ድሬዳዋ፡- ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችና በፓርቲው የትግል አቅጣጫ ዙሪያ ከድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በከተማዋ ተገኝቶ ባደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተወያየ፡፡
በስብሰባው ላይ ፓርቲው እስካሁን ያደረጋቸውን ህዝባዊ ትግሎችና ያስገኛቸውን ዋና ዋና ውጤቶች በድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ጌታነህ ባልቻ በኩል ለነዋሪዎች ገለጻ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም በፓርቲው ሀገራዊ አላማና የፖለቲካ ፕሮግራም ዙሪያ ለከተማዋ ነዋሪዎቹ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
‹‹ወደ ድሬዳዋ ከተማ መጥታችሁ ስላነጋገራችሁን ደስ ብሎናል›› ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ‹‹ምርጫ ሲደርስ ብቻ ወደ እኛ የመምጣቱን የቆየ ልምድ ሰብራችሁ ከአሁኑ ራሳችሁን ስላስተዋወቃችሁንና የትግል አጋራችሁ እንድንሆን ስለፈቀዳችሁ እናመሰግናለን›› ብለዋል፡፡ በስብሰባው ላይ የተገኙ አንድ አስተያየት ሰጭ በድሬዳዋ ከተማ ስላለው ወቅታዊና የፖለቲካ ሁኔታ አንስተው፣ በኢህአዴግ አገዛዝ የድሬዳዋ ነዋሪዎች እየደረሰባቸው ያለውን በደል አጋልጠዋል፡፡
‹‹ኢህአዴግ የማይገባበት ነገር የለም፤ ወዳጅ መስሎ በመሐላችን እየገባ ያጣላናል፡፡ ኢህአዴግ ክፉ መንግስት ነው፡፡ እንኳን መጣችሁልን እንጂ አብረናችሁ እንታገላለን፤ ለነጻነታችን ለመታገል ሞትን አንፈራም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በድሬዳዋው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ከህዝቡ በርካታ ጥያቄና አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችም ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የድሬዳዋ ነዋሪዎች መሬትን፣ ብሄር ብሄረሰብን፣ ሰንደቅ አላማን፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን፣ ምርጫ-2007ን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የውህደት አጀንዳን እና ሌሎች በርካታ አንኳር ጉዳዮችን አንስተዋል
ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ
ድሬዎች ለሰማያዊ ፓርቲ፡ “ኢሕአዴግ ክፉ መንግስት ነው፤ አብረናችሁ እንታገላለን”
- zeru
- Leader
- Posts: 952
- Joined: 19 Aug 2009 17:01
- Contact: