እንቆቅልሽ ተረትና፣ ምሳሌ...

Love, Relationship, Habesha intimate, Ethiopian girls,
ፍቅር ፣ ጋብቻ :ጉዋደኝነት: እንተዋወቅ:
Forum rules
NO Rated R Pictures! please. :)
Post Reply
User avatar
ሰላም
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 9
Joined: 27 Oct 2009 17:07
Contact:

እንቆቅልሽ ተረትና፣ ምሳሌ...

Unread post by ሰላም » 02 Nov 2009 14:56

የልጃገረድ አውታታ
አውራ መንገድ ላይ ተኝታ
ተይ ተነሽ ቢላት ምነው
ይህ አለማፈር ነው.. :lol:

እንቆቅልሽ....
ሰገባ ወደ ውጭ
ሲወጣ ወደ ደጅ?

:lol:ለፈገግታ :lol
ያባይን ልጅ ዲቪ ደረሰው
ስም ያለው በ ኪሎ ይሽጠው
ሰውን ማመን ተፈራርሞ ነው
እኔ ከሞትኩ ትንሹው ቴፕ ለእናቴ
ሰርገኛ መጣ ልብስ ቀይሩ
አሳን መብላት ጠብሶ ነው
ጋደኛክ ሲታማ አንተ ምን አገባክ
ከዝንጀሮ ቆንጆ የድመት አስቀያሚ ይሻላል :lol: :lol:

User avatar
ሰላም
ጀማሪ Starter
ጀማሪ Starter
Posts: 9
Joined: 27 Oct 2009 17:07
Contact:

Re: እንቆቅልሽ ተረትና፣ ምሳሊ...

Unread post by ሰላም » 02 Nov 2009 15:04

መሸ ደሞ አምባ ልውጣ

አምባ ወጥቼ እኩለ-ሌሊት ፥ ስለት ገብቼ በስሟ
ከርሞ ሰይጣን በሷ አስቶኝ ፡ ልገላገል ከሕመሟ
ጠበሏ አፋፍ በጨረቃ ፥ ደጋግሜ ማሕሌት ቆሜ
ሆዴ ቃትቶ ባር ባር ብሎ ፥ እርቃኔን ከሷ ታድሜ
ደጀ ሰላሟን በአራት እግር ፥ ተንበርክኬ ተሳልሜ
በሥጋዬ እሚነደውን ፥ በጸሎት ላቤ አጣጥሜ
እፎይ ብዬ አመስግኜ ፥ ውዳሴዋን ደጋግሜ . . . .
ገና ከደጅዋ እልፍ ሳልል ፥ ደሞ ይምጣ የቁም ሕልሜ?
ሌት በጥምቀቷ የነጣው ፥ ነጋ ደፈረሰ ደሜ ።
ለሷ እንጂ ለኔ አልያዘኝ ፥ አዬ የስለት አታምጣ !
በውጣ ውረድ በጠበል ፥ ባሣር ወዜ ቢገረጣ
ልክፍቷ እንደሁ አልለቀቀኝ ፥ መሸ ደሞ አምባ ልውጣ ! :lol: :lol:
:D :D
ባዶ መሶብ

ባንበሳ ብሂል ተጀግኖ
ዘራፍ ብሎ ፣ ሰብቆ ገድሎ
ጉራ ገኖ ፣ ዳቦ አክሎ
ገድል ሆኖ ፣ ሞልቶ መሶብ
ታሪክ ጠግቦ ፣ ቀርቶ ማሰብ
የእድሜ አተላ ፣ ግቶ አግቶ
ባዶ መሶብ ፣ ላይ ተኝቶ፡፡

Post Reply

Return to “Ethio Love ...ኢትዮ ፍቅር”