ከእያንዳንዱ ቅዳሜ ጀርባ........

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
selam sew
Leader
Leader
Posts: 620
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ከእያንዳንዱ ቅዳሜ ጀርባ........

Unread post by selam sew » 23 Jul 2016 19:38

ከእያንዳንዱ ቅዳሜ ጀርባ........

========================
~> አንዲት ጎረምሳ ወንድሞቿን እንድታሳድግ የአርባ ቀን ዕድሏ የፈረደባት
ኢትዮጵያዊት እህት አቧራ የጠጡ ጅንስ ሱሪዎችን ስትፈትግ ትውላለች
~> ካልዲስ በረንዳ ላይ ጋዜጣ የሚያነብ መስሎ በቄንጥ ማስቲካውን እያኘከ ፣
በሸበቶው አፍሮ ጥቁር ቀለም ተቀብቶ ከሰል ተሸካሚ የመሰለ ፣ ተማሪ ሴቶችን
ገንዘቡን እንቁልልጭ እያለ የሚዳራ ሹገር ዳዲ አለ
~> አንድ ለሱሱ ሳንቲም የጠረረበት ጎረምሳ ከቤት ዕቃ ሰርቆ ለቁራሌ ይሸጣል
~> አንዲት አለሟ ብርጭቆ ውስጥ የሆነባት ወጣት ማታ የሚጋብዟትን ወንዶች
ስልክ በጉጉት ትጠባበቃለች
~> አንድ ፍቅረኛውን የቀጠረ ወንድ ፔንሲዮኖችን ሲያማርጥ ይውላል
~> አንድ ደመወዝ የተቀበለ አባት ግማሽ ኪሎ ስጋ ገዝቶ ወደ ቤቱ ይሄዳል
~> አንዲት ምስኪን ወላድ የሆነች ሴት እንጀራ ለመጋገር በቅጠል ጭስ
ትጨናበሳለች
~> የደላቸው ፍቅረኛሞች ላንጋኖ ና ሶደሬ ላይ አስረሽው ምቻቸውን ያደሩታል
~> አንድ ሰኞ ይሁን ቅዳሜ ያን ያህል ለውጡ የማይታያት በስደት ሆና
ሳያልፋባት እንዲያልፍላት እየታገለች ያለች ምስኪን ቤተሰብ አስተዳዳሪ ሴት
አለች። በላይፏ # ላኪ (ዕድለኛ) ሳትሆን ላኪ ብቻ እየተባለች የምትጨቀጨቅ
~> ፖስት ፒል ለመዋጥ የተዘጋጀች አንዲት ሴት አለች
~> የሆኑ ጓደኛሞች ሰብሰብ ብለው ወደ አዋሳ ሄደው ለእርጅና ጊዜያቸው
የሚሆን ትዝታ ለማስቀመጥ ሲኦቭሩ ያድራሉ
~> ኮንዶም ነጋዴዎች ና ጫት ሻጮች የሳምንቱን ሽቀላቸውን በአንድ ቅዳሜ ቀን
ያካክሱታል
~> ቢያንስ ቢያንስ አንዲት ሴት ድንግልናዋን ታጣለች
~> ትምህርት ባለመኖሩ ደስ የሚላቸው ብዙ ተማሪዎች አሉ
~> ባላቸው ሰክሮ የሚደበድባቸው ጥቂት ሚስቶችም አይጠፉም
~> የሰፈሩ ጎረምሳ ወንዶች ለሊት 11፡00 ተነስተው ኳስ ጨዋታውን ያደሩታል
~> እያንዳንዷ ሴተኛ አዳሪ "ዛሬ ሸቀል ሸቀል አድርጌ የቤት ኪራዬን ወይም
የልጄን የትምህርት ቤት ክፍያ እከፍላለሁ" ብላ ተስፋ ታደርጋለች
~> ከሌላው ቀን በባሰ ሁኔታ አብዛኛዎቹ ሰፈሮች በሺሻ ጭስ ይታጠናሉ
~> የሆኑ ዘመናዊ እናትና አባቶች ልጆቻቸውን ቦራና ኤድናሞል ሲያዝናኑ የሆኑ
ዕድል ፊቷን ያዞረችባቸው ወላጆች ልጆቻቸው ጉሊት እንዲሸቅሉ በጠራራ ፀሀይ
ያንቃቁዋቸዋል
~> ኳስ ከሌለ መደበሪያ የሌለ የሚመስላቸው ዲኤስቲቪ ቤቶችን ምሽግ ያደረጉ
እልፍ ወጣቶች እንዳሉ ሁሉ ደምና ላባቸው እስኪቀላቀል ፣ የወገባቸው ውሀ ልክ
እስኪዛባ ድረስ ለማይሞላ ኑሮ የሚደክሙ ወጣቶችም አሉ
~> የሆነ አንድ ለፍዳዳ ሰካራም አለ
~> የሆነች መስከር እርድና የሚመስላት ፒያሳ መሀል አስፋልት ላይ ሽንቷን
የምትሸና ብሽቅ ሴት አለች
~> አንድ የተባረከ ማጅራት መቺ አለ
~> አፋቸውን በነጠላ የሸፈኑ ነጭ በነጭ የለበሱ ቆራቢ ህፃናትና አዛውንቶች
አሉ
~> መሀል ዶሮ ማነቂያ ጫት ቤት ውስጥ በምርቃና የተፃፈ አንድ ውብ ግጥም
አለ
~> ወሎ ሰፈር አካባቢ ወጣት ወንዶችን ለመጥበስ መኪናዋን አስፋልቱ ዳር ላይ
ቀስ ብላ የምትነዳ የአሮጊት ቀላል የሆነች አንድ ሹገር ማሚ አለች
~> አንድ መሄጃ ያጣ ግራ የገባው ይሄን ፁሁፍ የሚያነብ ሰው አለ
~> አንድ ካለመፖሰት መፖሰት ይሻላል ብሎ ይሄንን ፁሁፍ የሚፅፍ ፀሀፊም አለ

ፏ ያለች ቅዳሜ ትሁንላችሁ!!!
© ወንድማገኝ ለማ

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”