ችሎታ የተደነቀው የበረራ ትምህርት ቤቱ ነጭ ዳይሬክተር ሮቢንሰን የበረራ ማስልጠኛ ትምህርት ቤት እንዲገባ ፈቀደለት፡፡ ጆን ሮቢንሰን በዚህ የበረራ ትምህርት ቤት ገብቶ ለመሰልጠንም የመጀመሪያ ጥቁር አሜሪካዊ ኾነ፡፡
ትምህርቱን ካጠናቀቅም በኋላ ያለ ምንም ቀለም ልዩነት የበረራረ ትምህርትን የሚሰጥ ተቋም በዘሜሪካ በማቋቋም ብዙዎችን በበረራና በአቬዬሽን ሙያ አሰልጥኖ ለመርቃት
እንዲበቁ አደረገ፡፡
2-የፋሽስት ወረራና የጥቁር አሜሪካውያን ቁጣ
ለአፍሪካ አሜሪካውያንና ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ቀንደሊል ብርሃን ኾና የምትታየው ኢትዮጵያ በኢጣሊያ ፋሽስት መወረሯ በአሜሪካ በተሰማ ጊዜ በርካታ ጥቁር አሜሪካውያን ከኢትዮጵያውየን ጎን ኾነው ለመዋጋት ጠየቁ፡፡ ግና በአሜሪካ
ሕግ መሠረት አሜሪካ በምታደርገው ጦርነት ካልኾነ በስተቀር አሜሪካዊ ዜጋ ኾኖ ሌላ አገር መዋጋት አይቻልም፡፡ ይሁን እንጂ አፍሪካ አሜሪካውያን የአሜሪካን አደባባዮች በተቃውሞ
ሰልፍ ማናወጥ ያዙ፡፡
ከጣሊያን ወረራ በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው ኮ/ል ሮቢንሰን የኢምፔሪያል ኢትዮጵያን አየር ኃይልን፣ ኦርማ ጋራዥንና እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊትን የኤሌክትሪክና
የመካኒካል ኢንጂነሪንግ ክፍል በማቋቋም ከፍተኛ የኾነ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ አሜሪካ የተመለሰው ሮቢንሰን የኢትዮጵያ በፋሽስት ኢጣሊያ መወረሯን በሰማ ጊዜ አፍሪካ አሜሪካውያንና ሌሎች በአሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያኖች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ለመርዳት እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመሩ፡፡
የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ቀንዲልና ብቸኛ ተስፋ የኾነችው ኢትዮጵያ በፋሽሽት ኢጣሊያ መወረር ዕረፍት የነሣው ሮቢንሰን እ.ኤ.አ. በ1936 አሜሪካን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት
የኢትዮጵያን አየር ኃይልንና አርበኞችን በመቀላለቀል በተለያዩ ግንባሮች የኢትዮጵያውያንን የነጻነት ተጋድሎ ዋና አጋር
ለመኾን በቃ፡፡ ኮ/ል ሮቢንሰን በኦጋዴን ግንባር ከጥቁር አንበሳ ኃይሎች ከእነ መላኩ በያን ጋር በመኾን የላቀ አስተዋጽኦ ማድረጉን ዮሹዋ እስራኤል The Lion and the Condor:
The Untold Story of Col. John Robinson and the
Crippling of Ethiopia መጽሐፉ በሰፊው ተርኮታል፡፡
3- የዮሹዋ እስራኤል ቁጭት የወለደው የኮ/ል
ሮቢንሰን ታሪካዊ መጽሐፍ ለኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክና የነጻነት ተጋድሎ ልዩ
አክብሮት ያለው አፍሪካ አሜሪካዊው የታሪክ ተመራማሪ ዮሹዋ እስራኤል ይህን የኢትዮጵያ ባለውለታና የኢትዮጵያውያን
የቁርጥ ቀን ወዳጅ የኾነውን የኮ/ል ጆን ሮቢንሰን ታሪክ እንዲጽፍ ያስገደደውን ምክንያቱን እንዲህ ሲል በአጭር ቃል
ይገልጸዋል፡፡ ‹‹My quest was to find out why Col.
Robinson’s legacy had been forgotten and had
gone unrecorded in Ethiopian history …››
በእርግጥም ዛሬ በኩራት ስለምንናገርለት የአገራችንና የሕዝባችን ነጻነትና ሉዓላዊነት መከበር ከአፍሪካ እስከ አሜሪካ ከአውሮፓ እስከ ኤዥያ፣ ኩባ፣ ጃማይካና ካረቢያ ድረስ ትልቅ
መሥዋዕትነትን የከፈሉና የዘነጋናቸው የኢትዮጵያውያን የቁርጥ ቀን ወዳጆችና ባለውለታዎች አሉ፡፡ አሜሪካዊው ዮሹዋ
እስራኤል ከእነዚህ የአገራችን ነጻነት ባለውለታዎች መካከል በሚወዳት ኢትዮጵያ በአውሮፕላን አደጋ ስላረፈውና መካነ መቃብሩ በአዲስ አበባ ጉለሌ ስለሚገኘው ስለ አርበኛው ኮ/ል ሮቢንሰን ለበርካታ ዓመታት ምርምርና ጥናት አድርጎ የጻፈውን
መጽሐፍ አበርክቶልናል፡፡
ዮሹዋ ይህን መጽሐፍ ሲያዘጋጅ መረጃ በማሰባሰብና ሮቢንሰንን የሚያውቁ እድሜ ባለጠጋ የኾኑ ኢትዮጵውያንና አፍሪካ አሜሪካውያንን በማነጋገር በርካታ ዓመታትን አሳልፏል፡፡
በዚህ ምርምርና ጥናት ለኢትዮጵያ ታሪክና ቅርስ ልዩ ክብር ያላቸው እንደእነ ኢንጂነር ታደለ ብጡል፣ ፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስትና ሪታ ፓንክረስት፣ ካፒቴን አለማየሁ አበበ፣ካርዲናል ብፁዕ ብርሃን ኢየሱስ፣ ሀጂ ሀምዛ፣ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር፣ የቀድሞ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ፕሬዝዳንት መ/አ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ … እና ሌሎችም የዚህን
የኢትዮጵያ ባለውለታ የኮ/ል ሮቢንሰን ታሪክ ትንሣኤ እንዲያገኝ ያደረጉትን አስተዋጽኦና እገዛ ዮሹዋ በመጽሐፉ ውስጥ ከምስጋና እና ከልዩ አድናቆት ጋር ገልጾአል፡፡
ባሳለፍነው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ኢትዮጵያን የጎበኙት የመጀመሪያ ጥቁር አሜሪካዊ ፕ/ት ባራክ ሑሴን ኦባማ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተደረገላቸው የእራት ግብዣ ላይ፣
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጅና ባልደረባ የኾነውን ኮ/ል ጆን ሮቢንሰን በተመለከተ ባደረጉት ንግግራቸው እንዲህ ነበር ያሉት፣ ‹‹Colonel John Robinson, an American who
was one of the fathers of the Tuskegee Airmen,
nicknamed the Brown Condor, came to Ethiopia
and trained Ethiopian pilots to tame their
heavens and helped to set up the Ethiopian air
Force.››
በዚሁ ታሪካዊ የእራት ግብዣ ላይ ጠቅላይ ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝም በዚሁ የእራት ግብዣ ላይ ስለዚህ ጀግና
የኢትዮጵያ ወዳጅ እንዲህ አስታውሰውታል፣
I feel this an appropriate moment to mention one
African-American hero who came to Ethiopia in
1935 to help us in our struggle against Fascism
and colonial aggression. Colonel John Robinson
was the first American to take up arms against
Fascism. Colonel Robinson was responsible for
founding the Ethiopian Air Force during the
Italian Invasion. Called the Brown Condor of
Ethiopia, he became the first Commander of the
Air Force. He was a wonderful example of those
Americans who actively supported Ethiopia in
time of both peace and conflict.
በመጨረሻም አንድ ነገር ለማለት እወዳለኹ፡፡ የኢትዮጵያ ጥንታዊት ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ጀግኖች አርበኞች-
አባቶቻችንና እናቶቻችን በዱር በገደሉ ከፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ጋር ተፋልመውና ክቡር የሕይወታቸውን ሠውተው በዓል አቀፍ
መድረክ ዳግመኛ የአገራችንን የኢትዮጵያን ነጻነትና ሉዓላዊነትን ያበሰሩበትን 70ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ መታሰቢያ በዓል ለማክብር በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደኾነ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም መንግሥትም ኾነ የኢትዮጵያ ጥንታዊት ጀግኖች አርበኞች ማኅበር እንደእነ ኮ/ል ጆን ሮቢንሰን ያሉ የዘነጋናቸውን የአገራችንና የሕዝባችን ባለውለታና የቁርጥ ቀን ወዳጅ የኾኑ ጀግኖች፣ አርበኞቻችንን በዚህ የነጻነት/ድል በዓላችን የ70ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ መታሰቢያ በዓል
ላይ በሚገባ የሚዘከሩበት ታሪካቸውና ገድላቸው የሚነገርበት እንዲሆን እንደሚገባው በማስታወስ በአፍሪካ አሜሪካዊው አርበኛው፣ በኮ/ል ጆን ሮቢንሰን ታሪክ መጽሐፍ ላይ ያደረኩትን አጭር ዳሰሳ ላብቃ፡፡
ሰላም!!
እኔም ለዛሬ በዚህ ላብቃ በተረፈ በሌላ ፅሁፍ ለመገናኘት ያብቃን።

Source: Facebook
Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”