አንድነት ሃይል ነው!

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

አንድነት ሃይል ነው!

Unread post by zeru » 25 Mar 2014 19:05

ባለፉት ረጅም አመታት ኢትዮጵያና ህዝቦቿ የነበራቸዉ የፍቅር ተጣምሮ ኢትዮጵያን የሚያዉቋት ሲግልጿት አይናችው በእንባ ይሞላል። ምክንያቱ ደግሞ ዛሬ በለስ ቀንቶት በስልጣን ላይ ያለዉ አምባገነኑ ወያኔ ከህዝብ ልብ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት፣ አንድነት፣ ፍቅር እንዳይኖር የብሔር ብሔረሰቦች መብት እና እኩልነት በሚል የመከፋፈል ዘይቤ ለሶስት ሺህ ዘመን የነበረውን የአገር ፍቅር ስሜት ሆድና ጀርባ በማድረግ ህዝቡን ገለልተኛ እና ብሄርተኛ ስላደረገ ነው። በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደርሰው በደልና መከራ ወለደን ብለው እየፎከሩ ወደ ጫካ ለትግል የገቡት ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባ ገብተው ከተደላደሉ በኋላ በህዝብ መብትና ነፃነት፤ በሀገር አንድነትና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ ይህ ነው ተብሎ ሊነገር የማይችል እጅግ በጣም የከፋ በደል ፈፅመዋል፤ አሁንም እየፈፀሙም ይገኛል። የዘረኞቹ ወያኔ መሪዎች እቅድ የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘር፣ በሀይማኖትና በክልል በመከፋፈል በጠመንጃ ሀይል የያዙት ስልጣን በግዜና በህገ-መንግሰት ያልተገደበ መሆኑን ለማረጋገጥና የእኛ ነው ለሚሉት የሕብረተሰብ ክፍልና ለሚተባበሯቸው ሆዳሞች ተቆጥሮ የማያልቅ ሀብት ማጋበስ የሚችሉበት መንገድ መፍጠር ነው።
ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን እኛ ኢትዮጵያውያን በድህነት፣ በረሃበ የምናልቀው በዘረኝነት አለንጋ የምነገረፈው፣ የምንሰደደው፣ የምንታሰረው፣ የምንገደለው ፈጣሪ የሰጠንን ነፃነት የሚባል ሀይል ወያኔ ሲቀማንና አፋችንን ዘግተን እጃችንን አጣጥፈን ስለተቀመጥን ነው። የፖለቲካ ተቀናቃኞችን፤ ጥርስ የነከሰባቸውን የህብረተሰብ አባላት እያሰረና እየገደለ ዛሬ ላይ ደርሷል። በተለይ የወያኔ መንግስት ብዕርና ወረቀት ይዘው በሀሳብ እና በመግባባት ችግርን ይፈታ፤ ድምፃችን ይሰማ እያሉ የሚዘምሩትን የመብትና እና የነፃነት ጥያቄ አንግበው በሰላማዊ መንገድ የታገሉትን ኢትዮጵያውያን የእስልምና እምነት ተከታዮችን አክራሪዎች እያለ በፍትህ ተቋሞች በኩል ላይ ተፅእኖ በመፍጠር የፖለቲካ ውሳኔውን በማሳለፍ ሰላማዊ ዜጎችን ለረጅም ጊዜ እስርና እንግልት እየዳረጋቸው ይገኛል፡፡ የወያኔ መንግስት በኢኮኖሚውም ዘርፍ ላይም የአንድ ጎሳ የበላይነት ባዘለ መልኩ ሌሎች ሰዎች እንዲንቀሳቀሱ የተለያየ ማነቆዎች በማዘጋጀት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በብቸኝነት ተቆጣጥሮታል።
የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ አገዛዝ ሲያሸማቀቅና በተናጥልና በጋራ ለጥቃት ሲይጋለጥ ኖሯል። አልፎ ተርፎ ወያኔዎች በታሪክ አጋጣሚ ወደር የማይገኝላቸዉን በፍፁም ጭካኔ የተሞሉ ጭፍጨፋዎችንና የአካልና የስነ ልቦና ጠባሳዎችን እያደረሱ ይገኛሉ። በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች መንስኤው በውል ባልታወቀ ምክንያት ከቤታቸውና ከየመንገድ እየተለቀሙ በየእስርቤቱ ታጉረዉ ሰቆቃና ግፍ እየደረሰባቸው ይገኛል። ህጻናት፣ እናቶች እና አባቶች በየመንገድ ላይ ያለምንም ጥፋት በአምባገነኑ የወያኔ መንግስት ቀጥተኛ ትእዛዝ ያለምንም ርህራሄ በግፍ እየተጨፈጨፉ ነው።
ስለዚህ አምባገነኑ ወያኔ በሃገራችንና በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያ፤ እስር፤ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እና ሰብዓዊነት የጎደለዉ አፈናን ለማስቆምና ስርአቱን ለመገርሰስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ ትግላችንን ለማጠናከር መዘጋጀት አለብን። በተለይም በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የተያዘዉን የትግል ጎዳና ጫፍ ለማድረስ የአለም መንግስታት ድምጻችንን እንዲሰሙና በወያኔ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርጉ አቅማችን በፈቀደዉ መጠን ሁሉ አንድነታችንን አጠናክረን መረባረብ አለብን። እንደ ዜጋ በሃገራችንና በህዝቧ ላይ የሚደረግ ማንኛዉንም ጥቃትና ኢ-ሰብዓዊ ተግባር ሊያመንና ሊሰማን ይገባል። ለዚህም ነው የወያኔ መንግስት እያደረሰ ያለዉን ኢ-ሰብዓዊ ተግባር ከስር ከመሰረቱ ለማስወገድ በሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ መሳተፍ የአንድ ዜጋ ማንነት ጥያቄ ነዉ የሚባለው። በአስተሳሰብ ደረጃ የበሰለ ማንኛዉም ዜጋ፤ ወይንም ክፉውንና በጎዉን ነገር የሚለይ ሰው በሃገሩ ላይ የሚቃጣ ማንኛዉም ጥቃት በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ በእርሱ ላይ የተደረገ ያህል ሊሰማዉ ይገባል። በዚህ ዘመን አለም ስለተሻለ ለውጥ በሚሯሯጥበት ዘመን ላይ፤ እኛ ኢትዮጵያዉያን የአፋጣኝ ግዜ የምግብ እርዳታ እየለመንን የምንኖርበት ጊዜ ሊያበቃ ይገባል። የበለፀገችና የተረጋጋች እንዲሁም ዜጎች መብቶቻቸዉ ተጠብቆ የሚኖሩባት ኢትዮጵያን መፍጠር የምንችለዉ የወያኔን መንግስት በቃ ብለን ከስልጣን ስናወርድ ብቻ ነዉ። ይህንንም ማድረግ የምንችለዉ ራሳችንን ለለውጥ ስናዘጋጅ ነዉ። ለውጥ ናፋቂ ህዝብ ምን ማድረግ እንዳለበት ከዮክሬን ህዝብ ብዙ መማር ይቻላል። ስለዚህ ሁላችንም በተያያዝነዉ የትግል ጎዳና ላይ የነገይቱን የተሻለች ኢትዮጵያን እያሰብን አንድነታችንን አጠናክረን መቀጠል አለብ
ሞት ለወያኔ! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
በተስፋየ ታደሰ (ኖርዌይ)

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”