የፕሮስቴት ካንሰር መንስኤ እና የህክምና መፍትሄዎቹ

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
User avatar
Ethiopian News
Leader
Leader
Posts: 967
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

የፕሮስቴት ካንሰር መንስኤ እና የህክምና መፍትሄዎቹ

Unread post by Ethiopian News »

ላንቺና ላንተ ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ

“እኔ ስሜ ኃይሉ ተሰማ ሲሆን እድሜዬም ወደ 70
አመት ደርሶአል። የኖርኩትም በአዲስ አበባ መገናኛ
አካባቢ ነው። የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ሽንትን
በመሽናት በኩል ሕመም ገጠ መኝ። ሽን በጣም
ይወጥረኛል። እሸናለሁ ብዬ ስሞክር ግን በጣም
ትንሽ ሽንት እሱም በምጥ በመከራ ይፈሰኛል። ሽን
እንደሽንት ሳይሆን ቁርጥ ቁርጥ እያለ ነው የሚፈሰው።
በጣም ተሰቃ የሁኝ። በሁዋላም ወደሐኪም ቤት
ስሔድ ምርመራውን በቁጥር ለይተው ነገሩኝ። ጉዳዩ
የህክምና ቋንቋ ስለሆነ ለኔ ባይገባኝም ግን አሁን
ያለኸው 80 ቁጥር ላይ ነው። እጢው እያደገ ከሄደ
ችግር ስለሚያመጣ ቶሎ ይውጣ አሉኝ። እኔም እሺ
ብዬ ኦፕራሲዮን ልሆን ስል አ.አ.ይ ቁጥሩ እስከ 90
እስኪደርስ ድረስ ባለበት ሁኔታ እርዳታ ማግኘት
ትችላለህ የሚል ሌላ ምክር ተነገረኝ። ከቤተሰብ
ጋርም ተመካክሬ ኦፕራሲዮን በመሆኑ ተስማምተን
ተሰራልኝ። ከዚያም ሐኪሙ በ15 ቀኑ ሁኔታው ታይቶ
የታሸገበት እና የሽንት መሽኛው ቱቦ ሊነሳልህ ይችላል።
ለክትትሉ ግን በየ5 ቀኑ እየመጣህ ቁስሉ ይጻዳዳልሀል
ስላለኝ ይህንኑ ጀመርኩ። ከዚያም ነርስዋ ...አ.አ.ይ
የእርስዎ እኮ ድኖአል። 15 ቀን አያስፈልገውም።
እንዲያውም ላውጣልዎት ? ብላ ስትጠይቀኝ...
ከዳንኩና ካላስፈለገ እማ እሺ አልኩዋት። እሱዋም
ከሐኪም ሳትማከርም ሆነ ሳትታዘዝ...እኔም ሐኪሜን
ላማክር ሳልል ...በተሰራው ስራ ግን የከፋ ችግር
ውስጥ ወደቅሁ።
ነርስዋ ካሩን ስታወጣ ወዲያው የተፈጠረው
ነገር... ሽንት በሶስት አቅጣጫ መፍሰስ ሆነ። አንድ...
ካሩ በገባበት ቀዳዳ...ሌላው ኦፕራሲዮኑ በተሰራበት
በኩል...ሶስተኛው በራሱ በብል ሽንቱ በፈለገበት
ጊዜ መፍሰስ ጀመረ። ከዚያም ችግሩ ለሐኪሙ
ሲነገረው...መጀመ ሪያውኑስ ለምን ተፈታ...ለምን
ካሩ ወለቀ? ገና መቼ ቁስሉ መጠጠ ብሎ ተቆጣ።
ነገር ግን በእኛ በኩል እንደመብት ለምን ተደረገ ብሎ
ለመጠየቅ አልቻልንም። ሳትታዘዝ ካሩን የነቀለችውን
ነርስም ድጋሚ ማግኘት አልተቻለም። የፕሮስት
እጢን ማውጣት በጣም ቀላል ሕክምና ነው ሲባል
እሰማ ነበር። ነገር ግን አጋጣሚው ሆነና ይኼው
ሳልድን ወደሁለት አመት ሊሆነኝ ነው። እስከአሁን
ድረስ ወደሶስት ጊዜ ኦፕራሲዮን ተሰርቶልኛል። ገና
ወደፊትም የሚሰራ መሆኑ ነው የተነገረኝ።”
ኃይሉ ተሰማ... ከመገናኛ

Image

ስለፕሮስቴት እጢ ወይንም ካንሰር አንዳንድ
እውነታዎችን ለዚህ እትም ማብራሪያ እንዲሰጡን
የጋበዝናቸው ዶ ር ኢብራሒም መሐመድ ይባላሉ። ዶ
ር ኢብራሒም በሀያት ሆስፒታል የሚሰሩ አጠቃላይ
የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ሲሆኑ በዩሮሎጂስትነት ልዩ
ሐኪም ናቸው። በዚህም ሽንት ባንቧ ፣ኩላሊት እና
ፕሮስትን ያክማሉ።
ጥያቄ፡ ፕሮስቴት (Prostate) ምንድነው?
መልስ፡ ፕሮስቴት ወንዶች ላይ ብቻ የሚገኝ እጢ
ነው። ፕሮስት የሚገኘው ከፊኛ ስር ነው። ፕሮስት
የሽንት ቧንቧ በውስጡ የሚያልፍበት ነው። ፕሮስት
የሚያመነጫቸው ፈሳሾች አሉ። የእነዚህ ፈሳሾች
አንዱና ዋነኛው ስራ በወንዴው የዘር ፍሬ ወይንም
ፈሳሽን እንደምግብ የሚያከፋፍል ነው። በዚሁ ዙሪያ
ማለትም ከዘር ፈሳሽና ከፈርቲሊቲ ጋራ የተያያዙ
ጥቅም የሚሰጡ ንጥረ ነገሮች አሉት።
ጥያቄ፡ ፕሮስት ቃሉ የአማርኛ ስያሜ የለውም?
መልስ፡ ፕሮስት አማርኛ የለውም። ፕሮስት
በየትኛውም ቋንቋ የሚነገር ተመሳሳይ አረዳድ ያለው
ቃል ነው።
ጥያቄ፡ ፕሮስት እራሱ እጢነው? ወይንስ በውስጡ
እጢ አለ?
መልስ፡ ፕሮስት በእንግሊዝኛው አጠራር ግላንድ
ማለትም እራሱ እጢ ነው። በየትኛውም የሰውነት
ክፍል እንደሚገኘው ለምሳሌ ታይሮይድ ግላንድ
ወይንም በጡት ውስጥ እንደሚገኝ ግላንድ ማለት
ነው። ነገር ግን በአማርኛው እጢ ሲባል እንደቲዩመር
ያሉ የበሽታ እጢዎች ስላሉ ሊያሻማ ይችላል። ስለዚህ
ፕሮስት እጢ በተጨማሪም በቅንፍ ግላንድ የሚለው
ቢገለጽ ትክክለኛውን ትርጉዋሜ ያሳያል። ነገር ግን
የፕሮስት በሽታዎች ከሚባሉት አንዱ እጢ ስለሆነ
እንደመጠሪያም እንደበሽታም ሊገለጽ ነው ማለት
ነው። ስለዚህ ፕሮስት ግላንድ ቢባል የማያሻማ ስያሜ
ይሆናል።
ጥያቄ፡ ፕሮስት እጢ ሕመሙ ስንት አይነት ነው?
መልስ፡ ፕሮስት እጢ ሁለት አይነት ሕመም
አለው። አንዱ ካንሰርነት የሌለው በእድሜ ተያይዞ
የሚመጣ የፕሮስት ማበጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ
የፕሮስት ካንሰር ነው። ካንሰር እንደሚታወቀው
የተለያየ አካል ውስጥ የሚበቅል በሽታ እንደመሆኑ
በፕሮስት ውስጥም ሊፈጠር ይችላል።
ጥያቄ፡ ፕሮስት የሚያብጠው በየትኛው የእድሜ
ክልል ነው?
መልስ፡ የፕሮስት ግላንድ ወይንም እጢ
የሚያብጠው ወንዶች እድሜያቸው ሲገፋ ማለትም
ከ50 አመት ጀምሮ ነው። ነገር ግን ሁሉም ሰው ፕሮስቱ
ስላበጠ ብቻ በዚያ ምክንያት ችግር ይደርስበታል
ማለትም አይደለም። የፕሮስቱ ማበጥ የሚያስከትለው
ሕመም ደረጃው በተለያየ ሁኔታ ሽንትን እንደለመዱት
ማለትም እንደልብ መሽናት አለመቻል ነው። ፕሮስቱ
የሚገኘው ከፊኛ አፍ ስር ነው። የሽንት ቧንቧው
ማለትም ከፈኛ ሽንትን ወደውጭ የሚያወጣው አካል
በፕሮስቱ መሐከል ሰርስሮ የሚሄድ ነው። እጢው
እብጠት ካለው ቱቦውን ስለሚያጠበው ሽንቱ
እንደልብ ሊያልፍ ስለማይችል ችግር ይፈጠራል።
ካንሰርነት የሌለው የፕሮስት እጢ እብጠት መሆኑም
የሚታ ወቀው በሽተኛው ሽንቱን እንደልብ መሽናት
ሲያቅተው ነው። ሽንት ቶሎ ቶሎ ለመሽናት
መሞከር ፣ትንሽ ትንሽ ጠብታዎች መሆኑ ፣በምጥ
መልክ መሰቃየቱ አንዳንዴም ሽንቱን እስከመዝጋት
የሚያደርስ ሲሆን ሕመሙ እብጠት ነው ማለት
ይቻላል።
ጥያቄ፡ በሽታው ከምን ተነስቶ ነው ካንሰር
ከሚባለው ደረጃ የሚደርሰው?
መልስ፡ ካንሰሩና እብጠቱ በምንም አይገናኙም።
ብዙ ሰዎችም ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን
እብጠትም ወደካንሰርነት ይለዋጣል ብለው
ስለሚሰጉ ይውጣልኝ ይላሉ። ነገር ግን ስላበጠ
ወደካንሰርነት ይለወጣል የሚል ሳይንስ የለም።
ሕመሙን በተመለከተ ግን ካንሰሩም ቢሆን አንደኛው
መገለጫው ልክ እንደእብጠቱ የመሽናት ችግር ሲያስ
ከትል ነው። ነገር ግን ካንሰሩ ለየት የሚለው ሕመሙ
ትንሽ ደረጃ ላይ እያለም መሽናትን ሊያውክ መቻሉ
ነው። ሌላው የሚለይበት ነገር ካንሰሩ ወደሌላ አካል
ላይ ማለትም በሳንባ ወይም በአእምሮ በመሳሰሉት
ስፍራዎች ሊሰራጨ ይችላል።
ጥያቄ፡ ፕሮስት እብጠት ወይንም ካንሰር በምን
ምክንያት ይከሰታል?
መልስ፡ የፕሮስት እጢ ወይንም ካንሰር መንስኤ
እስከአሁን በትክክል አልታወቀም። ነገር ግን አንዳንድ
እንደመንስኤ የሚጠቀሱ ነገሮች አሉ። በዘር በቤተሰብ
የሚተላለፍ ነው ተብሎ የሚገመትባቸው መንገዶች
አሉ። ለምሳሌ በአሜሪካ በተደረገ ጥናት በከፍተኛ
ደረጃ ሕመሙ የተገኘው በአፍሪካ አሜሪካውያን ላይ
ነው። ከእርሱ በመቀጠል ደግሞ ነጮቹ በሕመሙ
የሚሰቃዩ መሆኑ ተረጋግጦአል። ከዚያ በሁዋላ
ላቲኖች ከእነርሱ ቀጥሎ ደግሞ ኤሽያኖች እያለ
ነው ደረጃው የተቀመጠው። ምክንያቱ አሁንም
በውል የተለየ ስላልሆነ ምናልባት በዘር የሚተላለፍ
የሚለው እንደ አንድ ምክንያት እንዲቆጠር ግድ
ሆኖአል። ከዚህ በተጨማሪም የመኖሪያ አካባቢ
የሚለውም እንደአንድ ምክንያት የሚቆጠርበት ሁኔታ
አለ። ለምሳሌ ኤሽያኖች በአገራቸው የሚኖሩትና
በአሜሪካ የሚኖሩት በሕመሙ የመያዛቸው ደረጃ
ስለማይመሳሰልና በአብዛኛው በአሜሪካ የሚኖሩት
ላይ ስለተከሰተ የመኖሪያ አካባቢ እንደ አንድ ምክንያት
ሊቆጠር ይችላል። ፣የአመጋገብ ሁኔታ፣ እንዲሁም
የአካል እንቅስቃሴ አዘውትሮ አለማድረግ የመሳሰሉት
እንደችግር ከሚጠቀሱ መካከል ናቸው።
ጥያቄ፡ የፕሮስት ካንሰር ይበልጥ የሚያጠቃው
የአለም ክፍል አለ?
መልስ፡ በእኛ ሐገር ይህን ያህል ሰዎች በዚህ
ምክንያት ሕመሙ አግኝቶአቸዋል ለማለት የሚያስችል
ጥናት የለም። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግን ፕሮስት
ካንሰር በአለም ላይ የሌለበት አገር የለም። በ2009
በተደረገ ጥናት የፕሮስት ካንሰር በአሜሪካ አገር
በወንዶች ላይ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠ የካንሰር
ሕመም ነው። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት
በአለም አቀፍ ደረጃ የፕሮስት ካንሰር 5ኛ አምስተኛ
ደረጃ የተሰጠው ሕመም ነው። ይህ ደረጃ የተሰጠው
ወንዶችንም ሴቶችንም የሚይዙ ካንሰሮች ጋራ
ተደምሮ ደረጃ ሲሰጥ በብዛት በደረጃ አምስተኛ መሆኑ
ተረጋግጦ ነው። ብዙ ሰዎች በዚህ ሕመም ምክንያት
ይታመማሉ ከስራ እንቅስቃሴያቸው ለመታገድ
ይገደዳሉ። ከዚያም አልፎ ፕሮስት ካንሰር ሕይወትን
እስከመቅጠፍ ይደርሳል።

ይህንን አምድ አዘጋጅቶ የሚያቀርብላችሁ
ESOG-Ethiopian Society of Obstetricians and Gynecologists
(የኢትዮዽያ የፅንስና የማህፀን ሀኪሞች ማኅበር) ነው። (በፖ.ሣ.ቁ 8731 ስልክ 011-5-506068/69 ልታገኙን ትችላላችሁ)

Source: AddisAdmass Newspaper
Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”