-------------------------------------------------------------------------------------------
‹‹አራተኛው የአለም ጦርነት በወንዶችና በሴቶች መካከል ይሆን››
-------------------------------------------------------------------------------------------
ከማያውቋት ሴት ጋር ድንገት ለመግባባት እንደምን ይቻላል...ለሚል ስንልቦናዊ ጥያቄም ሐበሻዊ የሆነ መለማመጃ አጋጣሚም ነው፡፡
ለምሳሌ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ቢገጥመንስ እንደሚከተለው አይነት፣
‹‹እህት...››
‹‹እኔን ነው››
‹‹እጎኔ ካንቺ ሌላ ሰው የለ! ሌላ ማንን ሊሆን ይችላል! አትኮሳተሪያ!››
‹‹ብኮሳተር በግንባሬ ነው፤ምን አገባህ!››
‹‹እስካሁን በርግጥ አላገባሁም!! ባገባም ያው ምን ይጠየቃል ሚስት...ሴት ነው የማገባው፡፡››
‹‹ላማንኛውም ምን ፈልገህ ነው የጠራኸኝ››
‹‹አውቃሸለው ልበል››
‹‹አዎን››
‹‹የት ነበር የማውቅሽ››
‹‹እዚህ ነዋ! አሁን!››
‹‹የምትገርሚ ነሽ!!...የሆኖ ሆኖ ሰአት ስንት ነው ባክሽ››
‹‹ሰአት...ነጋዴ እመስላለሁ እንዴ!››
‹‹...ማለቴ...››
የተንቀሳቃሽ ስልኳን ታወጣለች፡፡ ከአሁን አሁን ነገረችኝ ብለህ ስትጠብቅ፤ውጭ ውጭውን እያየች ጥፍሯን ብጥርሶቿ መቀረጣጠፍ ትያያዘዋለች፡፡ አንት ደግሞ ወንድ ነህ ቆመህ የምትሸና ወንድ እልህ ይይዝሃል፡፡ እልህ ጥያቄውን ደግመህ እንድትጠይቅ ግድ ይላሃል፤ደግመህ ጥጠይቃለህ...
‹‹እህት...››
‹‹እኔን ነው››
ከንፈርህን አስረህ በአፍንጫ በኩል ቡፍ! የሚል ሳቅ ትስቅና....
‹‹ማስለመንሽ ነው ማለት ነው››
‹‹ምኑን››
‹‹ሰዐት መንገሩን፡፡››
‹‹ሰ.ዐ.ት..ብዙ ነው!››
ትልና ጊዜን እረሷ ትቀምር ይመስል ሰዐት መናገር ጎሮሮዋ ላይ ዳገት ይሆንባታል፡፡ በዚህ መሃል ዐይኗን ባለፀጉራማ ክንድህ ላይ ሲንከራተት ጥይዘዋለህ፤...ግራ እጅህ ላይ ቋጥኝ የሚያህል ሲቲዝን ሰዐት አስረህ ኖሯል፡፡ ኩምታ...እፍረት ያሸማቅቅሃል፡፡ እንኳንም አሸማቀቀህ ስንትና ስንት መነጋጋሪያ አጀንዳ እያለ ጥንት አያቶችህ የተጠቀሙበትን መጥበሽያ ሳይሆን ማድረቂያ፤ለኮምፒውተር ዘመን እህቶች ማን ተጠቀም አለህ!...አሁን የማርትሬዛ ብር ይዞ ፒያሳ መሀል ካሉ ቡቲኮች ስሪ-ፒስ ምናምን መግዛት ይቻላል!...አይቻልምኮ ወንድሜ...እናም ታክሲ ነው...ማን የት ያውቀኛል...አሁን ስንወርድ እንረሳሳ የለም ውይ ብለህ ምላስህ ያመጣልህን ዝም ብለህ አትቀባጥር...ትልሃለች የማታውቅህ እህትህ...
ያሬዳዊ
የወንዶች ጉዳይ
Forum rules
NO Rated R Pictures! please.
NO Rated R Pictures! please.

-
- ጀማሪ Starter
- Posts: 10
- Joined: 08 Oct 2009 18:40
- Contact:
Re: የወንዶች ጉዳይ
arif newu