በቦረና በተነሳ የጎሳ ግጭት ከ8 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ሲያጡ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም፤

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

በቦረና በተነሳ የጎሳ ግጭት ከ8 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ሲያጡ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም፤

Unread post by zeru » 27 Jan 2014 20:21

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን መልካ ሶዳ ወረዳ ኩሮ ነጌሌ ቀበሌ በቦረና እና በጉጂ ኦሮሞ ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት ከ8 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማጣታቸውን የፍኖት ነፃነት ምንጮች አስታወቁ፡፡ የመከላከያ ሰራዊቱ ምንም አይነት የማረጋጋት እርምጃ አለመውሰዱ ጉዳቱን እንዳባባሰውም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡
የአካባቢው የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንዳስታወቁት ለጊዜው መነሻው ባልታወቀ ምክንያት ጥር 17 ቀን 2006 ዓ.ም በተነሳ የሁለቱ የኦሮሞ ጎሳዎች ግጭት ከስምንት በላይ ሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በርካታ ሰዎች የገቡበት አልታወቀም፡፡
የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ወደ አካባቢው በመደወል ባደረገው ማጣራት በአካባቢው በስፋት ሚንቀሳቀሰው የመከላከያ ሰራዊት አንዳችም የማረጋጋት እርምጃ ባለመውሰዱ በግጭቱ የደረሰው ጉዳት መባባሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግጭቱ የቆመ ቢመስልም ሁለቱም ጎሳዎች ከግጭቱ አካባቢ ንብረቶቻቸውን በማሸሽ ለሌላ ጦርነት መዘጋጀታቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ጨምረው ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት “ባለፉት 22 አመታት በየጊዜው በአካባቢው ያለው የግጭት መጠን የመጨመር አቅጣጫ ማሳየቱ መንግስት የሚከተለው ፖሊሲ ውጤት ነው” የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች “የሀገሪቱ የመከላለያ ሰራዊት አንድም ጊዜ የማስታረቅም ሆነ ግጭቱን የማርገብ እርምጃ አለመውሰዱ አስገራሚ ነው፡፡”
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አካባቢው ወደ ግጭት ቀጠናነት እየተለወጠ በመምጣቱ በጉጂና በቦረና ኦሮሞዎች፣ በጉጂ ኦሮሞና በቡርጂ፣ በኮንሶ ና በቦረና፣በጉጂና በአማሮ እንዲሁም በአካባቢው ባሉ ሌሎች ብሄሮች መካከል በየጊዜው ግጭቶች እየተከሰቱ በሰው ህይወት፣ በአካልና
ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ


Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”