ተረት ጨ
• ጨረቃ ሲጠፋ ኮከብ አባወራ ይሆናል• ጨዋነሽ ቢሏት ሳቁ ገደላት
• ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ አለበለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይወረውሩሀል
• ጨጓራ ለመፍጨት አንጀት ለመጎተት በለው ዋተት ዋተት
• ጫማ የለኝም ብለህ አትዘን ካልሲ የሌለው አለና
• ጫማ የለኝም ብለህ አትዘን እግር የሌለው አለና
• ጭድ ይዞ እሳት ሳል ይዞ ስርቆት
• ጭድ ይዞ ወዘት ሳል ይዞ ስርቆት
• ጭለማ ቢመጣ አትፍራ ይነጋልና
ተረት ፈ
• ፈላ ገነፈለ ተሞላ ጎደለ• ፈረሰኛ ሲሮጥ እግረኛን ምን አቆመው
• ፈረሰኛ ሲሸሽ እግረኛን ምን አመጣው
• ፈረሰኛ የወሰደውን እግረኛ አይመልሰውም
• ፈረሱም ይኸው ሜዳውም ይኸው
• ፈረስ ሲያጠብቅ ልጓም አይለቀቅ
• ፈረስ በራሪ በቅሎ ሰጋሪ
• ፈረስ ቢያነክስ አህያ ታጉዝ
• ፈረስ ቢጠፋው ኮርቻውን ገልቦ አየ
• ፈረስ አውቃለሁ ስገታ እወድቃለሁ
• ፈረስና ገብስ ያጣላል
• ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም
• ፈረስ ጥሎ ይደነግጣል በቅሎ ጥሎ ይረግጣል
• ፈረስ ጥሎ ይደነግጣል አህያ ጥሎ ይረግጣል
• ፈረንጆች እንደመርፌ ይገቡ እንደዋርካ ይሰፉ
• ፈሩ ፈሩ ማጀት አሩ
• ፈሩ ፈሩ ማጀት አደሩ
• ፈሪ ለናቱ
• ፈሪ ለናቱ ይገባል
• ፈሪ ለናቱ ጀግና ለጀግንነቱ
• ፈሪ በገዛ ጠቡ ገላጋይ ይሆናል
• ፈሪ ቢሸፍት እስከ ጓሮ
• ፈሪ እንዳይሉኝ አንድ ገደልሁ ጀግናም እንዳይሉኝ አልደገምሁ
• ፈሪ ከውሀ ውስጥ ያልበዋል
• ፈሪ ካልጋ ላይ ይወድቃል
• ፈሪ ካልጋ ላይ ወድቆ ይሞታል
• ፈሪን ውሀ ውስጥ ያልበዋል
• ፈሪ ውሀ ውስጥ ሆኖ ያልበዋል
• ፈሪ ውሀ ውስጥ ያልበዋል
• ፈሪ የሚያባርረው ሳይኖር ይሸሻል
• ፈሪ የናቱ ልጅ ነው
• ፈሪ ፈራና እጉድባ ቢኛ ጆሮውን በላው ያይጥ ቀበኛ
• ፈሪ ፈራና እጉድባ ቢተኛ ጆሮውን በላው ያይጥ ቀበኛ
• ፈርተው ድንጋይ ሲጥሉ ጅብ ወጣ ከዱሩ
• ፈርተው ድንጋይ ቢጥሉ ጅብ ወጣ ከዱሩ
• ፈርተው ድንጋይ ቢወረውሩ ጅብ ወጣ ከዱሩ
• ፈሷን ፈስታ ቂጧን ጨበጠች
• ፈስ በወረንጦ እየተለቀመ ነው
• ፈስቶ ቂጥን መያዝ
• ፈስ ያለበት ቂጥ ዝላይ አይችልም
• ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም
• ፈትል ሲረዳዳ አንበሳ ያስራል
• ፈትል ሲረዳዳ አንበሳ ያስቀራል
• ፈክሮ መሽሽ ታሪክ ያበላሻል
• ፈዛዛ እያንቀላፋ ይገባል ፈፋ
• ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ እስቲበርድ ይራበኝ
• ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ እስኪበርድ ይራበኝ
• ፈገግታ የልብ አለኝታ
• ፈጣሪን የሚያህል ጌታ ርስትን ያህል ቦታ
• ፈጣሪን የሚያህል ጌታ ገነትን ያህል ቦታ
• ፈጥነው የገመዱት ፈጥኖ ይበጠሳል
• ፈጥኖ መስጠት ኋላ ለመጸጸት
• ፈጥኖ መስጠት ቶሎ ለመጸጸት
• ፈጥኖ መስጠት በኋላ መጸጸት
• ፈጭታ የነበረች ላመልማሎ ኮራች
• ፊት ያሞጠሙጧል ኋላ ያፏጩዋል
• ፍሪክና ጻድቅ አይቀጣጠርም
• ፍሬ በመስጠቱ ባልታወቀ ሾላ የወፎች ዝማሬ ቀደመ አሉ
• ፍቅር ሲጠና ቆሎ ያጓርሳል
• ፍቅርና ጉርሻ ካላስጨነቀ አያምርም
• ፍቅር ካለ ዘጠኝ ቂጣ ለባልና ሚስት ይበቃል
• ፍቅር ፍቅር ሲሉ ደሀ ሆነው ቀሩ
• ፍየል ሁለት ወልዳ አንዱ ለመጽሀፍ አንዱ ለወናፍ
• ፍየል ላምስት ዶሮ ለባልና ለሚስት
• ፍየል መንታ ወልዳ አንዱ ለመጽሀፍ አንዱ ለወናፍ
• ፍየል መንታ ትወልድና አንዱ ለወናፍ አንዱ ለመጽሀፍ
• ፍየል ሲሰባ ሾተል ይልሳል
• ፍየል በልታ በበግ አበሰች
• ፍየል በልታ በበግ አሳበበች
• ፍየል ሲቀናጣ እናቱን ይሰራል
• ፍዬል በግርግር እናቱን ይሰራል
• ፍዬል በግርግር እናቱን ይሰር
• ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ
• ፍየል ከቀዘነ ዲያቆን ከዘፈነ
• ፍየል የለኝ ከነብር ምን አጣላኝ
• ፍየልና ቀበሮ ምጥማጥና ዶሮ
• ፍየሏን እንደበግ
• ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ
• ፍዳ ለሀጥአን እሴት ለጻድቃን
• ፍጥም አያናግር የጎርፍ ሙላት አያሻግር
• ፍጥም አፍራሽ ቤተክርስቲያን ተኳሽ
• ፍጥም ያቆማል እርቅ ይጠቀልላል
• ፍጥም ያዋውላል አቧራ ያስላል
• ፎክሮ መሸሽ ታሪክ ያበላሽ