የአሜሪካ ኤምባሲ የዲቪ ሎተሪ ቪዛ አመልካቾች እንዳይጭበረበሩ አስጠነቀቀ 2012 DV lotter

Forum rules
በኢሚግሬሽን ጉዳይ ላይ የሚነሱ ማናቸውንም ጥያቄዎች እና መረጃዎችን ለመወያየት
munaye
Leader
Leader
Posts: 135
Joined: 27 Aug 2009 21:29
Contact:

የአሜሪካ ኤምባሲ የዲቪ ሎተሪ ቪዛ አመልካቾች እንዳይጭበረበሩ አስጠነቀቀ 2012 DV lotter

Unread post by munaye » 04 May 2011 13:01

አዲስ አበባ, የካቲት 24 ቀን 2003 (አዲስ አበባ) - በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የዲቪ ሎተሪ ወይም የዳይቨርስቲ ቪዛ አመልካቾች እንዳይጭበረበሩ አስጠነቀቀ፡፡
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የብዙኃንን ትኩረት ከሚስበው የአሜሪካ የቪዛ ሎተሪ ወይም የዳይቨርስቲ ቪዛ መርኃ ግብር ጋር በተያያዘ በአሁኑ ወቅት በርካታ የማታለያ የኢ-ሜይል መልዕክቶች ኢትዮጵያ ውስጥ እየተዘዋወሩ ነው፡፡
በመሆኑም የዳይቨርስቲ ቪዛ /ዲቪ/ አመልካቾች በእነዚህ የማታለያ የኢ - ሜይል መልዕክቶች እንዳይጭበረበሩ ኤምባሲው በመግለጫው አስጠንቅቋል፡፡
ኤምባሲው ለዲቪ 2012 አሸናፊ አመልካቾች የማሳወቂያ ሒደትን በተመለከተ አመልካቾች የሚከተሉትን እውነታዎች እንዲገነዘቡም አሳስቧል፡፡

Image

ለዲቪ 2012 መርኃ ግብር፣ አሸናፊዎች የማመልከቻቸውን ውጤት ማወቅ የሚችሉት በኤሌክትሮኒክ ዲቪ /ኢ ዲቪ/ ድረ ገፅ ላይ / http:www.dvlottery.state.gov ማመልከቻው የሚገኝበት ሁኔታ /Entry Status Check/ በማየት ብቻ ነው ሲል ጠቁሟል፡፡
የ2012 ዳይቨርስቲ ቪዛ መርኃ ግብር አሸናፊ መሆንዎትን የሚገልጽ ማንኛውም የኢ ሜይል መልዕክት ቢደርስዎት ማጭበርበሪያ መሆኑን ማወቅ እንደሚገባም አመልክቷል፡፡
የአሜሪካ ኤምባሲም ሆነ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢንተርኔት፣ በዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ማስተላለፊያ /ሐዋላ/ ወይም በኢ ሜይል ምንም ዓይነት ክፍያ እንዲከፍሉ በፍፁም አይጠይቁዎትም፡፡
ከዲቪ መርኃ ግብር ጋር በተያያዘ ክፍያ ይፈፅሙ ዘንድ የሚጠይቅ ማንኛውም የኢ ሜይል መልዕክት ቢደርስዎ ለማጭበርበር የታለመ መሆኑን ይወቁ ብሏል፡፡
የዲቪ ውጤት ማሳወቅን የሚመለከት የማጭበርበሪያ ኢ ሜይል ከደረሰዎት፣ እባክዎን መልዕክቱን በኢሜይል አድራሻ fpmaddis@state.gov ይላኩት ሲል ጠይቋል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እነዚህን የማጭበርበሪያ የኢ ሜይል መልዕክቶች ለማስቆም በማለም ከኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪዎች ጋር የሚሠሩ የሥራ ክፍሎችን መድቧል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፣ የዲቪ አመልካቾች ከኤምባሲው የቆንስላ አገልግሎት ክፍል ጋር በኢሜይል አድራሻ consaddis@state.gov መገናኘት ይችላሉ፡፡
አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የማጭበርበር ተግባራትን በፀና ቁርጠኝነት ይዋጋሉ ሲል መግለጫው ጠቅሷል፡፡
የአሜሪካ ኤምባሲ ዶክመንት ሻጮችን ወይም የተጭበረበሩ ዶክመንቶች የሚያዘዋውሩ ሰዎችን የሚያውቅ ማንኛውንም ሰው በኢ ሜይል አድራሻ fpmaddis@state.gov እንዲያሳውቁ ያበረታታል፡፡
Post Reply

Return to “Immigration and Related things...ኢሚግሬሽን እና ተዛማጅ ጉዳዮች”