ኢትዮጵያ(ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ)

Love, Relationship, Habesha intimate, Ethiopian girls,
ፍቅር ፣ ጋብቻ :ጉዋደኝነት: እንተዋወቅ:
Forum rules
NO Rated R Pictures! please. :)
Post Reply
User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

ኢትዮጵያ(ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ)

Unread post by girreda » 19 Dec 2009 10:49

ኢትዮጵያ(ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ)

ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ መሠረቱ ግሪክ ሲሆን ከክርስቶስ ልደት በፊት በውል ከታወቀችው ከግብፅ በስተደቡብ የሚገኘው የአፍሪቃ ክፍልና ደቡብ ምዕራብ እስያ የሚጠሩበት አጠቃላይ ስም ነበር፡፡ ይሁንና ከክርስቶስ ልደት በኋላ አገባቡ ጠበብ እያለ አሁን ኢትዮጵያ የምትገኝበት አካባቢ መጠሪያ ለመሆን በቃ፡፡ ስያሜውን ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ በጠበበና እስካሁንም ቋሚ በሆነ መልኩ የምናገኘው በ4ኛው ምእተ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የክርስትናን እምነት የተቀበለው የአክሱም ንጉሥ ዔዛና በድንጋይ ላይ ባስቀረፀው አንድ ጽሑፍ ላይ ራሱን የኢትዮጵያ ንጉሥ ብሎ ሲጠራ ነው፡፡ ከዚያም በተከታታዮቹ ምእተ ዓመታት በጊዜው በተጻፉ ጽሑፎች አክሱም የኢትዮጵያውያን ከተማ፣ አፄ ካሌብ ደግሞ የኢትዮጵያውያን ንጉሥ ተብለው ሲጠቀሱ ስናይ ስያሜው ቋሚ መልኩን እየያዘ መምጣቱን እንረዳለን፡፡ በ14ኛው ምእት ዓመት መጀመሪያ ላይ የተጻፈው ክብረ ነገሥት የተሰኘው ንግሥተ ሳባ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ያደረገችውን ጉዞ የሚያትተው መጽሐፍም፣ ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ በአሁኒቱ ኢትዮጵያ ካለችበት ግዛት ጋር ያለውን መያያዝ ኦፊሲዬል አድርጎታል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ነገሥታት መደበኛ መጠሪያቸውም "ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ" ወይም "ንጉሠ ኢትዮጵያ" ሆኖ ቆይቷል፡፡

(ባሕሩ ዘውዴ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1848 እስከ 1966፣ 1989)

User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

ታዳጊው መስማት ከተሳነው ከ9 ዓመታት በኋላ መስማት ቻለ

Unread post by girreda » 19 Dec 2009 10:51

ታዳጊው መስማት ከተሳነው ከ9 ዓመታት በኋላ መስማት ቻለ

ለዘጠኝ አመታት ያህል መስማት የተሳነው ታዳጊ ሕፃን ጃሮሜ ባርተንስ በድንገት መስማት የቻለው ጆሮው ውስጥ ተቀምጦ የነበረው የጆሮ መጥረጊያ በድንገት መውጣት በመቻሉ ነበር፡፡

የ11 ዓመቱ ባርተንስ ከህፃንነቱ ጀምሮ በቀኝ ጆሮው በኩል መስማት አይችልም ነበር ሲል ዴይሊ ሜይል ዘግቧል፡፡

“ድምፅ የሰማሁት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ፑል ስጫወት ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜም ሁሉንም ነገር ለማዳመጥ ተቸግሬ ነበር፡፡ አሁን ግን እየለመድኩት መጥቻለሁ፡፡ ከእንግዲህ ጓደኞቼ ጮክ ብለው እንዲያወሩልኝ አልፈልግም፡፡ የቴሌቪዥንም ሆነ የቴፕ ድምፅ ከፍ አድርጌ ማዳመጥም አይጠበቅብኝም” ሲል ባርተንስ ደስታውን ገል”ል፡፡

የሁለት ዓመት ሕፃን እያለ ጆሮው ውስጥ የጆሮ መጥረጊያውን ከቶ ሊሆን እንደሚችል የጠረጠሩት ወላጆች የህክምና ኤክስፐርቶች እስካሁን ድረስ የልጃቸውን ያለመስማት ችግር አለማወቃቸው አስገራሚ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
[/color]
Last edited by girreda on 29 Dec 2009 05:09, edited 2 times in total.

User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

Re: ኢትዮጵያ(ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ) የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ምንጭ ከየት ነው?

Unread post by girreda » 19 Dec 2009 10:53

የኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥልጣኔ የት መጣ ሲነሳ፣ በተለይም ከዘመነ አክሱም ወዲህ የታየው የፊደል፣ የጥበባተ ዕድና ልዩ ልዩ ሥልጣኔዎች መነሻ አስመልክቶ የተለያዩ ሐሳቦች ሲራመዱ ኖረዋል፡፡

ሲባሉ፣ ሲጻፉ ከኖሩት በአነስተኞቹም ሆነ በከፍተኛዎቹ የትምህርት ተቋማት ሲራመዱ ከነበሩት መካከል የሚዘወተረው የአገሪቱ ሥልጣኔ መነሻ በተለይ ከደቡብ ዓረቢያ ፈልሶ በመጣ ሕዝብ አማካይነት የሚለው ነው፡፡

ይህም በውጭ ሀገር ምሁራንና የእነርሱን አሰር በተከተሉ ኢትዮጵያውያን በዋናነት የተቀነቀነ ነው፡፡ "የለም፤ ጥንተ ሥልጣኔው መነሻው ሀገር በቀል ነው፡፡ ከባሕር ተሻግሮ የተተከለ ፣መጤ፣ አይደለም" ብለው የሞገቱ ኢትዮጵያውያንም ባሕር ማዶዋውያንም አሉ፡፡

ለዚህ ጽሑፍ መጻፍ ሰበብ የሆነው ባለፈው ሐምሌ ወር መገባደጃ በአገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለንባብ የበቃው የዶክተር ግርማ አውግቸው "ማሻስ Origin of ቂሻሮቈሽሰ" (ዘ ኦሪጅን ኦፍ አምሃሪክ) ጥናታዊ መጽሐፍ ነው፡፡

አማርኛ ከሴማዊና ኩሻዊ (ሴሚቲክና ኩሽቲክ) በድቅል የተገኘ ተደርጎ በመላምት የተነገረውን አስተሳሰብ የሚሞግት፣ ስለ አማራ ማንነትና ምንነት የሚፈትሽ መጽሐፍ ነው፡፡

ስለ አማርኛ ከሚነገሩት አፈ ታሪኮች ሁለቱ የሚከተሉት ናቸው፡፡ አንደኛው "አንድ ግእዝ ያልሆነ ከግእዝ ጋራ የተቀራረበ ቋንቋ ከሰሜን ከአክሱም አካባቢ ተነስቶ ወደ ደቡብ ወረደ፤ በተለይ ከአገውኛ ጋር ተቀላቀለ፤ በአገው አካባቢ በኩሽና ኦሞቲክ ቋንቋዎች ተናጋሪ ከሆኑት ወታደሮች ጋር ርስ በርስ ለመግባባት እንዲያመች ተዳቅሎ ተፈጠረ የሚል ነው፡፡ ሌላው አፈታሪክ ደግሞ "ቀሳውስትና ደብተራዎች ከግእዝና ከትግርኛ በማውጣጣት ለንግግር የሚመች ቋንቋ ፈጠሩ" የሚለው ነው፡፡ በተለያዩ የሥነ ልሳን ምሁራን የተነሳው የድቅልነት መላምት በየማስተማሪያ መጽሐፍ (በታሪክ፣ በአንትሮፖሎጂና ሥነ ልሳን) ውስጥ በመግባቱ በስፋት መወሰዱ ስህተት መሆኑን መጽሐፉ ያመለክታል፡፡

ሁለተኛው ነጥብ አማርኛ ከግእዝ መጣ የሚባለው ነው፡፡ ዱሮ የሚታወቀው አስተሳሰብ፣ ግእዝ ከሳብኛ መጣ፤ ግእዝ የሁሉም ቋንቋዎች አባት ነው፣ ትግርኛንም ትግረንም ወለደ የሚል ነው፡፡

አማርኛን አንዳንዶች ከኩሽቲክና ሴሜቲክ በድቅል የተፈጠረ ነው ይላሉ፡፡ በቋንቋ ቤተሰብ ክፍፍል ሲመጣም አማርኛ የሴም መሆኑ፣ ከአርጎብኛ እንደሚመደብ ይነገራል፡፡ የሴም ከሆነ እንዴት ድቅል ይሆናል? ከግእዝና ትግርኛስ ጋር ተቀላቅሎ እንዴት ሊወጣ ይችላል የሚል ጥያቄ የሚያስነሳና የሚጋጭ ሐሳብ ነው፤ የሚሉት ዶ/ር ግርማ፣ እነዚህን የተሳሳቱ ነገሮችን ለማስተካከል መጽሐፉን ያዘጋጁት መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

አማርኛ የሴማዊ ቋንቋ ቤተኛነቱ እንጂ ድቅል አለመሆኑ የሚያሳዩ ገጽታዎች መኖራቸውን ያመለከቱት ዶ/ር ግርማ፣ አማርኛ ያገሪቱ የጋራ መግባቢያ ሆኖ ለሺሕ ዓመታት የዘለቀ በኩሽቲክ ተጽዕኖ ሥር ያለፈ፣ ኦሞቲክም የዳሰሰው ቢሆንም በቋንቋው ውስጥ ሴማዊ ያልሆኑ ባሕርያት በሰዋሰውም ሆነ በቃላቱ ውስጥ ቢኖሩትም በድቅል ተፈጠረ አያሰኘውም ብለዋል፡፡

በዶ/ር ግርማ ጥናት፣ አማርኛና አርጎብኛ ሁለቱ ትስስር ያላቸውና የጋራ አባት ቋንቋ (Proto-Amharic-Argoba) እንዳላቸው የሚያሳዩ ሥነ ልሳናዊና ታሪካዊ ነጥቦች አሉ፡፡ የደቡብ ኢትዮ ሴሜቲክ መደብ ውስጥ ያሉት አማርኛና አርጎብኛ ዘዬያዊ ልዩነት መፍጠር የጀመሩት ከ9ኛው ምእት ዓመት ጀምሮ ነው፡፡

በተለይ የተለያዩ ቋንቋዎች ሆነው የተገኙት በጣም በቅርቡ በ17ኛው ወይም 18ኛው ምእት ነው፡፡

በዶ/ር ግርማ አገላለጽ፣ የአማርኛ መስፋፋትና ዕድገት የመጣው የሓቈቄ..ቄ..ቂሻሮቈሽሰ..ቈሸቄሯሮ ተናጋሪዎች ጥንተ መሠረታቸው ከሆነው ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች፣ ወደ ሰሜን ምሥራቅና ደቡብ መሰራጨታቸው ነው፡፡

አማርኛ ከአርጎባ ተለይቶ መስፋፋት የጀመረው ደግሞ ቋንቋው ከ13ኛው መቶ ጀምሮ የአስተዳደር ቋንቋ ከሆነ በኋላ ነው፡፡

አማርኛ በኋላ የተዋቸው ግን ዱሮ ይጠቀምባቸው የነበሩ አሁን በአርጎብኛ ውስጥ ያሉ ቃላት አሉ፡፡ ለምሳሌ ወግር - ደህና ማለት ሲሆን፣ ጌይ ደግሞ አገር ማለት ነው፡፡ በ15ኛውና 16ኛው መቶ ዘመን በተጻፉ የአማርኛ ጽሑፎች ውስጥ ያሉ ቃላት በአርጎብኛ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ከአማርኛ ይልቅ የአማርኛን ጥንታዊ ገጽታ አርጎብኛ ያሳያል፡፡

አማራ
በመጽሐፉ አንድ ንኡስ ምዕራፍ ውስጥ ስለ ..አማራ.. ስያሜ ምንነትና ይዘት፣ የሚገልጽ ክፍል አለው፡፡ አማራ በአሁን ጊዜ ለብሔር መጠሪያነት ይዋል እንጂ ከዚህ ቀደም የማኅበራዊ ተቋም መገለጫ እንደሆነ ነው የሚያስረዳው፡፡ በዶ/ር ግርማ ማብራሪያ በቤተሰብ ደረጃ ገብተው ያጠኑ አንትሮፖሎጂስቶች እንደሌሎቹ ብሌረሰቦች ብሔረሰባዊ ግንኙነት የለውም፡፡ ያላቸው ግንኙነት ማኅበራዊ ተዋረድ ነው የሚል ነገር አምጥተዋል፡፡ ከታሪክ አንፃር ሲቃኝም በዘጠነኛው መቶ ዘመን አማራ የሚባል ቦታ መኖሩ ተጠቅሷል፡፡ አሁንም አማራ ሳይንት የሚባልም አለ፡፡

የ16ኛው ምእት ዓመት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ካርታ (ማፕ) እንደሚያሳየው አማራ በጎጃምና በአዳል መካከል ያለ ክልል ነው፡፡

በ14ኛውና 15ኛው ምእት ዓመት የዐረብ ጸሐፊዎች አማራን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር አያይዘው ያቀረቡበት ሁኔታ ተመዝግቧል፡፡ ከክርስትና ተከታይነት ጋርም ይዛመዳል፡፡

ኦሮምኛ ተናጋሪ ሆነው "አማራ ነን" የሚሉት፣ በጎጃም ያሉ ሙስሊሞች "አማራ እንዲህ አድርገውን" የሚሉትና፣ "አማራና እስላም ሆነናል" የሚለው ሁሉ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

አማራን በብሔረሰብ መጠሪያነት መጠቀም በቅርብ ጊዜ ቢጀመርም የተለያዩ ማኅበረሰቦች ማንነታቸውን ሲገልጹ የሚጠቅሱት ጎጃሜ፣ ተጉለቴ፣ መንዜ፣ ይፋቴ ወዘተ. በማለት ነው፡፡

በዴቪድ ሌቪን እንደተጻፈው፣ ከ14ኛው እስከ 18ኛው ምእት ዓመት ድረስ በተጻፉት ዜና መዋዕሎች አማራ የሚለው ቃል በወሎ ውስጥ ያለን መልክዐ ምድራዊ ሥፍራን የሚያመለክት ነው፡፡ በ1902 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ብዛት በ..ብሔረሰብ.. ስብጥር ሲያስቀምጥ ሸዌና ጎጃሜን በአማራ ውስጥ አላካተተም፡፡ ራሳቸውን ችለው ነው የቀረቡት፡፡

በንግሥት ዘውዲቱ ዘመን፣ ሰኔ 2 ቀን ሰኞ በአዲስ አበባ ለተካሄደው የፈረስ እሽቅድድም ውድድር የወጣው የአማርኛ ማስታወቂያ "አማራ" የሚለውን መጠሪያ ኢትዮጵያዊ ለማለትና 'ፈረንጅ" ከሚለው ለመለየት የተጠቀመበት ነው፡፡ ማስታወቂያው

ከስምንት የእሽቅድድም ዓይነቶች አምስተኛው፣ "የእንጦጦ ማሽቀዳደም ለአማራ ብቻ (Entoto Race For Abyssinians Only) የሚል ነው፡፡

ዶ/ር ግርማ የመረመሩት ሌላው ነጥብ፣ የፍልሰት መላምት ነው፡፡ የሴማውያን ሕዝብ ክፋይ ከደቡብ ዐረቢያ በመፍለስና ወደ ሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል በመግባት የራሱን ዓይነት ሥልጣኔ ገነባ፡፡ ቆይቶም የአክሱምን መንግሥት መሠረተ፡፡ በጊዜ ሂደትም ከአገሬው ተወላጆች ጋር እየተዛመደ በማዕከላዊ፣ ምሥራቃዊና ደቡባዊ ክፍል ኢትዮጵያ የሚገኙትን ያሁኖቹን ኢትዮ ሴሜቲክ ቋንቋዎች ፈጠረ፡፡ እንዲሁም ፈልሰው የመጡት ሴማውያን ቋንቋቸውን ብቻ ሳይሆን የዳበረ ሥልጣኔያቸውን ጽሕፈትን፣ ኪነ ሕንፃንና እርሻን አወረሱ የሚል መላምት ያራመዱት ተመራማሪዎች፣ መጤዎቹ ሴማውያን ካገር ተወላጆች የበለጠ ባህል ነበራቸው፣ ላልሰለጠኑት ሥልጣኔና ባህል አስተማሩዋቸው የሚልም አስተሳሰብ በየመጻሕፍታቸው አስርፀዋል፡፡

በዶ/ር ግርማ አገላለጽ፣ ይህ ዓይነት አነጋገር ሳይንሳዊ ሳይሆን ከዘረኝነት ስሜት የመነጨ ነው፡፡ የአፍሪካውያንን ጥንታዊ ሥልጣኔ ያበረከተውን አያሌ በረከት ለመካድ የተደረገ ጥረት ነው፡፡

የኢትዮ ሴሜቲክ እናት ቋንቋ ግእዝም ከሳባውያን የወረደ ነው የሚል ኀልዮት (ቲዮሪ) እስከ ቅርብ ጊዜ ተቀባይ ሆኖ የኖረ ነበር፡፡

ሴማዊ ቋንቋዎች ከውጭ መጡ፣ ሳቢኛ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ወደ ግእዝ ተለወጠ፡፡ የነገደ አግአዝያን (የነፃ አውጪዎች ነገድ) ቋንቋ ነው እየተባለ ለዘመናት በአፈ ታሪክ የሚነገረው ሥነ ልሳናዊ ማረጋገጫ እንደሌለው ዶ/ር ግርማ ይናገራሉ፡፡

በሳባ ፊደል የተጻፈ የድንጋይ ላይ ጽሑፍ የተገኘው ቅድመ ክርስቶስ 500 ዓመት ላይ ነው፡፡ ቀዳሚው የግእዝ ጽሑፈ ድንጋይ ተብሎ ሲታመን የነበረው በአራተኛው መቶ ዘመነ ክርስቶስ ላይ ነበር፡፡ በቅርብ ዘመናት የተገኙት ድንጋዮች ደግሞ ዘመኑን ወደ አንደኛው መቶ ይወስዱታል፡፡ በዶ/ር ግርማ ማብራሪያ በኢትዮጵያ የተገኙት በሳባ ቋንቋ የተጻፉት ጽሑፈ ድንጋዮች ሁለት ዓይነቶች ናቸው፤ አንደኛው በርካታ የግእዝ ተጽዕኖ ያለበት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ሳባዊ ብቻ ነው፡፡ በሳባ የተጻፉትን በጥልቀት ሲመረምሯቸው በአብዛኛው የግእዝ ተጽዕኖ ያደረባቸው ጥንታዊ ጽሑፎች ሆነው ተገኝተዋል፡፡

ይህም በኢትዮጵያውያን የተጻፈና ግእዝም የንግግር ቋንቋ በነበረበት ጊዜ መሆኑ ሳባውያን መጡ በተባለበት ጊዜ የዳበረ ጽሕፈት መኖሩን የሚያሳይ ነው፡፡

ግእዝ ከሳብኛ አልመጣም፡፡ ከሳብኛ ለመምጣቱ ምን ማስረጃ የለም፡፡ ይልቅ ሳብኛው ውስጥ የግእዝ ነገሮች አሉበት የሚሉት ዶ/ር ግርማ፣ ድንጋዮቹ በኢትዮጵያና በደቡብ ዐረቢያ መካከል ባህላዊ ግንኙነት መኖሩን ያሳያል እንጂ የግእዝ የትመጣ ከዚያ ነው አያሰኝም፡፡ የደቡብ ዐረቢያ ሰፋሪዎች የራሳቸው ዘዬና ሳባዊ ዕውቀት ይዘው መምጣታቸው ቢታወቅም ስለነርሱ ባህላዊ አላባዎች የመረመሩ የቅርብ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ግእዝ ወይም የማንኛውም ኢትዮ ሴማዊ ቋንቋ ቤተሰብ ዝርያው ከሳባው አይነሳም ብለዋል፡፡

ከፍልሰቱ መላምት (Migration Hypothesis) በተፃራሪ የቆሙት ምሁራን የሚያራምዱት፣ ዶ/ር ግርማ እንደሚሉት፣ የኢትዮጵያ ሴማዊ ቋንቋዎች እዚህ የነበሩ ናቸው፡፡ ከዐረቢያ አልመጡም፡፡ በተቃራኒው የሴም ቋንቋዎች ከዚህ ነው ወደዚያ የሄዱት፡፡ እንዲያውም ኢትዮ ሴማዊ ብቻ ሳይሆኑ የሴማውያን መነሻ ቋንቋ (Proto-Semitic) እና የአፍሮ እስያ (Afro Asiatic) የቋንቋ ቤተሰብ መፈጠሪያ ምንጫቸው ከኢትዮጵያ ነው የሚሉ ምሁራን አሉ፡፡ ቅድመ ክርስቶስ በዘጠነኛው ሺሕ ዓመት ላይ በምሥራቅ አፍሪቃ ስምጥ ሸለቆ፣ በደቡባዊ ኢትዮጵያና ሰሜናዊ ኬንያ ተደላድለው የነበሩት አፍሮ እስያቲኮች ወደተለያዩ አካባቢዎች መበታተናቸው ይነገራል፡፡

በበርናል አነጋገር የሴማውያን ቋንቋዎች ከስድስት ሺሕ ዓመታት በፊት ከኢትዮጵያ ወደ እስያ በመሄድ በአሲርያና ሶርያ ተሰራጭተዋል፡፡

የቅርብ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ አፍሮ እስያቲክ የቋንቋ ቤተሰብ መገኛው በአፍሪቃ ነው፡፡ ብዙ ተመራማሪዎች እንደሚሉት መወለጃው ቦታ ደቡባዊ ኢትዮጵያ ነው፡፡ የኢትዮ ሴሜቲክ መወለጃ ቦታ አንዳንዶች የጉራጌ ቋንቋዎች አሁን በሚነገሩበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሥፍራ ሲያደርጉት ሌሎች ሰሜናዊ ክፍለ ኢትዮጵያ ላይ ይወስዱታል፡፡

የኢትዮ ሴማዊ ቋንቋ ግንድ (Proto Ethio Semitic) የበለፀገው በደቡብ በጉራጌ ምድር ነው የሚሉት በኢትዮጵያ ካሉት 16 ኢትዮ ሴሜቴክ ቋንቋዎች ሦስቱ ብቻ በሰሜን ሲገኙ ሌሎቹ የደቡብ ኢትዮ ሴሜቴክ ቋንቋዎች በጉራጌ ዞን ይገኛሉ፡፡

የደቡብ ኢትዮ ሴሜቴክ ቋንቋዎች ግንድ ለሰሜኑ አያት ነው ይላሉ፡፡ የሰሜኑ የሦስት ሺሕ ዓመት ዕድሜ ሲገምቱት የደቡብ ከ4,000 እስከ 5,000 ዓመት ያደርሱታል፡፡ የጉራጌ አካባቢ በኢትዮጵያ ሴማዊ ቋንቋዎች መሠረትና የሴማዊ ቋንቋዎች መነሻ እንደሆነ ሊቃውንቱ እነ በርናል፣ ቤንደርና ብሌንች ያሰምሩበታል፡፡

ለዚህም ነው የጉራጌ ቋንቋዎች ከግእዝ ይልቅ ጥንታዊ ገጽታን በማሳየታቸው የግእዝ አያት ተደርገው ባንዳንዶች የሚታሰቡት፡፡

የግእዝ ጽሕፈት ምንጭ ከደቡብ ዐረቢያ መፃተኞች ጋር የሚያዛምዱት ግእዝ ፊደሉን ከሳባ ወስዶ ማሻሻሉን፣ አጻጻፉን መለወጡን፣ አናባቢን ጨምሮ ማስገባቱ ከአራተኛው መቶ ዘመን በኋላም የአበገደ ተራውን ወደ ሀለሐመ መለወጡን ይናገራሉ፡፡ ያራምዳሉ፡፡

ይህ አስተሳሰብ በቅርብ በተገኙ ግኝቶች እየተሻረ መሆኑን ዶ/ር ግርማ ያመለክታሉ፡፡ ቅጥልጥል (ክባዊ) ጽሕፈት በኢትዮጵያ የተገኘና ከግእዙ የዳበረ እንጂ ከሳብኛ ቀጥታ የመጣ አይደለም፡፡

አናባቢ የመጨመር ቴክኒክ በድንጋይ ላይ ጽሑፎች ላይ ዘግይቶ ይምጣ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ አናባቢ ጨምሮ የመጻፍ ልምድ ጥንታዊነት ያለውና በአናባቢ መጻፍም ከንጉሥ ኢዛና በፊት የተጀመረና በፓፒረስ፣ በብራና ወይም በሌላው መጻፊያ ላይ ሲጻፍ መኖሩን ዶ/ር ግርማ ጠቁመዋል፡፡ አንዱ ማሳያ በአክሱም በአንደኛውና ሁለተኛው መቶ (ድኅረ ክርስቶስ) የአክሱም ሳንቲሞች ላይ መገኘቱን ይህም ላናባቢ ምልክት መጻፍም የዘመኑ አንዱ ያጻጻፍ ዘውግ (ዓይነት) ሊሆን እንደሚችል ያመለከቱት ዶ/ር ግርማ፣ የ6ኛው ምእት ዓመት ክስተት አንዱ ማሳያ መሆኑን ያስረግጣሉ፡፡

"አዲሱን ባለ አናባቢ ጽሕፈት በ4ኛው ላይ አግኝተን ከሆነ 6ኛው ላይ ለምን አላናባቢው ተጠቀሙ?" በማለትም ይጠይቃሉ፡፡ ምናልባትም አንዳንድ ተመራማሪዎች እንደሚሉትም በድንጋዩ ላይ ያላናባቢ፣ ከዚያ ውጪ ባሉት መጻፊያዎች ላይ አናባቢን አካትቶ መጻፍ የዘመኑ ስልት ሊሆን ይችላል፡፡

የፊደል ቅደም ተከተል በተመለከተም ዶ/ር ግርማ ሲገልጹ፣ የ..ሀለሐመ.. ተርታ አዲስ መጥ ሳይሆን ጥንታዊ እንደሆነ፣ የ"አበገደ" ተራም ከሃይማኖታዊ ትምህርት ጋር ተያይዞ የመጣ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥልጣኔ መነሻ ላይ ያሉትን መላምቶችና ግኝቶችን የመረመረው መጽሐፍ መታተሙ ለተጨማሪ ጥናትና ውይይትም በር ከፋች ይሆናል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎችንና ኮሌጆቻችን እስካሁን እየተሰጡ ያሉት መረጃዎች የቅርብ ግኝቶችን ለማካተት መትጋትና የማስተማሪያ መጻሕፍቱን መከለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ዶ/ር ግርማ አጽንዖት የሰጡበት ዐቢይ ነጥብ አለ፡፡ "ዕውቀት ቋሚ አይደለም፡፡ በተለይ በማኅበራዊ ሳይንስ ያሉ ነገሮች እየተለወጡ፣ እየዳበሩ የሚሄዱ በመሆናቸው በተለይ በምርምርና በማስተማር ላይ ያሉ መምህራን ትኩረት ሊሰጡበት ይገባል፡፡ የቆየውና ተዛብቶ ሲሰራም የኖረውን መረጃ ከአዳዲስ መረጃዎች ጋር ለኅብረተሰቡ ማስተዋወቅ አስፈላጊ ነው፡፡"

User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

ንቦች(በታታሪነት ንቦችም ከጉንዳን የሚተናነሱ አይደሉም)

Unread post by girreda » 19 Dec 2009 10:58

ንቦች(በታታሪነት ንቦችም ከጉንዳን የሚተናነሱ አይደሉም)

በታታሪነት ንቦችም ከጉንዳን የሚተናነሱ አይደሉም፡፡ ግማሽ ኪሎ ግራም ማር ለመሥራት አንዲት ንብ ሁለት ሚሊዮን አበባዎች ላይ አርፋ መቅሰም አለባት፡፡ በንቦች ሕይወት ውስጥ ሌላም አስገራሚ ነገር አለ፡፡ ንግሥቲቱ ማለትም አውራዋ ንብ፣ ጉልበቷ በሚደክምበት ጊዜ ዙፋኗን ለትውልድ ለማስረከብ እንቁላል መጣል ትጀምራለች፡፡ አያሌ የንግሥቲቱ እጮች ቢፈለፈሉም፣ አልጋውን የምትወርሰው በመጀመሪያ የምትበረው አንዷ ንብ ነች፡፡ ይህችም አልጋ ወራሽ ንብ ሕይወት እንደዘራች በቅድሚያ የምትወስደው እርምጃ ያልተፈለፈሉትን የንብ ልዕልቶችን እያደነች መግደል ነው፡፡ በመጨረሻም ብቸኛዋ ነጋሢ መሆኗን ስታረጋግጥ፣ የአመራር ሥልጣኑን "እፎይ"" ብላ ትጨብጣለች፡፡

(ሻለቃ አባይነህ አበራ፣ ጭላሃ ወግ (ትርጉም"፣ 1981)

User avatar
girreda
Runner
Runner
Posts: 55
Joined: 01 Oct 2009 12:45
Location: Adama University
Contact:

ከ67 አመታት በኋላ የተገኘው የአልማዝ ቀለበት

Unread post by girreda » 19 Dec 2009 11:00

ከ67 አመታት በኋላ የተገኘው የአልማዝ ቀለበት

እ.ኤ.አ በ1941 የጋብቻ በዓላቸውን ለማክበር አንድ ወር ያህል ሲቀራቸው ነበር በሚስ ቫዮሌት ቡዝ እና በሚ/ርፊያንሴ ሳሙኤል መካከል መጠነኛ አለመግባባት የተፈጠረው፡፡

ዘ ሰን እንደዘገበው ሚስ ቫዮሌት ሳሙኤል በንዴት የአልማዝ ቀለበቱን ሲወረውሩት የገባበት ጠፋ፡፡ እጮኛሞቹም ሌላ ቀለበት ለመግዛት ተገደዱ፡፡
ከ67 ዓመታት በኋላ የማዕድን ፈታሽ የሆነው የልጅ ልጃቸው የአልማዝ ቀለበቱን ምንም ሳይሆን አግኝቶታል፡፡

ሚስ ቫዮሌት ቀለበቱን በደስታ በጣታቸው በማጥለቅ “አስገራሚና ከ15 ዓመታት በፊት የሞተውን ባለቤቴን ትዝታ የሚቀሰቅስ” ብለውታል፡፡ የ88 ዓመቷ ሚስ ቫዮሌት “ይህ ቀለበት ለኔ አለም ማለት ነው፡፡ ብዙ አስደሳች ጊዜያትን ያስታውሰኛል፡፡ እነሱን ማየት አላቆምም” ብለዋል፡፡

“ለጋብቻቸው ያሰቡትን የአልማዝ ቀለበት ከጠፋ ከ67 ዓመታት በኋላ ቆፍሬ አውጥቼ ለአያቴ ስሰጣት ፊቷ ላይ ያየሁትን ደስታ አልረሳውም፡፡ በጣም የሚያስደስት ነበር” በማለት የሚስ ቫዮሌት የልጅ ልጅ ሚ/ር ሊንግተን ቦየስ ተናግሯል፡፡

Post Reply

Return to “Ethio Love ...ኢትዮ ፍቅር”