የአብርሃ ደስታ የፍርድቤት ውሎ………

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
selam sew
Leader
Leader
Posts: 599
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

የአብርሃ ደስታ የፍርድቤት ውሎ………

Unread post by selam sew » 05 Sep 2014 09:58

የአብርሃ ደስታ የፍርድቤት ውሎ………
By Mer Ethio Addis
አብርሀ ደስታ ለሁለተኛ ግዜ ዛሬ አራዳ ፍርድቤት ቀርብዋል፡፡
በዛሬው የፍርድቤት ውሎው ላይ እንደባለፈው ሁላ ብዙ ወጣቶች የተገኙ ሲሆን አብርሀ ወደ ግቢው ሲገባ ሞቅ ያለ አቀባበለ የተደረገለት ሲሆን ይሄ ከነበሩት ፌደራል ፓሊሶችና የአዲስ አባባ ፓሊሶች ላይ ቁጣ አስከትልዋል፡፡ ከግቢ ውጡ ከሚል ጭቅጭቅ ጀምሮ ተዋቻው አንድ በአንድ በተራ ይመጣሉ የሚል እሰጣ ጋበን አስተናግድዋል፡፡
ፓሊሲ ለፍርድ ቤቱ ማስረጃ እና ምስክር ሰብስቦ ስላልጨረሰ ተጨማሪ የምርመራ ቀን የጠየቀ ሲሆን የአብርሀ ጠበቃ አቶ ተማም ደግሞ ፍርድቤቱ የፓሊሰን ጥያቄ መቀበል የለበትም፡፡ ፓሊሲ ማስረጃ ምስክር ማዘጋጀት የነበረበት ክስ መስርቶ ደንበኛዬን አስሮ መሆን አልነረበትም ይህ ህገወጥ ነው፡፡ እንዲያውም እንዲህ አይነት አካሄዶች ጉዳዩን ያፓሊካ እንጂ የ ወንጀል ክስ እንዳልሆነ ያሳያሉ ብለዋል፡፡
Image
ፍርድቤቱ……የሁለቱንም ጥያቄ ካዳመጠ ቡሀላ የፓሊስን ጥያቄ ተቀብሎ የሀያ ስምንት ቀን ቀጠሮ ሰጥትዋል፡፡
በተጨማሪም ጠበቃ ተማም አባቡልጎ በዳኛው የደረሰባቸውን አንዲህ ይገልጻሉ ዳኛው አቶ ሙሉ ክንፈ ፍርድቤትን ደፍረሀል ብለው አስፈራርተውኛል ፡፡ጥብቅናዬንም እንደሚያሰርዙብኝ ዝተውብኛል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም አቶ ተማም አብርሀ እየቀረበ ያለው ፍርድቤት ችሎት ውስጥ አደለም የአቶ ሙሉ ቢሮ ውስጥ እንጂ ይህ ደሞ በፍፁም አግባብ አደለም ብለዋል፡፡
አብርሀ በበኩሉ ቤተሰብ እና ጠበቃውን እንደልቡ ማግኝትእንዳልቻለ አሳውቅዋል፡፡ ፍርድቤም ለአብርሀ ፖሊስ ጣቢያው ቤተሰቡን እና ጠበቃን ማየት እንዳይከለክለው ትዛዝ አስተላፏል፡፡ ለመስከረም ሀያ ሁለት ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ ውሎውን አጠናቅዋል፡፡
የአብርሀ የፍርድቤት ይህን ይማስላል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የአረና ፓርቲ ተወካይ አቶ ካህሳይ ህብረተሰቡ ለአብርሀ እስካሁን ላደረገለት ድጋፍ አመስግነው ከዚህም ቡሀላ ድጋፉ እንዳያለይ አሳስበዋል፡፡
አብርሀን ለመርዳት ተከታዩን የሂሳብ ቁጥር ይጠቀሙ፡፡
አዋሽ ባንክ አራት ኪሎ ቅርንጫፍ ሰዊፈት ኮድ ፡ AWINETAA 01320215682400

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”