የኢህአዴግ በደሉ፤ ከመደበደቡ… እሪታ መከልከሉ

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

የኢህአዴግ በደሉ፤ ከመደበደቡ… እሪታ መከልከሉ

Unread post by zeru » 01 Apr 2014 20:36

የኢህአዴግ በደሉ፤ ከመደበደቡ… እሪታ መከልከሉ
እኔ የምለው ያቺ ብርቱካን ሚዴቅሳ የት ጠፋች… እንደ ተወርዋሪ ኮከብ ብልጭ በላ ጉልበታችንን ስመን ቀና ስንል ያጣናት አይነት እየተሰማኝ ነውኮ…
“እስቲ ፈልጉልኝ በርቱካን ብላቹ
ኮምጣጤ እና ሎሚ መሮናል ያላቹ”
ምናምን የሚል ግጥም ክሽን ካለች ዜማ ጋር አድርጌ አንድ ነጠላ ዜማ ልልቀቅ እንዴ… መቼም ብርቱ ካህንን ለመሰለች ተወዳጅ ፖለቲከኛ በየግድግዳው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ መለጠፍ አይመጥናትም። ስለዚህ እስቲ የግጥም እና ዜማ አድባር የቀረባችሁ ወዳጆች ለብርቱዋ ሴት የሚመጥን የ አፋልጉኝ ዜማ እና ግጥም አዋጡ።
ዛሬ በምን ትዝ አለችኝ መሰላችሁ… “ኢሃአዴግ መግረፉ ሳይሆን አትጩሁ ማለቱ ነው በጣም የሚደንቀኝ” ብላ በአንድ ወቅት ያጫወተችን ትዝ ብሎኝ ነው… እርሱስ በምን ትዝ አለኝ…
አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ሰሞኑን አንድ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ ነበር… ሰላማዊ ሰልፉ በአዲሳባ እንደ ዳይኖሰር ድራሻችው ሊጠፋ ጥቂት የቀራቸው የሚመስሉት፤ ውሃ፣ መብራት፣ ስልክ እና ትራንስፖርትን አስመልክቶ በጋራ እሪ ብለን በመጮህ በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ጠቀላይ ሚኒስትር ሆነው በቤት መንግስት ውስጥ ለተቀመጡት ሰውዬ አቤት እንበል በሚል ነበር። (በቀንፍም ሰውዬን በትምህርተ ጥቅስ ብዬ የጠቀስኳቸው እኔ ነኝ እንጂ አንድነቶች አይደሉም… ተደፋፈርኳቸው አይደል…!)
እና… ከአይናችን የተሰወረችቱ ብርቱ እንዳለችው ኢሃዴግ መድብድቡን ብቻ ሳይሆን ጩኸት መገደቡንም ያውቅበታልና ትንፍሽ ማለት እንደማይቻል ትላንት በተሰራጨው ደብዳቤ ለሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስተኛ ግዜ አሳይቶናል (ቁጥር ላይ እጅግም ነኝ እና ግምቴ ያነሰ ከመሰላችሁ በሃያ ማባዛት ነው… ልሳቅ ልተወው ማለት ይሄኔ ነው አትሉኝም…!)
አንድነቶች ሰልፉን የጠሩት ቀበና ከሚገኘው የአንድነት ቢሮ በመነሳት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ድረስ ለመሄድ ነበር። የአዲሳባ ሰላማዊ ሰልፍ አዋቂ ክፍል በበኩሉ “በርካታ ትምህርት ቤቶች፣ ዩንቨርስቲዎች እና የመንግስት ተቋማት ባሉበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ማድርግ አይቻልም” ብሎ ከልክሏል። እንደኛ “ልማቱ ጣራ በነካበት” ሃገር ደግሞ መንገድ ሁሉ ዩንቭርስቲ መንገድ ሁሉ ትምህርት ቤት መንገድ ሁሉ የመንግስት ተቋም ነው።
Imageታድያ ሰላማዊ ሰልፍ አዋቂ መስሪያቤቱ ምን ማለቱ ነው “ብዙ ትምህርት ቤት ዩንቭርስቲ እና የመንግስት ተቋም ባለበት ሰልፍ አታደርጉም” ማለቱ… ብለን የጠየቅን እንደሆነ ከተማ ውስጥ ምንም ተቃውሞ ማሰማት አይቻልም የከፋው ካለ ጫካ መግባት ይችላል ማለቱ ሳይሆን እንደማይቀር እንጠረጠራል።
ሰለ ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባ የወጣው አዋጅ ቁጥር 3/1983 በአንቀጽ 7 ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እና የፖለቲካ ስብሰባ ማድረግ የሚከለክልባቸውን ቦታዎች እንዲ በማለት ያስቀምጣቸዋል፡-
1. ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ቦታዎች 100 ሜትር ርቀት ውስጥ ሊደረግ አይችልም፡-
ሀ. በኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሥራ ቦታና የመኖሪያ ቦታ፣
ለ. በቤተክርስቲያን፣ በመስጊድና በመሳሰሉት የጸሎት ቤቶች እንዲሁም በሆስፒታልና በመካነ መቃብር ዙሪያ
ሐ. በገበያ ቀን ሰላማዊ ሰልፎችን ወይንም የሕዝብ ስብሰባዎችን ለማስተናገድ አስቸጋሪ በሚሆኑ የገበያ ቦታዎች
2. ማንኛውም ሰላማዊ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ በጦር ኃይሎች በጥበቃና የሕዝብ ሰላምና ደህንነት በሚቆጣጠሩ የመንግስት የሥራ ክፍሎች አካባቢ 500 ሜትር ርቀት ውስጥ ሊደረግ አይችልም፡፡
የአዲሳባ ሰላማዊ ሰልፍ አዋቂ መስሪያ ቤት እውቅና ለመከልከል ከእነዚህ ውስጥ አንዱን እንኳ አልጠቀስም። ቢያንስ… ለአዋጁ ክብር ሲባል እንኳ ምናለ አንዱን እንኳ ጠቅሶ እውቅና አልሰጥም ቢል ብለው የጠየቁ እንደሁ እኔ ድንጋይ ነክሼ እምላለሁ በሀግሪቱ ላሉ አዋጆች ተቃዋሚዎች እና እኛ ተርታ ግለሰቦቹ የምንጨነቀውን ያክል የመንግስት አካላች ቁብ የላቸውም። (ደሮስ የመንስግስት አካላት እቁብ እንጂ ለምንስ ቢሆን ምን ቁብ አላቸው አይሉኝም!)
ለማንኛውም በአንድነቶች በኩል የተሰጠውን ምላሽ እስካሁን አልሰማሁም፤ እኔ በበኩሌ ግን ከስልኩም፣ ከመብራቱም፣ ከውሃውም እኩል አዎጆቹን እና ሀገምንግስቱን አስገድዶ እየደፈረ ያለው ጎረምሳው መንግስታችን አቅሉን ሰብሰብ ያደርግ ዘንድ እሪታ ያስፈልገናል ባይ ነኝ።
በመጨረሻም፤
“አንተ እንግሊዝ ሆነህ ማክዶናልድህን እየበላህ ምስኪኑን ህዝብ ልታስጨርስ…” ከሚለው አስተያየት ውጪ ሊሌች አስተያየቶችን በሙሉ የማስተናግድ መሆኔን በታላቅ ትህትና እገልጻለሁ

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”