የሁለት ሺ ሰባት ምርጫ ወዴት ይመራናል?

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

የሁለት ሺ ሰባት ምርጫ ወዴት ይመራናል?

Unread post by zeru » 11 Feb 2014 19:38

Image
ግርማ ሠይፉ ማሩ
በኢህአዴግ መንደር የምርጫ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየት ጀምረዋል፡፡ የምርጫ ቦርድ በገዢው ሰፈር ሁሉ ነገር መጠናቀቁ ጥቅሻ ሲሰጠው እንቅስቃሴ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የምርጫ ዘመቻው በተቃዋሚ ጎራ እንደምንፈልገው ነፃ፣ ፍትሓዊ እና ሁሉም ተወዳዳሪ እኩል በተዘጋጀ ሜዳ ይሆናል ማለት ከባድ ሊሆን እንደሚችል ከአሁኑ መገመት ለዝግጅት የሚረዳ ይመስለኛ፡፡ ኢህአዴግ ከጅምሩ የመጫወቻ ሜዳውን ብቻ ሳይሆን አጫዋቾችን ሁሉ ተቆጣጥሮ ጨዋታው እንዲጀመር መፈለጉን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየት ጀምረዋል፡፡ በዚህ ወቅት የመንግሰት አካላት የሆኑት ህግ አውጭውም ሆነ አሰፈፃሚውም በዚህ ጉዳይ ላይ ተጠምደው ነው የሚገኙት፡፡ እንደ አሰፈላጊነቱም የፍትህ ስርዓቱ ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ካለን ልምድ በመነሳት ይህ ከግምት በላይ ነው፡፡

ህግ አውጭው ማለትም ምክር ቤቱ ውስጥ የሚገኙት ሰዎች በምርጫ የሚሰየሙ ስለሆኑ በዋነኝነት ተግተው ለቀጣይ አምስት ዓመት በምክር ቤት በመቆየት የአዲስ አበባ ኑሮን ማጣጣም ይፈልጋሉ፤ ይህን ሀቅ መካድ አይቻለም፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው በኮንዶሚኒየም ስርዓት ውስጥ ቅድሚያ ለማግኘት ብዙ ሙከራዎች ይደረጋሉ፤ በቀጣዩ ካልተመረጡ ወደ መረጣቸው ህዝብ ተመልሰው በሌላ መስክ ለማገልገል ዝግጁ የሆኑት በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ አስፈፃሚውም ቢሆን በቀጣይ በገዢነት ለመቆየት ቆርጦ የተነሳ ነው የሚመስለው፡፡ ስለዚህ አስፈፃሚው የሚያወጣውን ምርጫ መተግበሪያ እቅድ ነፃ ፍትዊ ይሁን ብሎ የሚከላከል አይኖርም፡፡ ይልቁንም የሚጠበቀው ተባብሮ በቁርጠኝነት መተግበር ነው፡፡ ከዚህ ዘለግ አድርገን ስናስብ ደግሞ አስፈፃሚው የሚያስበው የኢህአዴግ ዕጮዎችን ብቻ ሳይሆን በተቃዋሚ ጎራ ማን? እንዴት? መወዳደር እንዳለበት ሁሉ የመወስን ፍላጎት አላቸው፡፡ ለዚህ ጉዳይ ፓርቲዎችን አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ የሆኑ በአሁኑ አጠራር ልማታዊና ዲሞክራሲ አመለካከት ያላቸው፤ ከዚህ ውጭ ኒዎ ሊብራል ቢሆንም በኢህአዴግ እይታ ፅንፈኛ አይደሉም የሚባሉት ብቻ ቢወዳደሩ እና ለአበዳሪዎቻቸው እና ዕርዳታ ሰጪዎች ማስመሰያ ቢሆኑ ደስ ይላቸዋል፡፡ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት አለ እንዲባል ይህ ቻይናን እና መሰሎቿን አይጨምርም፡፡ በዚህ ጉዳይ ኢህአዴግ ማፈር ትቶዋል፡፡ ኢህአዴግ አውራ ፓርቲ የሆነው ተቃዋሚዎች ሰራቸውን ስለማይስሩ ነው ብሎ ማውራትና ማስወራት ጀምሮዋል፡፡ ተገደን ነው ውስኪ የለመድነው አሉ የደርግ ባለስልጣናት ይባል ነበር፡፡ ኢህዴግም ተገዶ አውራ ፓርቲ ሆኖዋል፡፡ አንግዲህ በዚህ ዓይነት ድባብ ውስጥ ነው የሁለት ሺ ሁለት ምርጫ የሚካሄደው፡፡ ምርጫ መወዳደር ካለብን ይህን ሁሉ ተረድተን ነው፡፡ ምን እናድርግ? ብለን ማስብ የሚኖርብን ይመስለኛል፡፡
በኢህአዴግ በኩል ለምርጫ ዘመቻ በእቅድ የተያዙት ዋና ዋና ተግባራት ይህችን ሀገር ሊመሩ ይችላሉ የሚባሉ ምርጥ ምርጥ ካቢኔ እና የምክር ቤት አባላትን በማቅረብና በይፋ በማስገምገም አይደለም፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ይህችን ሀገር በቁንጮነት የሚመራትን ሰው ለመምረጥ ዕድል የለንም አንድ ወረዳ የመረጠልንን ሀገር እንዲመራ ከመጋረጃ ጀርባ በሚዶልቱ ሰዎች ዕድል ይሰጠዋል፡፡ በነገራችሁ ላይ ኢህአዴግ ትንንሽ አባላቱን በወረዳ ደረጃ ያስገመግማል፡፡ ኢህአዴግ ምርጫ ማሸነፍ የሚፈልገው በብቃቱ አይደለም፡፡ ይልቁንም ለዚህ ጉዳይ ጉልዕ ሚና ይጫወታሉ ብሎ ያመነባቸውን አካላት በማሸማቀቅ እና አንገት በማስደፋት ነው፡፡ ከዚህ በዘለለም የፓርቲው ያልሆኑ በመንግሰት ኃላፊነት የተከናወኑ ተግባራትን ለምርጫ ዘመቻ በማቅረብ ነው፡፡ እነዚህን በትንሽ በትንሹ መመልከት እንችላለን፡፡

ቀዳሚው ተግባር ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በፀረ ሰላም ሀይልነት መፈረጅ ለዚህም “የፀረ ሽብር ህጉን” እንደመሳሪያ በመጠቀም ቅስቀሳዎችን ማድረግ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ከፊት በማስቀደም ተቃዋሚዎችን በፅንፈኝነት መፈረጅ ሲሆን ተቃዋሚዎች ለዚህ ምላሽ መስጠት እንዳይችሉ ሚዲያ መከልከል፡፡ ከተቻለ የተወሰኑ አስተያየቶችን እንዲሰጡ በማድረግ እየቆረጡ ማቅረብ ናቸው፡፡

ለምሳሌ አሽባሪነት በተመለከተ ፓርቲዎች በይፋ የያዙት አቋም እና ፕሮግራማቸው ላይ ያስቀመጡትን ግልፅ አቅጣጫ ወደ ጎን በመተው ኦነግና ኢህአዴግ አብረው ሀገር ሲመሩ የተፈፀሙ ወንጀሎችን በፊልማ በማሳየት የሽብር ስራ ነው በማለት ድራማ እየሰሩ ከዚህ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ፓርቲዎች የሚወነጅልበት ፕሮፓጋንዳ ይሰራሉ፡፡ እን አንዱዓለምን ከእንዲህ ዓይነት እኩይ ተጋባሮች ጋር በማገናኘት ሌሎች የፓረቲ አመራሮቸን ተጠንቀቁ ማለት አንዱ በመተግበር ላይ ያለ ዕቅድ ነው፡፡ ሲከፋም ህዝቡ መምረጥ የሚገባው የሰላም ሀይል የሆነውን ኢህአዴግን ወይም ፀረ ሰላም የሆኑትን ተቃዋሚዎች ብሎ የተሳሳተ ምርጫ ያቀርባል፡፡ ይህን እውነት ለማስመሰል ሚዲያውን በህገወጥ መንገድ ይጠቀማሉ፣ ሚዲያውም መደበኛ ሰራው አድርጎት እየሰራው ይገኛል፡፡

ለተቃዋሚዎች ኢህአዴግና መንግሰት ተለይተው እንደ ፓርቲ መወዳደር ካልጀመሩ ምርጫ የተወሰኑ ወንበሮች ከማግኘት በዘለለ የስልጣን መያዣ መንገድ መሆኑ እያከተመ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መስመር ነው፡፡ መድበለ ፓርቲ ስርዓት ለገዢው ፓርቲ እንደ መታጠቢያ ቤት መስታውት ፊትን መመልከቻ ሆኖ ማገልግል ነው፡፡ ይህን ዕቅድ ተግባራዊ እንዳያደርጉ ተቃዋሚዎች ከምንግዚውም በላይ ከህዝቡ ጋር በመሆን ማክሸፍ የግድ ይላል፡፡ በቀጣይ ዓመት ምርጫ ኢህአዴግ እንደ ከዚህ ቀደሙ በሙሰሊም ማህበረሰብ ድጋፍ ላይ ስለማይተማመን አሁን በከፍተኛ ደረጃ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮችን ስጋት ውስጥ በመክተት ድምፃቸውን ለኢህአዴግ ድምፅ እንዲሰጡ ማድረግ አንዱ እቅድ ነው፡፡
ለተጨማሪ ምንባብ ይህን ይጫኑ

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”