ድንቅ ያፍሪካ አትሌቶች የሚሰሩት ስራ
መላውን ጥቁር ህዝብ እጅግ ስላኮራ፤
በየደረሱበት በየውድድሩ፣
ታሪክ እየሰሩ፣ ድል እያበሰሩ፤
የናት ምድራቸውን ስም ስላስከበሩ
ለታላቅ ሽልማት
ወደ አፍሪካ አዳራሽ በክብር ተጠሩ።
ከዚያም ጋዜጠኛ- ተናግሮ አናጋሪ የወሬ ሱሰኛ፤
ወደ አንዱ አትሌት ቀርቦ
አድናቆቱን ደልጾ ድምጹን አለዝቦ፤
‘ጽናት በሚጠይቅ በረዥም ርቀት
ታሸንፋላችሁ ሁሌም ያለጭንቀት፣
አምስት ሽ አስር ሺው ውጤቱ ቢያረካም
ዱላ ቅብብሉስ ለምን አይሳካም?’
በማለት ጠየቀ።
ታዋቂው አትሌትም በስሱ እየሳቀ
‘ቀን ከሌት በመስራት ጥረታችን ሰምሮ፣
ውጤታችን አምሮ
በስካሁን ድላችን
ረክቷል ህዝባችን
ዌል.. እንግዲህ ደግሞ ዱላ ቅብብሉን- ለመሪዎቻችን’
ብሎ ተናገረ
በዚህ ንግግሩም ሪከርድ ሰበረ።
አቤል ካሳሁንና ማህሙድ እንድሪስ ካሳተሙት
‘ከ… እስከ’ የግጥም መድብል የተወሰደ
ዱላ ቅብብል ግጥም (በአቤል ካሳሁንና በማህሙድ ኢድሪስ)
- girreda
- Runner
- Posts: 55
- Joined: 01 Oct 2009 12:45
- Location: Adama University
- Contact: