ለ22 አመታት የዘለቀው የህወሀት ኢህአዴግ የግፍ አገዛዝ ዛሬም እንደትላንቱ እድሜውን ለማራዘም

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ለ22 አመታት የዘለቀው የህወሀት ኢህአዴግ የግፍ አገዛዝ ዛሬም እንደትላንቱ እድሜውን ለማራዘም

Unread post by zeru » 30 Jan 2014 23:26

ለ22 አመታት የዘለቀው የህወሀት ኢህአዴግ የግፍ አገዛዝ ዛሬም እንደትላንቱ እድሜውን ለማራዘም ያፈና ተጋባሩን ቀጥሎበታል።
ባለፉት ሳምንታት እና ጥቂት ወራት ብቻ አሳፋሪ በሆነ መልኩ በአረና ፓርቲ አባላት ላይ ድብደባ እና አሰጸያፊ ተግባር ተፈጽሟል። ለምሳሌም ባለፈው ሳምንት ማለትም በጥር 16 ቀን 2006 ዓ/ም በኣቶ ኣስገደ ገ/ስላሴ፣ ኣቶ ኣብርሃ ደስታ፣ አቶ አንዶም ፤ መምህር ፍፁም ግሩም፣ ገዛኢ ንጉሰ እና ሌሎችም የአረና አባላት ላይ በዓዲግራት ከተማ ድብደባ እና አስጸያፊ የሆነ ተራ የዱርየ ምግባርን የሚያንጸባርቅ ክብረነክ ተግባር ተፈጽሞባቸዋል፡፡
ይህ የሆነው የአረና አባላት የገዥው ቡድን የማስፈራራት ዘመቻ ሳይበግራቸው ስርአቱ በመፈጽም ላይ ያለውን ግፍ እና በደል ለትግራይ ህዝብ ለማሰማት የሚያደርጉትን ተጋድሎ ለማጨናገፍ ነው። እጅግ አሳፋሪ የሆነው ጉዳይ ደግሞ፣ ገዥው ቡድን ለዚህ እኩይ ተግባሩ ህጻናትን በማሰማራት የአረናን አባላት በመከታተል እንዲሰድቡ፣ እንዲደበድቡና ተመሳሳይ አሳፋሪ ተግባር እንዲፈጽሙ ማድረጉ ነው።
ኢትዮጵያዊ ባህላችን ህጻናት ታላቆቻቸውን እንደ ወላጆቻቸው አክብረው እንዲያዩ ያስተምራል። ገዥው ቡድን ህጻናትን በዚህ አይነቱ እጅግ ዝቅ ያለ አሳፋሪ ምግባር ውስጥ እንዲሳተፉ ማድረጉ፣ ለአካባቢውም ሆነ ባጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባህል ምን ያህል ግድ የሌለው እንደሆነ ያሳያል። በተጨማሪም ገዥው ቡድን ከርሱ የተለየ ሀሳብ ያላቸውን ለማኮላሽት ምን ያህል እንደሚጓዝና በአሁኑ ሳአትም ምን ያህል የሚይዘውና የሚጨብጠው እየጠፋበት እንደሆነ ያመለክታል።…
ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”