ባለ532 ብር ደመወዝተኛው የሕወሓት ታጋይ ከ10 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ሃብት ማግበስበሱ ተሰማ

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ባለ532 ብር ደመወዝተኛው የሕወሓት ታጋይ ከ10 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ሃብት ማግበስበሱ ተሰማ

Unread post by zeru » 11 Feb 2014 19:50

የደህንነት ሃላፊ ከነበሩት ከአቶ ወልደስላሴ ወልደ ሚካኤል ጋር በግብረ-አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዮች ከደሞዛቸው ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን ሃብት አግበሰው መገኘታቸው ታውቋል።
በተለያዩ አለመግባባቶች የተነሳ እየተመሰረቱ ያሉ ክሶች የህወሃት ተጋዮች በህገወጥ መንገድ የሰበሰቡትን የሃብት መጠን ለማወቅ እየረዳ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን ከአቶ ወልደስላሴ ጋር በግብረ አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዩ የአቶ ወልደስላሴ ወንድም አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ የመከላከያ ሚኒስቴርን ሲለቁ በመጨረሻ ይከፈላቸው የነበረው ወርሃዊ ደሞዝ 532 ብር ብቻ እንደነበር አመልክቷል ፡፡ ይሁንና፣ ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ባደረገው ማጣራት ግለሰቡ በተለያዩ ባንኮች በስማቸው 5 ሚሊዮን ብር ከማስቀመጣቸውም በተጨማሪ፣ አዲስ አበባ ቤቴል ሆስፒታል አካባቢ በ74 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታ እያካሄዱ ፣ በአፋር ክልል ደግሞ ከ1 ሚሊዮን 400 መቶ ሽ ብር በላይ በሆነ ወጪ የእርሻ ኢንቨስትምንት እያከናወኑ መሆናቸው እንዲሁም በስማቸው 2 ሚሊዮን 700 ሺ ብር ግምት ያላቸው 2 ሎደር መኪኖች መገኘታቸውን ገልጽዋል።
የአቶ ወልደስላሴ እህት የሆኑት ወ/ሮ ትርሃስ ደግሞ የ8ኛ ክፍል ተማሪና ምንም ስራ ያልበራቸው ሲሆን፣ በወንድሞቻቸው ድጋፍ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዛ አንድ ስካቫተር፣መኪና እንዲሁም በአዲስ አበባ በየካና ቦሌ ክፍለ ከተሞች፣ በለገጣፎ፣ መቀሌና አክሱም 3 ሺ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስማቸው መገኘቱ ተመልክታል ፣እንዲሁም በተለያዩ ባንኮችም 8 ሚሊዮን ብር ተቀማጭ ማድረጋቸውን አንድ ተጨማሪ ዘመናዊ
ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”