የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
አንፈራራ
Runner
Runner
Posts: 50
Joined: 03 Jan 2012 12:51
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አንፈራራ » 09 Aug 2013 10:00

ቡና እንጠጣ!!
Attachments
Durra gujii Buuna Qaltu.jpg
Durra gujii Buuna Qaltu.jpg (29.39 KiB) Viewed 8461 times

Bale-Suk
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 11
Joined: 28 Mar 2013 12:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Bale-Suk » 12 Aug 2013 00:44

እንዴት ታምራለች
.........ጉጂቱ
ቡና ቀዳጂቱ
ያገሬ ሊጅ የጀምጀሚቱ
ሰላምታዬ ይድረስሽ ቆንጂቱ
አካል ደማሚቱ
ፐ ፐ ፐ
ገጥሜ ሞቻለሁ
አይደል

Bale-Suk
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 11
Joined: 28 Mar 2013 12:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Bale-Suk » 14 Aug 2013 03:20

ሰላም ያገር ልጆች :: ዛሬ መቸም ምን ይዞ መጣብን እንደምትሉ እርግጠኛ ነኝ ...
አንድ ጓደኛዬ ይህችን ግጥም ፌስ ቡክ ላይ አስነብቦኝ ስላስደመመኝ ....ልካፈላቹ ነው የመታሁት
እንደገለፀልኝ ከሆነ ... ፀሀፊው እስካሁን አልታወቀም .... የምታውቁት ካላቹ
እጅህ ይባረክ በሉልኝ ባካቹ
በስነፅሁፍ አይን እንጂ በሀይማኖት አይን እናዳታነቡት አደራ እላቹዋለሁ

እንዲህ ይነበባል[table][tr][td]
Quote:[/td][/tr][tr][td]

ለእግዜር የተላከ ደብዳቤ
(ስሙ ለጊዜው ካልታወቀ ገጣሚ )

እንደምነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው ........?

እኛማ .....
ለእልፍ አላፍ አለቃ
ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይህዝብ
መድረክ ላይ ለፍፈን
ፆለት ቤታችንን
እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ
ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ ...........

አይንህን ካየነው
ሁለት ዘመን
እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ
እየኮሰመነ
መቅረትህ ገዘፈ ....

እንደውም እንደውም .....
‹‹በእመጣለሁ ተስፋ
ሁለት ዘመን
ቀጥሮን ከጠፋ
በቀጠሮው ሰአት
መምጣት ከተሳነው
እግዜር አበሻ ነው ››
እያሉ ያሙሃል

እኔ ምን አውቃለሁ ....
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ .....
ሰባኪው እግር ስር
በደስታ እምቀመጥ
እግዚ ...በሉ ሲባል ....
እንባየን የማፈስ
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ .....
በሳቅ ልቤ እሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ

እኔ ምን አውቃለሁ ......
ግን አንተ ደህና ነህ .......?
ከምር እንደሚያሙት
ምፅአት ቀረ እንዴ ?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ
አትከፋም አንዳንዴ ..... !

ከሆነስ ሆነና
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
አብረሃም ሰላም ነው ...
እዛስ ቤት ገነባ
ዛሬም በድንኳን ነው ?

እኛማ ይሄውልህ .....
በቤት ኪራይ ችንካር
እየተሰቀልን ‹‹ኤሎሄ›› እንላለን
ጎጆ እንድጥልልን .......

ወደላይ ገነባን
ወደጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ
ወደጎንም ከጎን
እንደጉድ ተገፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት
ጭራሹኑ ጠፋን !!

አባታችን ሙሴ
እነዴት ነው ለክብሩ
ውቂያኖስ መክፈያው
ደህናናት ብትሩ ?

እኛማ ይሄውልህ ....
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ
የተስፋዋን ምድር
አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን
የትም አሳ ላሰን
ብትሩን ያውሰን .......

እናልህ እግዜር ሆይ ....
ከተስፋዋ ምድር
ወደሌላ ተስፋ
አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን
መመለሻ መንገድ
መቆሚያ ቦታ አጥተን ......!

ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን ....
‹‹የመሄድ ዘመን ነው
ባህር የመሻገር
ዱላህን ላክልን ››
ብሎሃል በልልን .....

ሰማይ ቤት እንዴት ነው ....
ዳዊትስ ደህና ነው .....
ዛሬም ይዘምራል ...
ዛሬም ይፎክራል ?

ሰላም ነው ጠጠሩ ....
ሰላም ናት ወንጭፉ
እዛስ አቅል ገዛ
ጎሊያድ ተራራው
ጎሊያድ ግዙፉ ......
እልፍ አላፍ ጎሊያድ
ከቦን ሲደነፋ
ወንጭፉን ጠቅልሎ
ምነው ዳዊት ጠፋ ?
ብሎሃል በልልኝ !!

ለረከሰ ጠጠር
ለሞላ ወርዋሪ
‹‹ወንጭፍህን ስጠው
ለዚህ ታሪክ አውሪ››
ብለህ እዘዝልን .........!!

እንዴት ነህ ጌታ ሆይ ....
ሰማይ ቤት እንዴት ነው ....
የሙሴ አልጋ ወራሽ
እያሱ ሰላም ነው .....
ያቆማትን ፀሃይ
ግቢ ቢላት ምነው ...
ያው እንደምታውቀው
አስራ ሶስት ወራት ነው
ፀሃይ የምንሞቀው ......

ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
የመጣው ወር ሀሉ
ፀሃይ እያዘለ
የተሸመው ሁሉ
<ፀሃይ ነኝ >እያለ


የአስራ ሶስት ወር
የግዜር ፀሃይ
የአስራ ሶስት ወር
የሰው ጀምበር
ባቃጠላት ምድጃ አገር
ምን ታምር ሊኖር ይችላል
ፀሃይ ሁኖ እንደመፈጠር ........

ኧረ እግዜር በናትህ ....
ኧረ እግዜር በናትህ ...
በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ
ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን
ወይ ዝናብ ሁነህ
ሙቀት ገደለና .......!

እናል .....
እግዜር ሆይ
ማጣፊያው አጥሮናል
ስም ያለው ሞኝ ነው
ሁሉም ይጠራናል ....

ጳውሎስ ሲሉን ...አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን ...ወይየ
ይሁዳ ሲሉንም
አቤት እንላለን

ስማችንን ሸጠን ...
ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን

ተወው የኛን ነገር ...
ሰማይ ቤት እንዴት ነው ....
ሂዋንስ ደህና ናት .....?
ያው የልጅ ልጆቿ
በእግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርምህ
ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም
ባይኑ ያገምጡታል

ሰይጣንም ደህና ነው
ኑሮ ተስማምቶታል ........
ሰውን ለማሳሳት
ላይ ታች ማለት ትቷል
ሳይጠራው የሚጎርፍ
ህዝብ በዝቶለታል ...... !!

ኧረ እግዜር በናትህ
በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ
ባቀፉህ እጆቿ

ወይ ዝናብ ላክልን
ወይ ዝናብ ሁነህ
ሙቀት ገደለና !!
End of Quote[/td][/tr][/table]

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 15 Aug 2013 17:51

ገና ግጥምህን ሳየው የትና እንዴት እንዳነበብኩት አስታወስኩ::
ምርጥ ምርጥ መጣጥፎችና ኢትዮጵያዊ የስነጽሁፍ ቅኝቶችን ለማየትና ለመዝናናት ጎራ የምልበት ስፍራ ትዝ አለኝ::
ግጥሙ በጣም አስደናቂና ዘንድሮን ወይንም ያለንበትን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ በመስታወት የሚያሳይ ሲሆን የስነጽሁፍ ዘይቤው ግን ከዚህ ህብረተሰብ ማለትም ከኢትዮጵያዊነት ጋር ለመራመድ ቸኩሏል የሚል እምነት አለኝ::
ጥቂትም ቢሆን ንቃትን አልያም ስነጽሁፋዊ ለዛ ነው ብሎ የሚያምን አንባቢን ማግኘት የሚያሻ ይመስለኛል ::
ለምሳሌ ደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር ከእረፍቱ ቀደም ብሎ ከጻፋቸው ውስጥ አንዱ ዘመኑን የቀደመ ነበር::
በአለማችን የነበሩ አንዳንድ ደራሲዎች ሰዓሊዎችና ፈላስፎች ስራዎቻቸውን ለአለም ባቀረቡ ጊዜ ወይንም ባቀረቡ ዘመን ተንቀውና ተስቆባቸው የነበሩ ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ ስራዎቻቸው የወቅቱን ማህበረሰባዊ ንቃት እጅግ ቀድሞ እንደነበር የሚነገርላቸውና እነሱ ካለፉም በኋላ በስራዎቻቸው ዓለምን ያስደደነቁ ሰዎች እንደነበሩ የምናውቀው ነው::
የሆነው ሆኖ እነ ደራሲ ስብሃትን እና የዚህን ግጥም ጸሃፊ ከገለጽኩት ሰዎች ጋር ለመመደብ ፈልጌ ሳይሆን ጽሁፎቻቸው ውሸት የሌለበት ነገር ግን ጊዜውን ያልጠበቀ አልያም ቀደም ያለ ነው ብዬ ሰለማስብ ነው::
እግረመንገዴንም እዚያው ያንተ ግጥም ካለችበት መንደር ያገኘኋትን እና ሸፍኘ ቁጭ ያደረኳትን ሞገስ ጋሻው የጻፋትን አንዲት የኔንም ቀልብ የሳበችች ግጥም ላስነብባችሁና ወደ ሰላምታዬ ልመለስ ::
አባትሽ ጀነራል ወንድምሽ ሻለቃ
እናትሽም ዳኛ እህትሽ ጠበቃ
ታዲያ እንዴት ብዬ ልጥላሽ ለደቂቃ
በዚህ ሁሉ ጉልበት ተከበሽ እያየው
እኔስ ምን አቅብጦኝ አንቺን አጠላለው
ደግሜ ደግሜ ውዴ እወድሻለው
አዎ እወድሻለው
"እልፍ አህላፍ ለሊት
ሚሊዮን መሠለኝ
እኔ አንቺን ስወድሽ
ስወድሽ ስወድሽ
ስወድሽ ስወድሽ"
የሚለውን ግጥም
ሁሌ ማነብልሽ
ለምን እንደሆነ
አድምጪኝ ልንገርሽ
ውዴ.........
አንቺና መንግስቴን
እንዲህ ምወዳቹ
ለሞት እንዳትሰጡኝ ስለምፈራቹ .............................end
የምወድህ ወንድሜ እንደምን አለህ ?
እነዚያ ደሳስ የሚሉ ጽሁፎችን የሚያቀልሙ ጣቶችህ ከመጻፊያው /ኪቦርድ/ ጋር ፍቅራቸው መቀነሳቸው ስለምን ይሆን ?
ዳሩ ዘንድሮ ፍቅርና ብር ወረተኞች ሆነዋል ! ስለዚህ ማንንም አልወቅስም ብቻ ግን ምን መሰለህ የአዶላ ልጆች የራስብሩ ወልደገብርኤል ተማሪዎች የወዩ ልጆች የአጂፕ ልጆች የኩሚና ልጆች የአደቆርሳ ልጆች የአራዳ ልጆች የካምቦ ልጆች የጨፌ ልጆች የቲቤ ልጆች የገበያ ክፍል ልጆች የፈረንጅ ውሃ ልጆች የዋደራ ልጆች የቦሬ ልጆች የይርባ ሙዳ ልጆች የመሌካ ልጆች የኦዶ ልጆች የሻኪሶ ልጆች ወዘተርፈ ...............ፍቅራቸው የሚያልቅ ስለማይመስለኝ ነው::
ድሮ ድሮ ትዝ ይልሃል ? ነጌሌ ቦረናና ጀምጀም ሲጫወቱ ባክህ እንደፈለክ እኔ ምናገባኝ ዝም ብዬኮነው የምለፈለፈው እንደውም አንተ ተሻለኛለህ::
ከፈለክ አትጥፋ ካልፈለክ ደሞ እልም ብለህ ጥፋ ........ ብቻ ደህና ሁን !
አንፈራራችን የአቦል ግብዣህ ደርሶናል ላንተም ምስጋናችን ይድረስህ
ስለ ዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በተነሳ ቁጥር አንጀት የሚያርሱና አንጀት የሚያሳርሩ ጉዳዮች ለኛ አሮጌዎች ናቸው ::
ኢትዮጵያ በስፖርት የተረገመች ያህል አንድም ቀን በፌዴሬሽኖች አሰራር ሳንደሰት በጥቂት አትሌቶች ትከሻ ብቻ የአለም መድረክ ላይ መገኘት ተስፋ የማይታይበት ጩኸት እየሆነ መጥቷል::
የአትሌቲክስ ውድድሩ መጠን ሰፋ ይበል
ብዙ ጠንካራ ጠንካራ ወጣቶች ይመልመሉና ለብሄራዊ ቡድን ይሰልጥኑ
ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት እንዲቻል በትምህርት ቤቶች የስፖርት ዘርፎች በመደበኛነት ይሰራባቸው
የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ይከለሉ......... ወዘተ የዛሬ ሃያ ዓመት ጀምሮ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ናቸው::
ሲስፋፋ የሚታየው የአሰልጣኞች ኪስና የሃላፊዎች ኑሮ ብቻ እንጂ ስፖርቱ አይደለም::
ኑሮውን ለማሸነፍ ራሱ ከሚደክም አትሌት በቀር በኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን ድጋፍ የትም የደረሰ አትሌት የለም::
እንዲህም ሆኖ ደሞ በ ሴቶች ማራቶን የሆነውን እንዳያችሁት የሚያሳዝን ጉዳይ ነው በውነት እኔ ከማዘን በስተቀር ምንም ማለት አልችልም::
ጥሩነሽ ዲባባ እና መሃመድ አማን እግዚአብሄር ይስጣችሁ !
ቸር ያቆየን ወዳጃችሁ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

Bale-Suk
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 11
Joined: 28 Mar 2013 12:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Bale-Suk » 23 Aug 2013 01:03

አደቆርሳዬ
/quote "ገና ግጥምህን ሳየው የትና እንዴት እንዳነበብኩት አስታወስኩ::
ምርጥ ምርጥ መጣጥፎችና ኢትዮጵያዊ የስነጽሁፍ ቅኝቶችን ለማየትና ለመዝናናት ጎራ የምልበት ስፍራ ትዝ አለኝ
::"/quote
እንዴ እንዴ ግጥሙን ማን እንደጥሳፈው ታውቃለህ ምማለት ነው እኮ... ዋው ታድለህ በናትህ
እኔ እንዳላደንቀው ማን እንደጥሳፈው አሁንም አላውቅም ከምር
አቤት ስንትና ስንት ነገር ላወራ መጥቼ
እምቢ አለኝ እኮ
ምን ሆንኩጝን ነው ሚለው ባካቹ ይሄ የሃሳብ ምንጭ
ህምምምምምም
ለማንኛውም
ስትጠፉ አያምርባቹም
አደቆርሳ ወንድሜ... በፈጠረህ የጥሰሃፊውን ስም.. ወይም መጥሳፍ ጥስፎ ከሆነም.... በጓሮ ሹክ በለኝ
ውዴ......... አደቆርሳዬ
አንተና መንግስቴን
እንዲህ ምወዳቹ
ለሞት እንዳትሰጡኝ ስለምፈራቹ .............................
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ብዬ አንተው ባስነበብከን ግሩም ግጥምህ ልሰናበትህ
ቸር ቆዩን
አቤት እዚህ ቤት በአማርኛ መጥሳፍ እንደሚያስቸግርርርርርርርርርርርርርር

አደቆርሳ
Jogger
Jogger
Posts: 45
Joined: 13 Jan 2012 04:13
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by አደቆርሳ » 23 Aug 2013 11:57

የዚህ ግጥም ጸሃፊ ራሱን ገልጾ ይናገራል ወይንም ያሳውቃል ብለህ ነው ? እኔ አይመስለኝም ::
የሆነው ሆኖ አቅራቢው አሌክስ አብርሃም ግድግዳ ላይ አገኘሁት ብሎ ነው የቋጨው ::
ግጥሙን ያነበብኩት ሻይ ቡና ጎራ ብዬ ነው አንተም ወደ ሻይቡና ዌብ ሳይት ጎራ በልና በእልፍ ግጥሞችና ደሳስ በሚሉ መነባንቦችን ተዝናና::
የተለያዩ ጽሁፎችን ማንበብ በጣም ነው የምወደው በፊት በፊት አንድ መጽሄት ወይንም ጋዜጣ ሳነብ የጀርባው ማስታወቂያ ሳይቀረኝ ነበር የማነበው:: ምናልባት ይሄ ከልጅነታችን መምህራኖቻችን ካሳደሩብን ስሜት ይሆናል ብዬ ገምታለሁ::
ግጥምና ስድ ንባብ እንዴት እንደሆነ ማለትም ልዩነታቸውን እና አንድነታቸውን አልያም የግጥምና የስድ ንባብ አጻጻፍ ዘዴዎችን የተማርነው የጁኒየር ተማሪዎች ሆነን ነው:
በሃገራችን ማንም ሰው እንደፈለገው ሳይሆን መንገድ እንደተመቸው የሚኖርና የሚማር ስለሆነ ብዙዎቻችን ከፍላጎት መስመራችን እንወጣለን::
ከዚህም የተነሳ ብዙ ብዙ የሞያ ልጆች ከከፍላጎታቸው ውጭ የሆነ ትምህርት በመማር ህይወታቸውን ያለደስታ ለመኖር ተገደዋል ይገደዳሉም ተገደናልምም::
በግጥምና በስነጽሁፍ ልዩ ችሎታ የነበራቸውን ልጆች አስታውሳለሁ ከአንዱ በስተቀር ማንም በፍላጎቱ ውስጥ የለም::
መምህራኖቻችን ጋሼ ገረመው ነጋሽ ከዚያም መሰረት ወርቁ ቀጥሎም ጋሼ ዓለሙ ጥሩ የሰዋሰው እና የስነጽሁፍ ችሎታ እንድናዳብር በደንብ አስተምረውናል ::
በትምህርት ቤታችንም ውስጥ የስነጽሁፍ ክለብ የፎቶግራፍ ክለብ የስፖርት ክለብ ወዘተ የነበረ ሲሆን እያንዳንዱ ክለብም ብዙ አባላቶች ነበሩት::
አብረን ከነበርናቸውና ከማስታውሳቸው ውስጥ
በግጥም ጽሁፍ ችሎታ:- ጌታቸው ተስፋዬ :ሙሉጌታ ገለታ: ዮሴፍ ጸጋዬ: ታደለ በቀለ (ፍልፈል)
...... በስነጽሁፍ ደሞ መስፍን ሚደቅሳ: (የሻኪሶ ልጅ) ሙሉጌታ እንደሻው: ኃይሉ ብሩ... በደንብ የማስታውሳቸው ናቸው::
በተመሳሳይ ወቅት አብረን ባንማርም እነ ወልደ እስራዔል ተስፋዬ ታምሩ መርጊያ ጸጋዬ መርጊያ ተስፋዬ መርሻ ገነት ተሰማ ወዘተ በግጥምና ሥነጽሁፍ ችሎታቸው የታደሉ አዋቂዎች ነበሩ::
ይህም ሆኖ ግን የተዋጣላቸው ደራሲያን ከመሃከላችን መውጣታቸው ኩራታችን መሆናቸውን ሳልዘነጋ ወርቃፈራሁ ከበደን እና ተስፋዬ ድረሴን በመጥቀስና በማመስገን እሰናበትሃለሁ::
ሌላው እዚህ ቤት አማርኛ መጻፍ ይቸግራል ማለትህ ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም ይባላልና ከፈለክ እንኳንስ ላንተ ለኔም ፍራንኳ ትኑረኝ እንጂ መጻፍ አይቸግረኝም::
በል ደህና ሁን የምወድህ ባለሱቅ ወዳጅህ አደቆርሳ ዘሃገረ አዶላ

Jigsa
Starter
Starter
Posts: 21
Joined: 13 Feb 2013 01:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Jigsa » 29 Aug 2013 08:14

14.00
ቡሄ በመጣ ቁጥር ያንን ሽማግሌ ለምን እንድምናበሳጫቸው ዛሬም አላውቅም!
ተክሌ ወለላው (የአባታቸውን ስም ዛሬም አላውቅም እሳቸው ማታ ሞቅ ብሎአቸው ሲመጡ ተክሌ ወለላው ዘራፍ እያሉ ስለሚፎክሩ ሰዉ ሁሉ ተክሌ ወለላው ብሎ ነው የሚጠራቸው) ማታ ማታ መጠጣቸውን ወስደው በኛ በር ላይ ሲያልፉ ዋን ቱ ትሪ ኢ ኢንግሊሽ …. ዘራፍ ተክሌ ወለላው ማለታቸው አይቀርም፡፡
ታዲያ ቡሔ ሊመጣ 1 ሳምንት አካባቢ ሲቀረው ሁላችንም ስራ ተከፋፍለን እንሄዳለን. ባላ የሚቆርጥ፣ ማገር የሚቆርጥ ርብራብ የሚቆርጥ፤ እንዲሁም ለጣራ ክዳን ሳር የሚያጭድ፡፡ ሁሉም በየፊናው ይሰማራል፡፡ እንጨቱ ሳሩ ተሰብስቦ በተመረጠው ቦታ የጎጆው ስራ ይጀመራል ፡፡ ከዚያም ከቡሄ ዋዜማ ጀምሮ አዳራችን በሰራናት ጎጆ ውስጥ ይሆናል፡፡
ይጨፈራል ፡፡ ይዘፈናል፡፡ ታዲያ እኩል ሌሊት እንነሳና ዘመቻ ወጥተን በጨረቃ ሄደን የቻልነውን ያህል በቆሎ እሸት ዘርፈን እንመለሳለን፡፡ ከዚያ እስኪያልቅ ድረስ ይበላል፡፡ ሆዳችንን ሲያመን እንተወዋለን፡፡ የሚገርም ግን በየአመቱ ዝርፊያው የሚካሄደው ግን ከዚህ ምስኪኑ ሽማግሌ ማሳ ላይ ነው፡፡
አቤቱ ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ! ኪርያላይሶን 41 ጊዜ….

Jigsa
Starter
Starter
Posts: 21
Joined: 13 Feb 2013 01:27
Contact:

Re: የጀምጀም ልጆች መገናኛ

Unread post by Jigsa » 13 Sep 2013 07:24

14.00
ይድረስ በጣም ላናደዳችሁኝ ለዚህ ቤት አባላት በሙሉ!


በዚህ ቤታችን ገፅ ላይ የመጨረሻው ጽሁፍ የወጣው ኦገስት 29 ነው፡፡ እሱም የኔ ብጫቂ ማስታወሻ ነው፡፡ ከዚያ ወዲህ አንድም ሰው ምንም አላለም፡፡ ክሁሉ በጣም የሚገርመው አንድ ሰው እንኳን እዚህ ቤት ገብቶ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳቸእሁ አይልም?!
14.00

Post Reply

Return to “የጀምጀም ልጆች መገናኛ”