መንግስት በጎንደር ለምርጫ ቅስቀሳ 8ሺህ ብር እያደለ ነው

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

መንግስት በጎንደር ለምርጫ ቅስቀሳ 8ሺህ ብር እያደለ ነው

Unread post by zeru » 29 Mar 2014 20:07

[justify]Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. March 29, 2014)፦ ዛሬ ገዥው ፓርቲ በጎንደር ከተማ አደባባይ እየሱስ በጠራው ስብሰባ ለእያንዳንዳቸው ተሰብሳቢዎች 8ሺህ ብር ብድር በመስጠት መጭውን ምርጫ ግን ኢህአዲግን እንዲመርጡ በመቀስቀስ ላይ ባለበት ወቅት ምርጫን በገንዘብ መግዛት አይቻልም ብለው ጥያቄ ያቀረቡ አምስት የአንድነት ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን አቶ ሃብታሙ አያሌው ዛሬ ይፋ አደረገ።[/justify]
[justify]የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት የሆነው አቶ ሃብታሙ አያሌው ከቫንኩቨር ካናዳ በየሳምንቱ ቅዳሜ ለሚተላለፈው መለከት የኢትዮጵያ ራዲዮ በሰጠው ቃል ለእስር ተዳርገዋል የተባሉትን የፓርቲውን አባላት ለማስፈታትና ጉዳያቸውን ለመከታተል ዛሬ እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።[/justify]
[justify]በጎንደር ገዥው መንግስት ለተሰብሳቢዎች 8ሺህ ብር ለእያንዳንዳቸው በማስፈረም በሚሰጥበት ሰዓት በሚቀጥሉት ሶስት አመታት ውስጥ የገንዘቡን እጥፍ እንደሚጨመርላቸው ቃል ተገባላቸውና ነገር ግን በመጨው ምርጫ ኢህአዴግን እንዲመርጡ መጠየቃቸውን የሰሙ ተቀላቅለው የገቡ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ምርጫውን በገንዘብ መግዛት አይቻልም በማለት ተቃውሞ በማንሳታቸው አምስት ሰዎች ወደ እስር ቤት መወሰዳቸውን ለማወቅ ችለናል።[/justify]
[justify]ወጣቱ የሚያደርገውን የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ሊገታ የማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጸው የአንድነቱ ሃብታሙ አያሌው የወጣቶቹን ታሳሪዎች ሁኔታ ድርጅቱ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አመልክቷል።[/justify]
[justify]
[/justify]

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”