አራት የሰቆቃ ዓመታት በህወሓት እስርቤት - በየነ ገብራይ ከደንማርክ
ክፍል 1
ምንጭ:- በየነ ገብራይ ፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/btesfu1ቀኑን ግንቦት 30 1984 ነበር። ወደ ማምሻ ላይ ከባድ ዝናብ ዘንበና ዋልካው የተዋባ መሬት ጭቃ በጭቃ ሆኖ ነበር። ስለሆነም በጊዜ እራታችን በልተን በዕለቱ በዘነበው ዝናብ ምክንያት መሬቱ ቀዝቅዞ ስለነበረ ሌላ ጊዜ በግቢው ውጭ ስንተኛ የነበረ በዛን ዕልት እኔና ባለቤቴ የሁለት ዓመቷ ልጃችን ይዘን ቤት ውስጥ በጊዜ ተኛን። አንድ እኔ ጋር ተጠግቶ የሚኖር የነበረ ዘመድ፣ አንድ ያስጠጋናቸው ሽማግሌና ሌላ እንግዳ ግባዛ ውስጥ ተኙ።

እኔን ከግቢው ሲያወጡ ለቤተሰብ አንድ ድምጽ እንዳታሰሙ፣ ከግቢው ውጭ ጠባቂዎች አሉ ብለው አስጠንቅቀው ከግቢው ውጭ ቆማ ስትጠብቅ ወደ ነበረች ፒክ አፕ ቶዮታ መኪና ወሰዱኝና ወደ መኪናዋ ውጣ አሉኝ። መኪናዋ ላይ እንደወጣሁ እጆቼን የኋሊት አስረው፣ በ5 የድህንነት ሰዎች ታጅቤ መኪናዋ ከተዋባ ወደ ገዳሪፍ ከተማ አቅጣጫ በፍጥነት በረረች። ሲንያን (የካርቱም ከሰላ መንገድና ወደ ገዳሪፍ የሚወስደው መንገድ መለያያ) አልፈን፣ ገዳሪፍ ከተማን ማኸል ለማኸል የሚያቋርጠው ዋና መንገድ ይዘን በደመኑር በኩል ወደ ራብዓ የገዳሪፍ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ደረስንና ቶዮታዋ አንድ ትልቅ ሎሪ አጠገብ ቆመች፣ ከቶዮታዋ እንድወርድና ወደ ሎሪዋም እንድወጣ አዘዙኝ። እጄ ታስሯል እኮ መውጣት አልችልም ስላቸው ሁለት የደህንነት ሰዎች ደግፈው ሎሪዋ ላይ አወጡኝ። ላይ ሎሪዋ ላይ ተዘጋጅቶ ሲጠብቅ የነበረ የድህንነት ሰው በጠመንጃ ሰደፍ ማጅራቴ ላይ መቶኝ በሎሪዋ ወለል ወደቅኩ። እንደወደቁኩም ሌላ የድህንነት ሰው እግሮቼን ወደኋሊት አጥፎ ከእጆቼ ጋር ጠፍሮ አንድ ላይ በጣም አጥብቆ አሰረኝ። በሰደፍ ማጅራቴ ላይ ከተመታሁት ምት ትንሽ ማገገም ስጀምር ከኔ በፊት እንደኔው እጅና እግራቸው አንድ ላይ ታስረው ሎሪዋ ወለል ላይ በሆዳቸው የተኙ፣ እንዲሁም ጥግ ጥጉን ይዘው ቁጭ ያሉም ሰዎች ቢታዩኝም ሁሉም ጸጥ ብሎ ስለነበረ መጀመሪያ ላይ ማንነታቸውን ለመለየት አልቻልኩም ነበር። ትንሽ ጊዜ እንደቆየን ከጎኔ እንደኔ እጅና እግሩ አንድ ላይ ታስሮ በሆዱ ተጋድሞ የነበረ ሰው ማቃሰት ጀመረ። ይህን ጊዜ ያ ሲያቃስት የነበረው ሰው በደምብ የማውቀው ጓድ ስለነበረ በድምጹ ለየሁት። ከዛም ከየቦታው ጓዶችን በሎሪዋ ላይ እያሰባሰቡ መሆናቸው ተረዳሁ፣ አንድ ላይ አሰባስበው ለህወሓት ሊያስረክቡን እየተዘጋጁ መሆናቸውም ወዲያውኑ አወቅኩ።
ትንሽ እንደቆየን መሬት ላይ ከነበሩ የድህንነት ሰዎች አንዱ ጮክ ብሎ በመገናኛ ረዲዮ ሌላ ቦታ ካለ ሰው ጋራ መነጋገር ጀመረ። ወዲያ የነበረው ሰው ምን እንደሚል ባይሰማም አጠገባችን የነበረው የሚናገረው በደምብ ይሰማ ነበርና የሚያወሩት የነበረው ስለ ሌሎች ታፍነው ወደ ሎሪዋ መምጣት የነበረባቸው ጓዶች በተመለከት መኖሩ አውቅኩ። በምጨርሻ ቤቱን ካጣችሁት ክንግዲህ አሰሳዉን ተዉት፣ ከንግዲህ መጠበቅ አንችልም፣ መድረስ ያለብን ቦታ መሬቱ ከመንጋቱ በፊት መድረስ ስላለብን የያዝነውን ይዘን እኛ እንቀጥላለና እናንተ ወደ ሰፈራችሁ ተመለሱ ሲለው ሰማሁ። እንደላውም ከትንሽ ጊዜ ቆይታ በኋላ ሎሪው ለመንቀሳቀስ ሞተሩን ማሞቅ ጀመረ። ከጥቂት ደቂቃዎች ሞተሩን ማሞቅ በኋላ ሎሪው መንቀሳቀስ ጀመረ። ከከተማው እስከምንወጣ ምንገዱ አስፋለት ስለነበረ አንድ ላይ የታሰሩ እጆቼና እግሮቼ አከባቢ ከሚሰማኝ ቃንዛ ውጭ ብዙ ችግር አልነበረም። ከተማውን ጨርሰን ወደ ገጠሩ እንደገባን መንገዱ በጣም የተበለሸ ኮረኮንች መንገድ ስለነበረ ሎሪው ሲበር በሚያደርገው ወደላይና ወደታች መዝለል እኔም በደረቴ ከሎሪው ወለል ጋር መላጋት ጀመርኩ። እጅና እጋራቸው እንደኔው በንድላ ተጠፍሮ የታሰሩ ጓዶችም እንደኔው እንደ ኳስ መንጠርና እርስ በርስ መጋጨት ጀመርን። ስቃዩ ገና ከጀምሩ ከዓቅማችን በላይ ስለሆነብን መጮህ ጀመርን፣ ነገር ግን እሪ ብትልም ሰሚ አልነበረም። በዚህ ዓይንት ሁኔታ ወደ 5 ሰዓት ያሀል ተጉዘን ሊነጋጋ ሲል ወደ አንድ ሰፈር አከባቢ ደረስን። ለሰፈሩ መቃረባችን የተረዳነው በዶሮና በውሻ ጩኸት ነበር። ሌሊቱም ሊነጋ ተቃርቦ ጨለማውን ብርሃን እየወረሰው ስለነበረ በተወሰነ ደረጃ በትክክል ማን ማን መሆኑን ለመለየት ቢከብድም ከተቀመጡት መካከል ሴቶች መኖራቸውን መለየት ቻልኩ።
ትንሽ እንደተጓዝን ሎሪው ቁሞ ለኛ እጅና እግር አንድ ላይ ታስረን ለነበርን ጓዶች እግራችን ተፈቶልን እጃችን ብቻ እንድንታሰር ሃላፊው አዞ እግራችን ተፈታልን። ይህን ጊዜ በቂጤ ቁጭ ማለት ስለቻልኩ፣ እየነጋም ስለነበረ እሎሪዋ ላይ የነበሩ ሰዎቹን ለመለየት አትኩሬ መመልክት ጀመርኩ። በመጀመሪያ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ተቐምጦ የነበረ አንድ ጓድ በቀላሉ ለየሁት፣ ቀጥሎም ሁለት ነጣለ ለብሰው የነበሩ ሴቶች ለየሁ። ብርሃኑ እየጨመረ ሲሄድ ሁሉም ጓዶች በግልጽ ይታዩኝ ጀመርና ሁሉንም ለየሁዋቸው። ለራሴና በሎሪዋ ላይ ለነበሩ ለጓዶቹ ባዝንም በሎሪዋ ላይ ይኖሩ ይሆን እያልኩ በከፍተኛ ጭንቀት ስፈልጋቸው የነበረው ጓድ ጋይምና ጓድ ዑስማን የማእከላዊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎች ሲኒየር ጓዶች እሎሪዋ ላይ አለመኖራቸው ሳረጋግጥ ትልቅ የመንፈስ እፎይታ ተሰማኝ። ሎሪው ትንሽ ከተጓዘ በኋላ አንድ ሰፈር ደርሶ ቆመ።
ሎሪው የቆመበት ሰፈር መተማ ነበር። ሎሪው ቆሞ ትንሽ እንደቆየ መተማ ላይ እኛን ለመረከብ ሲጠባበቅ የነበረው የህወሓት ባለስልጣን ሰራዊቱን አስከትሎ ወደ ሎሪው መጣ። የህወሓቱ ባለስልጣን በአሰተርጓሚው አማካይንት ከደህንነት ሃለፊ ጋር ስለኛ ይጠይቃል። ስንት ናቸው ብሎ የህወሓት መሪ ደህንነቱን ስጠይቀው፣ የድህንነት መሪው በትክክል አልቆጠርናቸውም ወደ 20 ይሆናሉ ብሎ መለሰለት። የህወሓት መሪው እኛ የምንፈለጋቸው በሊስቴ ያሉት 18 ብቻ ናቸው ብሎ ራሱ እኛን ለማየት ወደ ሎሪው ወጣ። ሲያየን እግራቸው የተቆረጠ በክራንች የሚሄዱ፣ በጣም ስስ የውስጥ ልብስ ብቻ የለበሱ ሴቶች፣ ዓይነስዉር፣ ሁለት እግራቸው ፓራላይዝ የሆኑ ሲያይ ድንጋጠውና ሀዘኑ ፊቱ ላይ በጉልህ ይነበብ ነበር። ካየን በኋላ ከመኪናው ዘሎ ወርዶ ምን ዓይንት ሰዎች ናቸው ያመጣችሁልን፣ እኛ የፈለግናቸው ሰዎች እነዚህ አይደሉምና ከ4ቱ ውጭ ያሉትን መልሳችሁ ውሰዱዋቸው ብሎ ከደህንነቱ ሰውየ ጋር በአሰተርጓሚው ብኩል ሲነግረው የድህንነት ሰውየውም ብፍጹም አላደርገውም ከፈግክ ሁሉንም ተቀበላቸው ካልሆን ግን እዚሁ መተማ ላይ አርግፌያቸው ነው የሚሄደ በማለት ክርክር ገጠሙ። የደህንነቱ ሃላፊም የዋዛ አልነበረምና ትረከብ እንደሆነ ተረከብ፣ ካልሆነ ግን እዚሁ አራግፌያቸው ነው የምሄደው ብሚለው አቋሙ እንደጸና ቀረ። ከዛ የህወሓት ባለስልጣን በረዲዮ ከበላዮቹ ጋራ ከተነጋገረ በኋላ እንዳለን ለመረከብ ተስማምቶ ሎሪው ከመተማ ከተማ ወደ ሸሄዲ በሚወስደው መንገድ ከከተማው ወጣ ብሎ አንድ ጎድጓዳ ስፍራ ውስጥ እንዲቆም ተደርጎ እንድንወርድ ታዘዝን። ራሱን ችሎ መውረድ የሚችል ብዙ ሰላልነበረ ለመውረድ ረዳት ያስፈልገናል ብዬ እኔ በትግርኛ ለህወሓት አባላት ተናገርኩ። መሪው ሁኔታውን ተመልክቶ ስለነበረ የተወሰኑ የህወሓት ታጋዮች ሎሪው ላይ ወጥተው እንዲረዱን ተደርጎ ከሎሪው አወረዱን፣ ሎሪዋም እኛን አራግፋ ሲጠብቁን የነበሩ የሱዳን ደህንነቶችን ብቻ ጭና ወደ ሱዳን ተመለስች፣ ከዛች ሰዓት ጀምሮም እኛ በህወሓት ቁጥጥር ስር ገባን።
በክፍል 2 ፣
በመተማ የአንድ ቀን ተኩል ቆይታና ጉዞ ወደ ሸሄዲ ምን ይመስል ነበርን ይጄላችሁ እቀርባልሁ።▼▼ ክፍል 2ን ለማንበብ ወደታች ይቀጥሉ ▼▼
በየነ ገብራይ ከደንማርክbtesfu45@gmail.com
0045 20545658