አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከዋሊያ አሠልጣኝነታቸው ተሰናበቱ

እግር ኳስ ፣ አትሌቲክስ ...
Soccer, Premier league, Athletics...
selam sew
Leader
Leader
Posts: 616
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከዋሊያ አሠልጣኝነታቸው ተሰናበቱ

Unread post by selam sew » 05 Feb 2014 16:21

ቴክኒክ ኮሚቴ ያቃተዉን ብዙ አሰልጣኞች መናገር የፈሩትን የፊፋዉ ሰዉ ባቀረቡት ሀሳብ ሰዉነት ቢሻዉ ከዋልያዉ ተሰናብተዋል፡፡ከዉስጥ ዉስጥ አዋቂዎች የተገኘዉን አዲስ ዜና እነሆ!!

ትላንት የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚዉ እልህ አስጨራሽ ዉይይት አደረገ፡፡ገሚሱ ሰዉነት ይቀጥል አለ፡፡ገሚሱ ደግሞ አይቀጥል ያመጣዉ ዉጤት አያስቀጥለዉም አለ፡፡

ይቀጥል ያሉት ምክንያት ያቀረቡት ሰዉነት ሀገሪቱ አይታዉ የማታቀዉን ዉጤት እንዲመጣ አድርግዋል፡፡ስለዚህ በትንሽ ነገር ማሰናበት የለብንም፡፡ትንሽ ከሚድያ ጋር ያለዉን ግንኙነት እና ግትርነቱን ይቀንስ እና እድል ይሰጠዉ ነዉ ያሉት!!

ሌሎቹ ደግሞ በ2ት የአፍሪካ ዋንጫዎች ምንም ነገር አላመጣም፡፡ህዝቡም የሱን ስንብት ይፈልጋል በሚል ተተጋተጉ!!

መጨረሻ ላይ አንድ ዉሳኔ አሳለፉ፡፡ዉሳኔዉን ከይፋዊ መግለጫ በፊት ለማንም ላለመናገር ቃል ተገባቡ፡፡በመሀላ ነዉ ቃል የተግባቡት፡- ከስራ አስፈጻሚዎቹ መሀል አንዱን ብትጠይቁ ከመሰብሰባቸዉ ዉጪ ማንም ስለዉሳኔዉ አይነግራችሁም ነበር፡፡

Imageክርክሩ መሀል ላይ የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት የተናገሩት ነገር ሚዛን ደፋ እናም ሁሉንም አስማማ፡፡አቶ ተክለወይኒ የተናገሩት ነገር የፊፋዉ ዋና ፀሀፊ ዤሮም ቫልክ ስለ ዋልያዉ የሰጠዉን ግምገማ አቀረቡ፡፡ዋና ፀሀፊዉ የተናገሩት ዋልያዉ ለአለም አቀፍ ዉድድር ብቁ የሆነ አሰልጣኝ እንደሌለዉ…ነገር ግን ቡድኑ ጥሩ ነገር መስራት የሚያስችል አቅም እንዳለዉ ተናገሩ፡–ከዚህ በኋላ ሁሉም ተስማምተዉ ሰዉነት እና ምክተሉ ዳኜ እንዲሁም የበረኞቹ አሰልጣኝ ቅጣዉ ሙሉ እንዲሰናበቱ ተወሰነ፡፡

እናም ዛሬ 10.30 ላይ በፌዴሬሽኑ አዲሱ ጽህፈት ቤት መግለጫ ጠርቶ ሰዉነት መባረሩን ተናገረ፡፡ለቻን ዉድድር የተቀመጠለት ግብ ዋንጫ ማምጣት እንደነበር ፌዴሬሽኑ ዛሬ ይፋ አድርግዋል፡፡ተጫዋቾቹም ዋንጫ ብናመጣ ስንት ብር እንሸለማለን ብለዉ እንደጠየቁም ምክትል ፐ‹ሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

እስከዛሬ የነበሩት አሰልጣኞች የሚቀጠሩት እና እና የሚሰናበቱት ስታድየም ከሚገኘዉ ቢሮ ነበር፡፡ሰዉነት ስታድየም ተቀጥረዉ ካዛንቺስ የተሰናበቱ የመጀመሪያ ሰዉ ሆነዋል፡፡

ሰዉየዉ በቅዳሜዉ ግምገማ ወቅት በራሳቸዉ ጊዜ ለመልቀቅ እንዳለሰቡ አስታዉቀዋል፡፡

ይህን ስሰማ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡-ሰዉነት የቶም ሴንት ፊት ምክትል ሆነዉ የተቀጠሩ ጊዜ አንድ የስልክ መልእክት ላኩሉኝ፡-የዉጭ አሰልጣኝን እኛ ተባብረን ከሰራን ማስናቅ እንችላለን የሚል ሀሳብ የያዠ መልእክት ነበር ፡፡

አንድ የልምምድ ቀን አበበ በቂላ ስታድየም ሰዉነት ሱፍ ለብሰዉ መጡ፡፡ቶም ሴንት ፊት ፊቱ ደም ለበሰ፡፡ምክትል አሰልጣኝ ነህኮ እንዴት ሱፍ ለብሰህ ትመጣለህ አሉ፡–ነገሩ ተካረረ ከዛ አፈወርቅ በመሀል ገቡ!!እንዴት በገዛ ሀገሬ እንዲህ ትለኛለህ አሉት ሰዉነት፡–

ቶም በጣም ለሚቀርበዉ ሰዉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፡–እኔ የብሂራዊ ቡድን አሰልጣኝ ስሆን ምክትል መምረጥ የነበረብኝ ራሴ ነበርኩ፡-አሁን ግን ምክትሌ ዋና እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡ግን ይሳካለታል ብዬ አላስብም አለኝ!!

አሁን ይህ ነገር ከተፈጠረ ሶስተኛ አመቱን ይዥዋል፡፡ሰዉነትም እንደቶም ሊሰናበቱ ሰአታት የቀራቸዉ መስልዋል፡፡

ሰዉነት ቢሻዉ ዉሳኔዉን ሰምተዋል፡፡ሶስቱም አሰልጣኞች ተጠርተዉ ተነግርዋቸዋል!!!ዉሳኔዉንም ተቀብለዉታል፡፡

መጪዉ አሰልጣኝ ማን እንደሚሆን በቅርብ ግዜ እንደሚያሥታዉቅ ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርግዋል፡፡

ምንጭ: ኢትዮቲዩብ

Post Reply

Return to “Ethio Sport .... ኢትዮ ስፖርት”