ሌባዋ ተማሪ

Life, Health, Religion, Social, General Question
Forum rules
No cursing, bad language and offend other users !
No pornographic images or links!
This forum monitored regularly. We will BAN users without warning for not obeying rules.
እባክዎ የፎረሙን ህጎች ያክብሩ::
selam sew
Leader
Leader
Posts: 618
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ሌባዋ ተማሪ

Unread post by selam sew » 01 Nov 2018 09:03

ታሪኩ እውነተኛ እና መሳጭ በመሆኑ አጠር አድርጌ ላካፍላቹ ፦

ነገሩ እንዲህ ነው፦

በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ መምህሯ ክፍል ገብታ ስታስተምር ከተማሪዎቹ አንዱ ይነሳና "መምህር እቃ ተሰርቂያለሁ" ይላል።

መምህሯም የተሰረቀው እቃ ምን እንደሆነ ካጣራች ቡኃላ ተማሪዎች ለፍተሻ እንዲዘጋጁ አደረገችና ፍተሻዋን ቀጠለች።

በፍተሻው ሰአት ታዲያ አንዲት እድሜዋ 10 አመት እማይሞላ ተማሪ ተራዋ ደርሶ ቦርሳዋን እንድትከፍት ስትጠየቅ አሻፈረኝ ትላለች።

መምህሯም በንዴት ጦፋ አንቺ ሌባ አንቺ ነሽ የሰረቅሽው ፓሊስ ነው ምጠራልሽ እያለች ስትጮህ የሰሙት ዳይሬክተሯ ከተፍ ይላሉ።

ይህን ጊዜ ልጅቷ የባሰ ድንጋጤና ፍርሃት እያንቀጠቀጣት እባክሽ ይቅር በይኝ እኔ ሌባ ኣደለሁም ከፈለግሽ እንኪ ፈትሽኝ ግን እዚህ ተማሪዎች ፊት አደለም እያለች መምህሯ እግር ስር ወድቃ ልመናዋን ቀጠለች።

መምህሯ ግን እየደነፋች ነው። በዚህ ጊዜ በእድሜ ጠና ያሉት ሴት ዳይሬክተር ቆይ እስቲ መምህር ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ ብለው ዳይሬክተሯ ወደቢሮ ወሰዷቸው።

ከዛም ልጅቷን በተረጋጋ ሁኔታ እንድትቀመጥ ቢያደርጉም መምህሯ ግን እስካሁን መረጋጋት አልቻለችም።

ዳይሬክተሯ መምህሯን ከገላመጡና ዝም እንድትል ካደረጉ ቡኃላ ልጅቷን እረጋ ብለው "ቦርሳው ውስጥ ምንድነው ያለው" ብለው ጠየቋት።

ልጅቷም "ቦርሳው ውስጥ ያለው ተማሪዎች በልተው የጣሉት ትርፍራፊ ነው ያለው" አለች በህፍረት እየተሸማቀቀች።

ሴትዮዋም በመገርምና ባለማመን ስሜት "እንዴት እንዲህ ይሆናል" ሲሉ ጠየቋት። እሷም "ለወንድሞቼ ልወስድላቸው ብየ ነው" አለች አንገቷን ደፍታ በሚያሳዝን ሁኔታ ቅስሟ ተሰብሮ።

ይህን ጊዜ ዳይሬክተሯ ከመቀመጫቸው ተነስተው ተጠጓትና ፀጉሯን እየደባበሱ "አይዞሽ የኔ ልጅ ተረጋግተሽ ስለ አባትሽና ስለ እናትሽ ንገሪኝ ኣሏት።

ይቺ አንዲት ፍሬ ልጅ እንባዋ እየወረደ እንዲህ አለች" አባቴ በሹፍርና ነበር የሚያስተዳድረን በኋላ ግን በአደጋ ተለይቶናል ።

እናቴም ብትሆን ምንም ገቢ ያልነበራት ስትሆን ያባቴን ሞት ስትሰማ እራሷን ስታ ሆስፒታል ገባች። በዛው የተነሳ ሽባ ሁና ቀረች።

ታዲያ ሁለት ጨቅላ ወንድሞች አሉኝ ቤት ነው ጥያቸው የመጣሁት ዘመድ ስለሌለን ዘወር ብሎ እሚያየን የለም።

እሚላስ እሚቀመስ የለንም። ታዲያ ይችን ፍርፋሪ ወስጄ ሂወታቸውን ብታደጋት ብየ ነው። እባካችሁ ለተማሪዎች እንዳትነግሩብኝ።

ትምህርቴንም ቢሆን አቋርጣለሁ። ብቻ አትናገሩብኝ እያለች አንጀት በሚያላውስ ሁኔታ ችግሯን ስትናገር ዳይሬክተሯ ልጅቷን አቅፈው አነቡ።

�ስለዚህ ከመፀፀት ይልቅ የሰዎችን ሁኔታ በእርጋታ ለመረዳት መሞሞከር ታላቅነት ነው።

ከወደዳችሁት 💜 ለወዳጃችሁ አጋሩት

ምንጭ: ፌስቡክ

Post Reply

Return to “Ethio General .... ኢትዮ ማህበረሰባዊ ርዕሶች”