“የትግራይ ሕዝብ በአንድ ቤተሰባዊ ቡድን ለሚመራ ድርጅት በንብረትነት ለማገልገል የተፈጠረ ሕዝብ

ፖለቲካ ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች
Politics , Current affairs
User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

“የትግራይ ሕዝብ በአንድ ቤተሰባዊ ቡድን ለሚመራ ድርጅት በንብረትነት ለማገልገል የተፈጠረ ሕዝብ

Unread post by zeru » 27 Jan 2014 20:15

ሰሞኑን በትግራይ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ከየመንደሩ የተውጣጡ ነብሰ ገዳይ፣ ስብሰባ በታኝና አፋኝ የዱዬ ቡድኖችን በተለያየ መልኩ በማደራጀት በአረና ትግራይ አባላትና አመራር ላይ የከፈቱትን አዲስ የመንጥርና የድብደባ ዘመቻን አስመልክቶ በዲያስፖራ የአረና ትግራይ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ ድርጊቱን አወገዘ።
“ትግራይ እንደነ አሉላ አባ ነጋና ዮሐንስ የመሳሰሉ የብዙ ጀግኖች ዓፅም የተቀበረባትና አኩሪ ታሪክ ያላት ምድር ብትሆንም ዛሬ ህዝብዋ በአንድ ቤተሰባዊ ቡድን ለሚመራ ፓለቲካዊ ድርጅት በሞኖፓልና በንብረትነት ለማገልገል የተፈጠረ ህዝብ አድርገው በመቁጠር እንደ ህፃን ልጅ አፍህን ያዝ እየተባለ በካድሬ ዱላ እየተኰረኰመ ሲኖር ማየች እጅግ የሚያሳዝን የታሪክ ጠባሳ ነው።” የሚለው ይኸው መግለጫ “ስለሆነም ህወሓት በህዝቡም ሆነ የተለየ አመለካከት ይዘው በሚንቀሳቀሱ ወገኖቻችን ላይ የሚያካሂደው የስነ ልቦናና የአክል ጥቃት የዲሞክራሲ መርህ የሚፃረር ኢ ሰብኣዊ ተግባር ብቻ ሳይሆን የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ ሕገ ወጥ ተግባር ስለሆነ ድርጊቱን እናወግዛን።” ብሏል።
“ህወሓት/ኢሕአዴግ በትረ ስልጣኑን ከተጎናፀፈና ካደላደለ ወዲህ ከሱ የተለየ አመለካከትና ሃሳብ ያላቸው ወገኖች ሁሉ የተለያዩ ቀለማ ቀለሞችን በመቅባት፣ የፈጠራ ስም በመለጠፍና ሰበብ አስባብ በመፈለግ በቀጥታም ሆነ በረቀቀ መንገድ የመመንጠር፣ የማፅዳት፣ የመሰወር፣ የማሰር፣ የመግደልና እርስ በርስ የማናቆር ስራ ዋነኛ የስርዓቱን ባህርይ መገለጫ ሆኖ መቆየቱ እሙን ነው።” ያለው የአረና ደጋፊዎች መግለጫ “የእርምጃው ዋናው ምክንያትም እውነት ተቃዋሚዎቹ የሀገርና የህዝብ …
ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ

Post Reply

Return to “Ethio Politics .... ኢትዮ ፖለቲካ”