የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ “የረዳት አብራሪው አኩሪ ገድል የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃ እስኪወ

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ “የረዳት አብራሪው አኩሪ ገድል የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃ እስኪወ

Unread post by zeru » 20 Feb 2014 17:20

“የወጣት ሃይለመድህን አበራ አኩሪ ገድል የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነትእውን እስኪሆን ድረስ ይቀጥላል” ሲል የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ ለአለም ህብረተሰብ ያስተጋባው መልዕክት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድምፅን ነውና፤ አላማና ተግባሩም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ምኞትና ፍላጎት መሆኑን በፅኑ ያምናል” ብሏል። በተጫምሪም አኩሪ ተግባር ፈጽሟል ላለው ለረዳት አብራሪው የንቅናቄው የክብር አባል እንዲሆን የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡ ሙሉ መግለጫው ከምስክር ወረቀቱ በታች እንደወረደ እንደሚከተለው ተስተናግዷል።
“የወያኔ/ኢህአዴግ ጨቋኝ ሥርዓት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ቁጥር ስፍር የሌላቸው አፋኝ ህጎችን በመጫን፤ እንዳሻው ንጹሃን ዜጎችን መጥፎ ስም በመስጠት፤ ባልሰሩት ሃጥያትና በተፈበረከ የሃሰት ወያኔያዊ ውንጀላ በየእስር ቤቱ እንዲማቅቁ እያደረገ መሆኑ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ግልጽ ነው። ይህ አፋኝ ሥርዓት የምንወዳት ሃገራችን ኢትዮጵያንና ህዝቧን የማጥፋት እኩይ አላማ ሰንቆ፤ ምሁራን ዜጎች ለሚወዷት ሃገራቸውና ለሚሳሱለት ህዝባቸው የበኩላቸውን ማበርከት እንዳይችሉ፤ በተለይ ወጣት ምሁራን በሃገራቸው ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ተሳተፊ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ግድያ፣ እንግልት፣ ጭቆና፣ በደልና፣ ወከባ እያደረገ ይገኛል።
ይህ ፋሽስት ሥርዓት በዘረጋው አፋኝ መዋቅር ህዝብ እርስ በርሱ በጥርጣሬ እንዲኖር፤ ቤተሰብ ከቤተሰብ እንዳይተማመን፤ አንዱ ብሄር በሌላው ብሄር ላይ ጥላቻ እንዲኖረውና፤ አንዱ ሃይማኖት ከሌላው ሃይማኖት ጋር በፍቅር፣ በመተሳሰብና፣ በመቻቻል እንዳይኖር፤ ባጠቃላይ በሃገሪቷ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር፤ ብሎም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከምድረገጽ ፈፅሞ ለማጥፋት፤ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም
ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”