ሰበር ዜና፡- ለጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱ የክብር ሰርትፍኬት ሊሰጥ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡

User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ሰበር ዜና፡- ለጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱ የክብር ሰርትፍኬት ሊሰጥ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡

Unread post by zeru » 07 Aug 2014 17:01


ሰበር ዜና፡- ለጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱ የክብር ሰርትፍኬት ሊሰጥ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡

የሀገራችን ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ አስተዋፅኦ ላደረጉ ኢትዮጵያውያን የክብር ዶክትሬት ሲያበረክቱ መስማት ወይም ማየት አዲስ አይደለም፡፡ ሰሞኑን ከዙርያጥምጥም
የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሰማው ዜና ግን አስገራሚና አስደናቂ ነው፡፡ የዘ-ሽንኩርት የፌስቡክ ዜና ማሰረጫ ዘጋቢዎ
ች ትምህርት ቤቱ ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ቦታው ድረስ
በመገኘት ማረጋገጥ እንደቻሉት የዙርያጥምጥም የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት የወላጆች ኮሚቴ ለወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ የክብር ሰርትፍኬት ለመስጠት ወስኗል፡፡

የዛሚ 90.7 ኤፍ.ኤም ሬድዮ መስራችና ባለቤት የሆነችው ሚሚ ስብሃቱ በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሙያ ሶስት እርምጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ሰርትፍኬቱ
እንደተበረከተላትም ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ በሀገሪቱ የተከሰተው የህትመት ወረቀት ዕጥረት ምክንያት ሁለት ሰርትፍኬቶችን መስጠት አስቸጋሪ ባይሆን ኖሮ ሰርትፍኬቱ ለወ/ሮ ሚሚ
ብቻ ሳይሆን ለባለቤታቸው አቶ ዘሪሁን ተሾመም ይገባ ነበር ሲሉ ስማቸው እንዲገለፅ ፈቃደኛ ያልሆኑ የትምህርት ቤቱ ኮሚቴ አባል ለዘጋቢያችን አስታውቀዋል፡፡


የክብር ሰርትፍኬቱን የፊታችን ቅዳሜ ጥሪ የተደረገላቸው ወላጆችና እንግዶች በተገኙበት በቀበሌ 03 ቅጥር ግቢ ውስጥ የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁለተኛ ሴሚስተር ውጤት ይፋ ከተደረገ
በኋላ ከአርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ እጅ እንደምትቀበል ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

Image

Source: facebook ze-shinkurt


[addisnews][/addisnews]

Post Reply

Return to “Jokes and Funny stuff ...ቀልዶች እና አዝናኝ ርዕሶች”