Aባ ጃሌው!

Love, Relationship, Habesha intimate, Ethiopian girls,
ፍቅር ፣ ጋብቻ :ጉዋደኝነት: እንተዋወቅ:
Forum rules
NO Rated R Pictures! please. :)
User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Aባ ጃሌው!

Unread post by selam » 13 Oct 2009 20:54

Aባ ጃሌው!
“ክፉውን በክፉ Aትቃወሙት፣ ግራው ፊትህን ለሚመታህ የቀኙን ስጠው… ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ የሚረግሟችሁን መርቁ…!”
ማቴ፡ 5፡ 39 ፤ ሉቃ፣ 6፡ 27-28

Aባ ጃሌው በሰፈራቸው ከታወቁና Aሉ ከሚባሉት ሽማግሌዎች ሲሆኑ በጣም የተከበሩ ሰው ናቸው። የሰፈሩ ሰው ማንኛውም ጉዳይ ሲኖረው ሁሌ የሚጠራው Eርሳቸውን ሲሆን፣ ለምሳሌ ለሚስት Aማጭ ሰው ሲፈለግ Eርሳቸውን ለምኖ ከሽማግሌዎቹ መሃል ካስገባ፣ ተጠያቂው Eምቢ ብሎ መመለስ በጣም ይከብደዋል። ለዚህም ሁሌ ይቀናቸዋል፣ ጉዳዩም ቶሎ ይፈጸማል። በመሬት ሆነ በገንዘብ የተጣላውን ለመሸምገል ዘወትር ሰዉ ሁሉ የሚጠራው Aባ ጃሌን ነው። ባልና ሚስትም ሲጣሉ ዋና Aስታራቂ ከAባ ጃሌው የተሻለ ሌላ የለም? ስለዚህ Aባ ጃሌው የኅብረ ሰቡ ዋና ማገርና ምሰሶ ናቸው ቢባል ከሓቁ የራቀ Aይሆንም።
Aባ ጃሌው Eድሜያቸው በትክክል ባይታወቅም፣ Aሁን Eያረጁ ወደ ዘጠና ዓመት Eንደ ተጠጉ ይገመታል። ጥልቅ Aስተዋይነታቸውና ብልኅነታቸው የታወቀው ገና ድሮ ሲሆን፣ ያኔ የዓርባ ዓመት Eድሜ ያህል Eንኳን የነበራቸው Aይመስሉም ነበር። በሰፈሩ ሰርግ ሆኖ Aሳላፊ Eንዲሆኑ ተመድበው፣ የመጣውን Eንግዳ Eየተቀበሉ ከዳስ ሲያቀምጡና ሲያስተናግዱ፣ Aንዱ ጠጥቶ ሞቅ ያለው በሰፈሩ የታወቀ ልክስክስ፣ በሆነ ነግር ተላከፋቸውና ግርግር ፈጠረ። ሴቶች ወደሚሠሩበት ወጥ ቤትም ካላለፍኩ Eያለ፣ ተው Aይሆንም ሲሉት፣ ግልፍ ብሎ ዞር Aለና በቃሪያ ጥፊ ጆሮAቸውን Aጮላቸው። በዳሱም ሰዉ ሁሉም “O!’ ብሎ ደነገጠ።
Aባ ጃሌው ፈጽሞ ያልጠበቁት ነገር ነበር፣ ግን የቁጣ ቃል ሳይናገሩ፣ ፊታቸውን ሳያጠቁሩ፣ ድምፃቸውንም ሰበር ሳያደርጉ፣ ሰውየውን፤ “ና፣ ወንደሜ፣ ግድ የለህም፣ Aይዞህ፣ የማጫውትህ Aንድ ጉዳይ Aለኝ፣ ና Eማ!” Eያሉ Eጁን Aጥብቀው ይዘው ውጭ Aወጡትና Aጋፋሪዎቹን፤ “ስካሩ Eስኪበርድለት Eንዳይገባ!” ብለው ከዳስ ተመልሰው ገብተው፣ Aንዲትም Eንዳልሆነ ሰው የAሰላፊነታቸውን ተግባር በሚገባ ቀጠሉ።
Aባ ጃሌ ረጋ ያለው ባሕሪያቸው ከዚያ በፊት በሰፈሩ ቢታወቅም Eንኳ በይበልጥ Aንጸባርቆ ለሰዉ ሁሉ የታየው በዚያን ጊዜ ነው። ሰው ጠጋ Eያለ፣ “Aባ ጃሌው፣ Eንዴት Aስቻልዎት? Eጅግ የሚደንቁ ትEግስተኛ ሰው ነዎት!” ሲላቸው፣ “ይህንን ካልቻልኩማ ለAሰላፊነት የማልበቃ ሰው
ነኛ! መቻል Aለብኝ Eንጂ! Eርሱ መች መታኝ፣ የመታኝ ጠላው፣ ወይ ጠጁ Eንጂ Eርሱ Aልመታኝም።” Eያሉ ነው Aሳስቀው የመለሱላቸው።

“Aባ ጃሌው” ሊባሉ የቻሉት በሰፈሩ ሰው Aጠራር Eንጂ ትክክለኛው ስማቸውስ Aያሌው ነበር። ከሰፈሩ Aሮጊቶች Aንዷ፣ ፊዴል Eንኳን ያልቆጠሩት፣ Eማሆይ ወለተ-ጽዮን የሚባሉት Aንድ ቀን፤ “Aባ Aያሌው” ለማለት፤ “Aባ ጃሌው!” ብለው ሲጠሯቸው፣ ከዚያን ጊዜ ወዲያ ሁሉም ተቀብሎ፣ ስማቸውን ከAባ Aያሌው ወደ Aባ ጃሌው ለወጠው። በልጅነት የወጣላቸው ትክክለኛው ስማቸው ተረስቷል። ዛሬ ይኸው በሰፈሩ ሁሉ “Aባ ጃሌው” በሚል መጠሪያ ስም ብቻ ነው የሚታወቁት።
Aባ ጃሌው ያደጉት በባላገር ገበሬ ሆነው ቢሆንም፣ ልጆቼን ላስተምር ብለው ወደ Aውራጃው ከተማ ከተዘዋወሩ ብዙ ዓመታት Aልፏቸዋል። የEርሻው መሬታቸውንም ለባለ ሢሶ ገበሬ ሰጥተውት፣ በየዓመቱ በAህያ ጥቂት ዳውላ ገብስ፣ በቆሎና፣ ማሽላም Eየተጫነ ይመጣላቸዋል። ከዚህ ለቤታቸው የሚበቃቸውን Aስቀርተው፣ ‘ገበያ ደህና ውሏል’ ሲባል ከተማ ወርደው ለቸርቻሪ ነጋዴ ሸጠው ይገላገላሉ። ሌሎች ራሳቸው ከገበያ የሚቸረችሩ ሰዎች፤ “ለነጋዴ ከምትሰጥ ራስህ ብትቸረችረው የተሻለ ገቢ Eኮ ታገኛለህ…” ሲሏቸው፣ “ቸርቻሪውስ ምን ይብላ!” ነው የሚሉት። ዋናው ምክንያት ግን ከገበያ ቆመው ከAላፊ Aግዳሚው በዋጋ ውጣ-ውረድ የEንካ ስላንትያ ትንንቅ መያያዙን Aልፈለጉትም።
Aባ ጃሌው በኑሮAቸውም ሁሉ ረጋ ብሎ መመላለስን የሚወዱ ሰው ናቸው። Aንድ-Aንድ Aስቸጋሪ ሰው ሲያጋጥማቸው ገለል ይሉለታል፣ ወይም ከፊታቸው ገለል የሚያደርጉበትን መንገድ ይፈልጋሉ Eንጂ፣ መከራከር፣ መጨቃጨቅ፣ Eልኽ መያያዝ የሚባል ፍጹም Aይወዱም። ሊያገኙት የማይፈልጉትን ሰው ከሩቁ ሲያያዩት መንገዱን Aሳብረው ይሄዳሉ Eንጂ፣ ካልሆነ ሰው ጋር መላከፍና Aፍ መካፈትን Aይወዱም።
Aባ ጃሌውን Aሰተዋዩ AEምሯቸውና ትEግሥታቸው በሰፈሩ ሰው ሁሉ ዘንድ ታዋቂነትና ተወዳጅነትን Aትርፎላቸዋል። ስለዚህም ለሽምግልና፣ ለAማጭነት ሆነ የተጣሉትን ለማስታረቅ ሁሉም ሰው ይለምናቸዋል። ለሆነ ጉዳይ ምክር ፈላጊውም ሁሉ ከበራቸውና ከደጃፋቸው Aይጠፋም። Aባ ጃሌው በAውራጃው ከተማ Eንዲህ ቢከበሩም Eንኳን ተወልደው ባደጉበት በባላገሩ Aካበቢ ግን በወጣቶቹ ዘንድ ትዝታቸው መረሳቱ Aልቀረም። Eርግጥ ስማቸው Aልፎ-Aልፎ በAዛውንቱና በAሮጊቶቹ
ቢነሳም Eንኳን ማንነታቸው ግን ብዙም Aይታወቅም። ለዚህም ዋና ምክንያቱ ከተማ ከገቡ ብዙ ዓመታት በማለፉ ነው።
Aንድ ቀን በመኸር ወራት ታድያ መሬቱን Eንዲያርስ የሰጡት የሢሶው ገበሬ ድንገት በማታ ከተፍ ብሎ ወደ ቤት መጣ። Aባ ጃሌም፤ “ምነው ደህናም Aይደለህ? Aሁን በመኸር ጊዜ፣ ሥራ በበዛበት ወራት ከከተማ ድረስ ምን ጉዳይ ሊያመጣህ ቻለ?” ቢሉት፤ “Aረ Eኔስ ደህና ነኝ!” ብሎ ያመጣውን ጉዳይ ሳይናገር Aደረ። በማግስቱ ግን በማለዳ ተነስቶ፣ Eንደ መርዶ ነጋሪ፤ “Aስቻለው የተባለ Aንድ ጥጋበኛ ጎረምሳ ከAዙሪት ወንዝ ዳር ያለውን መሬት Aጥር Aጥሮበት ሄዷል…” Eያለ፣ Eርምዎን ያውጡ በሚል ዓይነት Aነጋገር መርዶውን Aረዳቸው።

Aባ ጃሌው ልጆቻቸውን Aሳድገው፣ ሁሉም Aዲስ Aበባ ሄደው በተለያየ መስክ በሥራ ገበታ ላይ ሲገኙ፣ ከሁሉም ታናሹ ልጃቸው ኮሌጅ ልማር ብሎ፣ ወንድሞቹ ይረዱታል። በክረምት ወራት ግን ከAባቱ ቤት Eየመጣ ያሳልፋል፣ ስለዚህ “ነገሩስ ነገር ነው፣ ግን ሰይፍ Aያማዝዝም!” Eንዲሉ፣ መሬታቸውን ማንም ጥጋበኛ Aጥር ተክሎ በመቀማቱ ቅር ቢሰኙም Eንኳ ብዙም Aልተጨነቁም። ከልጆቻቸው ማንኛውም ቢሆን ከAገር ቤት ሄዶ በግብርና የሚሰማራ Aይኖርም፣ Eርሳቸውም ከከተማው ምቾት ወጥተው ዳግም ወደ ባላገር ኑሮ Aይመለሱም። ቢሆንስ ታድያ መሬቱ የAያት፣ የቅድመ-Aያት ርስት ነውና ለቅርብ ቤተ ዘመድ ይሰጣል Eንጂ ማንም ጥጋበኛ ጐረምሳ Eንዴት ይነጥቀዋል! ነገሩ የሚከነክን ነው።
“Eስቲ ደግ ነው፣ መክሬ የማደርገውን Aደርጋለሁ። Eስከዚያው ሂድ ሌሎቹን Eርሻዎች Eያረስክ ቆይ…” ብለው የሢሶውን ገበሬ በማሰናበት፣ ነገሩን ማሰላሰል ያዙ። Eንደ ድሮ ጉልበትና ብርታት ቢኖራቸው ኖሮ ነገሩን ቶሎ ያጣድፉት ነበር፣ ዛሬ ግን Eርጅና መጣና፣ ወደ ፍርድ ቤት መመላለሱን ጠልተው፣ ጉዳዩን ለደህና ነገረ-ፈጅ ሰጥተውት ተመለሱ።
ይህ በሆነ ወር Eንኳን ሳይሞላው፣ የሆነ ሰው ከባላገር ተልኬ የመጣሁ ነኝ Eያለ ዘው ብሎ ከቤት ገባና መልEክቱን ሲነግር፤ “Aባታችን፣ Aባ ጃሌ፣ ሰላምታ ይድረስዎት። ፍርድ ቤቱን ይተውት፣ Eኛ Eናስታርቅዎታለን። ለጊዮርጊስ Eለት ረፋድ ላይ፣ Eርሶዎንና Aጥር ተከለ የተባለውን፣ ልጅ Aስቻለውን ጠርተናችኋልና Eንዳይቀሩብን Aደራ። በቀጠሮ ቀን ከAዙሪት ወንዝ ዳርቻ ባሉት ግራሮች ስር Eንጠብቅዎታለን!” የሚል ቃል ነበር።
Aባ ጃሌም፣ “የሚያሰታርቅማ ከተገኘ፣ ከፍርድ ቤት ማን ይንከራተታል” ብለው፣ “Eሺ፣ ካስታረቃችሁኝስ ደግ፣ Eመጣለሁ Eንጂ!” የሚል መልስ
ላኩ። በተባለውም ቀን በቅሎ ተዘጋጅታ፣ ከቤት ልጅ Aንዱን Aስከትለው ተነሱ። በማለዳም Eንደ ሰንሰለት ከተያያዙት ተራሮች ጥግ-ጥጉን ይዘው ሲሰግሩ ካረፈዱ በኋላ ከAዙሪት ወንዝ ደረሱ፣ ከተባለው ቦታ Aካባቢ መቃረባቸው ነበር። ትንሽ Eንደ ተጓዙም በሩቁ ሦስት ግራሮች ከወንዙ ዳር ብቅ ብለው ታዩ። የቀጠሮው ቦታም ከዚያው ነበር።
ወራቱ በልግ ስለ ነበረ AዝርEቱና Eሸቱ በመንገዱ ግራና ቀኝ ሜዳውን Aልብሶታል። የዱር Aበባም ሽታው ከሩቁ Eውድ-Eውድ ይላል፣ ንብ፣ ተርብና ልዮ-ልዮ ወፎችም ውር-ውር ይሉ ነበር። Aባም ከበቅሎዋቸው ኋላ ያፈናጠጡትን ልጅ፤ “በል ውረድ ልጄ፣ Aሁንስ ደርሰናል፣ ምንም Aልቀረንም፣ Eኒያ ግራሮች ድረስ በEግርህ ተከተለኝ” ብለውት ወርዶ፣ በEግሩ ከኋላ-ኋላቸው መከተል ያዘ።
ከግራሮቹ ጠጋ Eንዳሉም ሁለት ሰዎች ሲጠብቋቸው Aዩ። ሰዎቹም
Aባ ጃሌን Eንዳዩ፣ ከተቀመጡበት ተነስተው፣ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ በAክብሮት Eጅ ነስተው ተቀበሏቸው። ሰላምታ ከተለዋወጡም በኋላ፤
“Aባታችን፣ Aባ ጃሌ፣ ይቅርታ ያርጉልን Aደከምንዎት፣ ካሉበት ድረስ መምጣት የሚገባንስ Eኛው ነበርን፣ ግን ጉዳዩ ያለው ከዚህ ቦታ ሰለሆነ፣ Eርሰዎን ማድከም የግድ ሆኖብን ነው?” Eያሉ ይቅርታ ጠየቁ።
Aባ ጃሌም፤ “የለም ለጆቼ፣ ለኔም ነፋስ መቀበያ፣ ከቤት መውጫ ሆነኝ Eንጂ፣ ይህ በመሰለ ቀን ትንሽ ሽርሽር፣ ምን ድካም ይባላል?” Aሉ።
“Eንግዲያው Aስቀድመን ጥሪያችንን Aክብረው ስለመጡ Eናመሰግናለን፣ Aሁንም Aቶ Aስቻለው Eንደ መጣ ብዙ Aንይዝዎትም፣ በቶሎ ቤትዎ Eንዲመለሱ Eናደርጋለን፣ ብዙ የሚያስቆይ ነገር Aይኖረንም!” Aሉ።
Aባ ጃሌም፤ “ለመሆኑ ደህና ናችሁ ወይ? Aገሩ ሁሉ ሰላም ነው?” Aሉ።
ሰዎቹም ሲመልሱ፤ “Aባታችን፣ Eኛ ደህና ነን፣ Aገሩም ሁሉ በEርስዎ ጾምና ጸሎት ሰላም ነው። በልጉም Eንደሚያዩት Aምሮበታል፣ Aሁን በቅርቡ ለዓጨዳና ለዓውድማ ይደርሳል። ዘንድሮ ጥጋብ ነው!” Aሉ።
የAገር ሽፍታ የተባሉት ሰዎች ይቅርና የብረት መሣሪያ Eና ጠመንጃ፣ Aንዲት ጩቤም የሌላቸ፣ ከያዙት ቀጭን ከዘራ ብጤ በEጃቸው Aንድም ነገር የሌላቸው ሰዎች ነበሩ። Eንዲህ Eያወሩና Eየተጫወቱ ከAንድ ሰዓት በላይ ካለፈ በኋላ፣ ከሁለቱ መሪ መስሎ የሚታየው፤ “Aቶ Aስቻለው የሚመጣ Aይመስልም፣ በቂ ጊዜ ጠበቅነው ግን Aልመጣም። Eርስዎን
Aባታችንንም በከንቱ Aድክመን Aጉላላንዎት፣ ይቅርታ! Eንግዲያውስ ይሂዱ፣ የቀረውን ለኛ ይተውልን። Eኛው Eንጨርሰዋለን!” Eያለ ተነሳ።
Aባ ጃሌም፤ “ተባረኩ ልጆቼ፣ Eንደ Eናንተ የመሰለ Aውራ ከየሰፈሩ Eና ከየቦታው በሃገራችን Aይጥፋ። ሰውየው ካልመጣ’ማ ምን ይደረግ? በሉ በሰላም ዋሉ።” ብለው በመሰናበት ልጃቸውን Aስከትለው ወደ ቤታቸው መንገድ Aቀኑ። ከዚያ ትንሽ ራቅ Eንዳሉም በቅሎዋን Aቁመው ልጁን ከኋላ Aፈናጠጡና Eየሰገሩ ወደ Aውራጃው ከተማ ጉዟቸውን Aመሩ።

ይህ በሆነ ሳምንት Eንኳን ሳይሞላው፣ በAቶ Aስቻለው ላይ የደረሰው ጉድ ወሬው በከተማው ይነፍስ ያዘ። ‘ጠርተነው ሳይመጣ የቀረበትን ትEቢትና ንቀቱ Eንዲበርድለት…’ ብለው ሽፍቶቹ በሌሊት ከቤቱ ድረስ ሄደው፣ Eጅና Eግሩን ጠፍረው በማሰር፣ በሽመል ሙልጭ Aድርገው ገርፈው፣ ‘ሁለተኛ Aይለምደኝም!’ ብሎ Eየጮኸ፣ ተማጥኖና ተገዝቶ፣ ፍዳውን ሁሉ ቆጥሮ፣ Aፈር መሬት Aብልተው ለቀቁት ይባላል። ብዙ ሳይቆይም ዘመድ ወዳጆቹን Aለማምኖ ያቺ Aጥር ተነቅላ Eንድትነሳ Aስደረገ። በሰው Eንጂ Eርሱ’ማ ምንም ሊያደርግ Aይችልም ነበር፣ በግርፋት ቆስሎ የተገጣጠበው ጀርባው Eስኪድን ለረዥም ጊዜ የAልጋ ቁራኛ ሆነ Aሉ።
በጥጋቡ ያመጣው ጦስ ስለሆነ ከቅርብ ቤተሰቡ በቀር ማንም ያዘነለት Aልነበረም። የብዙዉ ሰው Aስተያየት፤ ‘በሃገሩ መሬትና ቦታ Aልጠፋ! ጥሻውን መንጥሮ፣ የሚለበደውን ለብዶ፣ የራሱ Eርሻ ማልማት ይገባው ነበር። በጥጋቡ የሽማግሌው፣ የAባ ጃሌው ንቀት ነው ያጋለጠው! የሰው መሬት ማን ንካ Aለው? ደፋር፣ ዓይነ ደረቅ፣ የEጁን Aገኘ፣ Eሰይ!’ ብቻ የሚል ነበር። Aቶ Aስቻለው ቀደም ብሎ የቅርብ ቤተ ሰብና ወዳጆቹን ቢያማክር ኖሮ ይህ መች ይመጣበት ነበር? ለሌላው መቀጣጫ ሆኗል።
Aባ ጃሌም ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ፣ “Eኔ ምን Aውቃለሁ? Eንደ Eኔ’ማ ፍርድ ቤት ይወስን ብዬ Aመልክቸ ነበር፣ ግን ይህ ጉዳይ በፍርድ ቤት ታይቶ፣ ምስክር ተቆጥሮ፣ ይግባኝ ተብሎ፣ ከላይ በዳኛ ተወስኖ፣ ለፍርድ Aሰፈጻሚ ደርሶ በተግባር ላይ Eስኪውል ድረስ ብዙ ዓመታት ይፈጃል። ያ ሁሉ Eሲኪሆን ታድያ ለጠበቃ፣ ለተላላኪ፣ ለመዝገብ ቤት ፋይል Aውጪ፣ ለዳኛ ጉቦ Eያሉ ስንት ወጪ Aስከትሎ ኪሳራ ላይ ይጥላል። መንግሥት ለሃገሩ ሁሉ የቆመ ስለሆነ ለስንቱ ይዳረሳል? Eስኪዳረስ ጊዜ ይፈጃል፣ የተበደለው ሰውም ብዙ ጥቃት ይደርስበታል። Eንዲህ የመሰለ Aውራ ሲኖር ግን፣ ማንም Aለሁ ባይ ባለጌ ጉልበቱን ተማምኖ ወንጀል
ሲፈጽም በቶሎ Aርሞ ይቀጣዋል፣ ለተበደለውም ይደርስለታል። ስለዚህ በየAገሩ፣ በየቦታው Aውራ Aይጥፋ!” ይሉ ነበር።
ይህ ከሆነ በኋላም Aባ ጃሌው ብዙ ሳይቆዩ በምስጢር በዚያ በሢሶ ገበሬ Eጅ መልEክት ልከው፣ መሬታቸውን ላስመለሱላቸው ሽፍቶች ከልብ ከመነጨ ምስጋና ጋር ማለፊያ የሆነ ሙክት Eንዲሰጥ Aደረጉ። ይኽም ከፍርድ ቤቱ ክፍያ ጋር ሲመዛዘን ቅንጣትም Aይሆንም። ምክንያቱም ለማመልከቻ ጸሐፊና ለፋይሉ ማስመዝገቢያ የወጣው ብቻ Eንኳን ቢደመር ከሙክቱ ዋጋ Eጥፍ ከፍ ብሎ ቢበልጥ Eንጂ Aያንስም።

Aባ ጃሌው ዛሬ ብዙውን ጊዜ ጋቢAቸውን ደረብ Aድረገው ከAልጋቸው ተጋድመው ነው የሚውሉት። ልጆቻቸው ከAዲስ Aበባ ሊጠይቋቸው ሲመጡ፤ “Aባባ፣ ምን ይዘንልህ Eንምጣ?” ሲሏቸው፣ “ልብስ!” ይላሉ። ልጆቻቸው የሚያመጡላቸውን ልብስ ግን ሲለብሱት ማንም ሰው Aይቶት Aያውቅም። የሰፈሩ ድሆች ብቅ Eያሉ፤ “Aባ ጃሌው! Eንዴት ሰነበቱ…” Eያሉ ሊጠይቋቸው ሲመጡ ልብሶቹን ከAጠገባቸው Eያነሱ፤ “Eንካ ያውልህ፣ ሸፍነህ፣ ደበቅ Aድርገኸው ሂድ!” ብለው መለገስ ነው።
የሰፈሩ ድኻ ሁሉ Eየመረቃቸው ለብሶ ይኖራል። Eንዲህ Eያሉ በሰላም ሲኖሩ ታድያ Aንድ ቀን በAውራጃው ከተማ ከታወቁት የማዘጋጃ ቤት ባለ ስልጣኖች Aቶ ስንዱ የተባለ ሰርግ ደግሶ፣ ልጁን ዳረ። Aባ ጃሌው ታድያ ከቤት ውለው፣ የሰርግ መሄጃ ዘመኑ Aልፏቸው፣ ስለ ድግሱ ሰፊ ዝግጅት በወሬ ይሰሙ ነበር። የዛሬን Aይበለውና በዚህች የAውራጃ ከተማ Aባ ጃሌ ከAማጭነት ጀምሮ Aስከ Aሰላፊነት ያልተካፈሉበት ሰርግ Eንደ ሰርግ የማይቆጠርበት ጊዜ ነበር። የማያልፍ የለም፣ ያም ሁሉ Aልፏል።
ሰርጉ በተደገሰበት ማግስት ታድያ Aንድ ጉድ ሰተት ብሎ ወደ ቤታቸው Aመራ። የተዳረችው የAቶ ስንዱ ልጅ ድንግል ሆና Aልቆየችም። ሙሽራው በዚህ ተናድዶና ተቆጥቶ ሙሺሪቱን ከጫጉላ ቤት Aባረራት። ቤተ-ሰብ ሁሉ ጉድ Eያለ ተሰብስቦ ሲያዝን፣ Aባት Eና Eናት ልጅቱን ለብቻዋ ከመኝታ ቤቷ Aስገብተው፣ በጥያቄ Eንዲህ ያደረገሽ ማን ነው Eያሉ Aውጣጧት። “የኔን ድንግል የወሰደው በቀለ ነው።” Aለች። Aቶ ስንዱም በቀለን Eገድላለሁ Eያለ መደንፋቱ በከተማው በይፋ ተወራ።
በቀለ የAባ ጃሌው የመጨረሻው ልጃቸው ነው። በEውነትም የኮሌጅ ተማሪ ሆኖ፣ በክረምት-ክረምት ከAዲስ Aበባ መጥቶ፣ ከAባቱ ጋር ጊዜ ሲያሳልፍ፣ ከAንዴም ሁለቴ ልጅቱን ይዟት ከቤት መምጣቱ Aባ ጃሌው ትዝ Aላቸው። ያ ነገር ታድያ ዛሬ ሦስት፣ ወይም ኣራት ዓመት ገደማ
ሆኖታል። Aሁን በቀለ ኮሌጅ ጨርሶ ከጅማ በቡና ቦርድ ሥራ ይዟል። ታድያ ምን ለማድረግ ይቻላል? Aባ ጃሌም በልባቸው፣ “ጐሽ የኔ ልጅ!” ቢሉም፣ ምን Eንደሚያደርጉ ማሰብና ማሰላሰል ያዙ። Aቶ ስንዱ በAጭር ጊዜ ውስጥ ወደ Eርሳቸው Aቅጣጫ Eንደሚገሰግስ ምንም Aልሳቱትም።
Aባ ጃሌው፤ ‘የልጄን ክብር ገሥሷል… በቀለን Eገድለዋለሁ’ Eያለና Eየደነፋ የሚመጣውን Aቶ ስንዱን Eንዴትና በምን ዓይነትስ ሁኔታ Eንደሚቀበሉት ጨነቃቸው። ምን ብለው Eንደሚመልሱለትና ምንስ Eንደሚሉት ማውጣትና ማውረድ ያዙ። ምን ቢሉት ይሻል ይሆን?

Aባ ጃሌው Aውርደውና Aሰላስለው መላ-ምት መቱ፣ Aንድ ብልሓትም ፈጠሩ። ከቤት ልጆች Aንዱን ጠርተው፤ “ልጄ Eስኪ ወረቀትና ብEር ይዘህልኝ ና። Aንድ የምትጽፍልኝ ደብዳቤ፣ የለም፣ ሁለት ደብዳቤዎች ናቸው። ቶሎ በል!” ብለው ጠሩት። ሁለቱን ደብዳቤ Eንደ ጻፈላቸውም በቶሎ Aንዱን ደብዳቤ ወደ ልጃቸው፣ በፖስታ ቤት ወደ ጅማ ላኩለት። ደብዳቤው ይዘቱ፤ “ልጄ፣ በቀለ! ለAንድ Aስቸኳይ ጉዳይ ስለምፈልግህ ሳትውል፣ ሳታድር፣ ዛሬውኑ ስልክ ደውልልኝ…” የሚል ነበር።
ሁለተኛውን ደብዳቤ ግን በትራሳቸው ከተደረደሩት የድሮ ደብዳቤዎች Aንዱን ፓስታ ከፍተው በውስጡ ከተቱና ጋቢAቸውን ደራርበው ገደም Aሉ። ገደም Eንዳሉ ብዙም Aልቆየ፣ “የፈሩት ይደርሳል… ” Eንዲባል፣ Aቶ ስንዱ ወድያው ከቤታቸው Eየደነፋና Eየጮኸ ከተፍ Aለ።
Aቶ ስንዱ ጤና ይስጥልኝ ብሎ ገብቶ፤ “ተቀመጥ!” ሲሉት፣ ሳይቀመጥ፣ በቁጣ ብው Aለና፣ “Aባ ጃሌው፣ ዛሬ የመጣሁበት ጉዳይ ልጅዎ በቀለ ልጄን Aስካለችን ደፍሮብኝ፣ Aዋርዶኛል። የመጣሁበት ምክንያት ካሳ ለመጠየቅ Eንዳይመስልዎት። Eኔ ሌላ ካሳ Aልፈልግም፣ በቀለን በEጄ ልገድለው ነው የመጣሁት። የት ነው ያለው? ይንገሩኝ!” Aላቸው።
Aባ ጃሌም፤ “ይካሱኝ ብትልስ ምኔን ነው የምክስህ? በል ሂድ ግደለዋ! Eኔ ምን ላድርግ? የዛሬ ልጆች ወላጅ የሚመክራቸውን መች ይሰሙና! Aንተስ ወልደህ Aይተኸው የለ? ምን Aድርግ ነው የምትለኝ?” Aሉት።
“በቀለ ያለበትን ብቻ ይንገሩኝ፣ የማደርገውንስ Eኔ Aውቃለሁ!” Aለ።
Aባ ጃሌም ደብዳቤውን ከጻፈው ልጅ ሌላውን የቤት ለጅ ጠርተው፣ ከትራስጌ ቀደም ብለው ያስቀመጡትን ደብዳቤ Aወጡና፤ “ባለፈው ሰሞን በፖስታ የመጣልኝ ነው፣ Eስኪ ልጄ Aንብብልኝ…” Eያሉ ሰጡት።
ልጁም፤ “Aባባ፣ ለጤናዎ Eንደምን Aሉ…” ወዘተ፣ ብሎ ስላምታውን ካቀረበ በኋላ፣ ስለ ራሱ ጤንነት፣ ቀጥሎም የሥራ Eድገት Aግኝቶ ወደ ሓረር መዘዋወሩን የሚገልጽ ዝርዝርና በቅርቡም ወደ Aውራጃው ከተማ መጥቶ Eንደሚሰናበታቸው የሚገልጽ ወሬ Aበሰረ። ይኸ ሁሉ Aባ ጃሌ Aስቀድመው ያውጠነጠኑትና የጠመጠሙት ሲሆን፣ በቀለ Aባቱን ሊያይ ይመጣል ብሎ Aቶ ስንዱ ከዚሁ ተቀምጦ Eንዲጠብቅና፣ Eሱን ለማደን ወደ ጅማ Eንዳይሄድ ያዘጋጁት የተንኮል ደብዳቤ ነበር።
Aቶ ስንዱ ይኸንን ሲሰማ፤ “መቸ ነው ደብዳቤው የተጻፈ ብሎ ጠየቀ። Aባ ጃሌም Aስቀድመው ባውጠነጠኑት የደብዳቤው Eለት የዛሬ ሦስት ሳምንት Aድርገውታል። Aቶ ስንዱ፤ “ነገውኑ ወደ ሓረር Eገሰግሳለሁ!” Eያለ ደጋግሞ ደነፋ። ቀጥሎም፤ “ካልገደልኹት ይኽን ሱሪየን ግልብጨ ነው የምለብሰው። ልጄን ደፍሯት Eንዲሁ በከንቱ Aይቀርም!” Aለ።
Aባ ጃሌም፤ “Eኔ ምንም የምልህ የለኝም። Eንዳልከው ሂድና ግደለው። Eውነትህን ነው፤ Eኔም ሴት ልጄን ማንም ሰው ቢደፍርብኝ ያው ነው። Aልምርም። ሂድ ግደለው!” Aሉት።
Aቶ ስንዱ ይህ ፈጽሞ ያልጠበቀው መልስ ሆኖበት ግራ ገባውና ምን Eንደሚላቸው ጠፋው። Aንደበቱ ሁሉ ተሳሰረ። ነገሩን ሲጀምር ‘ልጄን Eንዳትነካ!’ የሚሉት መስሎት ነበር፣ ‘ሂድና ግደለው…’ የሚል መልስ ሲሰማ ግን የቁጣ መንፈሱ በረድ Eያለ መምጣቱ ከፊቱ በግልጽ ይታይ ነበር። ያም ቢሆን Eንዳመጣጡ Eየፎከረና Eየደነፋ ወጣ።
ወጣ Eንዳለ ግን Aባ ጃሌው የቤት ልጆቻቸውን፤ “Eስኪ ልጄን መግደል ቀርቶ የፊቱን ዝንብ Eሽ ሲል Aያለሁ! ወይ ጉድ! የዛሬ ሴቶች ወንድ ሲያዩ የሚሆኑትን Eያጡ፣ ሲያቅበጠበጣቸው፣ Eራሷ ለምናውስ ቢሆን ማን ያውቃል? Aስገድዶኝ ነው ልትል ይሆን? ታድያ’ማ ከቤቱ ድረስ ምን ያመላለሳት ነበር? ደግ Aደረገ! የወንድ ልጅ ‘ሰረቀ፣ ዋሸ’ ተብሎ Aይወራበት Eንጂ፣ ይኽ’ማ የጀግና ሥራ ነው የሠራው፣ ጐሽ!” Aሉ።
Aቶ ስንዱ Eንደፎከረው በማግስቱ ማለዳ ገስግሶ፣ በAውቶቡስ ተሳፍሮ ሓረር መሄዱን ሰሙ። Aባ ጃሌ የጻፉት ሁለተኛው ደብዳቤም ከጥቂት ቀናት በኋላ ደርሶ፣ ልጃቸው በቀለ ከጅማ በጎረቤት ስልክ ደወለላቸው። Aባ ጃሌውም በከተማው የሆነውን ሁሉ ዘርዝረው በማስረዳት፣ “ልጄ! ተጠንቀቅ፣ ለጥቂት ቀናት ነገሩ Eስኪበርድ ድረስ ከወንድሞችህ ዘንድ፣ Aዲስ Aበባ ሂድና ተደብቀህ ቆይ… ነገሩ ሲበርድ Eኛው Eንነግርሃለን።” ብለው መክረው Aስጠነቀቁት።
Aቶ ስንዱ ሓረር ለሳምንት ያህል ተንከራትቶ፣ በቀለን ቢያጠያይቅ ሳያገኘው ቀረ። ምናልባት ገና ከጅማ Aልተዘዋወረ ይሆናል በማለት ወደ ጅማ ሄደ። ከዚያም Aጠያይቆ በቀለን በሥራ የሚያውቁት ሰዎች Aገኘ፣ ግን በጅማ ከተማ ለጥቂት ቀናት Aለመታየቱን Eንጂ ወዴት Eንደ ሄደ ለማወቅ Aልቻለም። ተስፋ ቆርጦ በሁለተኛው ሳምንት ከቤቱ ተመለሰ። የከተማው የማዘጋጃ ቤት ቋሚ ሠራተኛ በመሆኑ፣ በልጁ ሰርግ ሰሞን በወሰደው Eረፍት ላይ ተጨምሮ የዓመት Eረፍቱ ቀናቶች ሊያልቁበት ሆነና፣ ሳይወድ ከሥራው ገበታ Eንዲመለስ ተገደደ።
“የዋለ፣ ያደረ ነገር Aትጥላ!” Eንዲባል፣ ውሎ Aድሮ ነገሩ Eየቀዘቀዘ መጣ፣ Aባ ጃሌውም Aቶ ስንዱን Eንታረቅ ሲሉ ሽማግሌዎች ላኩበት።

ከAቶ ስንዱ ዘንድ የተላኩት ሽማግሎች ከቤቱ ገብተው፤ “Aባ ጃሌው ራሳቸው መጥተው፣ በጉልበታቸው ከመሬት ተንበርክከው ይቅርታ ቢጠይቁህ በወደዱ ነበር። ግን Eንዳየኻቸው Aርጅተው የAልጋ ቁራኛ ሆነዋል። ‘ሰው ቂም ይዞብኝ Eንዳልሞት’ Eያሉ በጣም ተጨንቀው ነው የላኩን። ታድያ ቂምህን Aውርጃለሁ በላቸው!” Aሉት።
Eርሱም፤ “Eኔ ከEርሳቸው መች ተጣላሁ፣ የምን ቂም ኖሮኝ ነው Eርቅ የሚያስፈልገን? ያልተጣላ ይታረቃል Eንዴ?” Eያለ Aንገራገረ።
Eነርሱም ቀጥለው፤ “Eስኪ ከዛሬ ልጆች ማን ነው የAባት፣ የEናት ምክር የሚሰማ? ምን ያድርጉ ብለሃቸው ነው? Eሳቸውም Eንደሆኑ ከAፋቸው የሰማኸው Aይደለም Eንዴ? የልጃቸውን ጥፋት ተቀብለው፣ ‘ሂድ ግደል!’ Aሉ Eንጂ፣ ልጄ ነው ብለው ጥፋቱን ለመሸፈን Aልሞከሩ፣ Aላንገራገሩ! በል Eንግዲያው Aሁን Eንዳልካት ከAባ ጃሌው ጋር ቂም ከሌለህ፣ Aሁኑ ሄደህ፤ ‘Aኔ በEርሰዎ ላይ ቂም የለኝምና፣ ‘ይቅር!’ ብያለሁ’ በላቸው Eና በሰላም ይሙቱ። ይቅር ለEግዚሄር ነው!” Eያሉ ለመኑት፣ ተማጠኑት።
Aቶ ስንዱ የተላኩትን ሦስት ሽማግሌዎች፣ የገፋ Eድሜያቸው፣ የሸበተው ጺማቸው፣ የተመለጡ ራሶቻቸውን፣ ከደረቡት ነጭ ጋቢ ጋር፣ ድንቅና Eጹብ ግርማ ሞገስ Aልብሷቸው ሲያይ፣ ከቤተክርስትያን ያለውን የሦስቱ ሥላሴን ምስል ያየ ሆኖ ተሰማው፣ Eንዴት ብሎ Eምቢ ይበል? ወዲህ፣ ወድያ Aያለ፣ የባጥ የቆጡን Eያወጣና Eያወረደ ዘላበደ፣ ለጥቂት ጊዜም Aቅማማ። Eነርሱስ መች ዋዛ፤ “Eሺ Eስክትለን ከተቀመጥንበት Aንነሳም፣ ከቤትህም Aንወጣም!” ብለው ወጥረው ያዙት፣ መፈናፈኛም Aሳጡት።
ቢጨንቀውና መውጫ ቢያጣ፤ “ካላችሁስ Eንግዴህ ምን ላድርግ፣ Eሺ!” Aላቸው። ሦስቱም ተራ በተራ Eየተነሱ፣ Aንቀው Eየሳሙ፣ “Eመቤታችን Eግዚትነ ማርያም ራሷ Eሺ ትበልህ፣ ተባረክ ልጃችን፣ ረዥም Eድሜና ሙሉ Eንጀራም ጨምሮ፣ Aብዝቶ ይስጥህ!” Eያሉ መረቁት።
Aቶ ስንዱም፤ “Aሜን፣ Aሜን!” Eያለ ምርቃታቸውን ተቀበለ።
“በል Eንግዴህ ዛሬ፣ ነገ ሳትል፣ ፈጥነህ ሄደህ ጠይቃቸው፣ የሽማግሌ ነገር Aይታወቅም፣ ብዙ ቀን የቀራቸውም Aይመስሉም። ንስሓ ገብተው፣ ነፍሳቸውን Aዘጋጅተው፣ ስጋ-ወደሙ Eንዳይቀበሉ፣ Aንተ የያዝክባቸው ቂም በልባቸው ገብቶ፣ Eስካሁን የጋረዳቸው Eሱ ብቻ ነው!” Aሉት።
“Eሺ፣ Eሺ! Aባቶቼ፣ ያላችሁኝን ሁሉ በቶሎ Eፈጽማለሁ!” ብሎ ቃል ገባላቸው። ከዚያም ሽማግሌዎቹ ተነስተው ወደ መጡበት ተመለሱ።
የAባ ጃሌው Aሰተዋይ ጥበብና ዘዴ Eንዲያ ቦግ ብሎ ሊነድድ Eና Aገር ሊያቀጣጥል ተነስቶ የነበረውን Eሳት Aበረደው። Aቶ ስንዱም በገባው ቃል መሰረት ከጥቂት ቀናት በኋላ ከAባ ጃሌው ቤት ሄዶ ቂሙን ማውረዱ ሊገልጽ ሲገባ፣ Eሳቸውም በቀረችው ጉልበታቸው፤
“ልጄ! ልጄ! Eሰይ፣ Eሰይ! Eንኳን’ማ መጣህልኝ!” Eያሉ ከAልጋ ሊነሱ ሲሞክሩ፣ ያረጀውና የሳሳው Aካላታቸውን Aይቶ Aንጀቱ ክልውስውስ Aለበት። የበፊት ንዴቱ ወዴት Eንደ ገባ Eርግፍ Aድርጎ ረሳው።
“የለም! የለም Aባቴ! Aይነሱ! Aይነሱ! Aይገባም፣ Aረ ፈጽሞ Aይገባም!” Eያለ Eንዳይነሱ ለመከልከል ወደ Eርሳቸው ጠጋ ሲል፣ Aባ ጃሌውም፤ “ይቅር በለኝ ልጄ፣ ይቅር በለኝ!” Eያሉ ተንገዳግደው ከላዩ ዝልፈልፍ ብለው ተጠመጠሙበት። Eንደምንም ደጋግፎ ከAልጋው መልሷቸው፤
“Eኔ Eርስዎን መች ተቀየምሁ? Aረ ይተውኝ Aባቴ፣ ደግሞስ ምን ቂምና ይቅር የሚባል ነገር ኖሮ ነው?” ብሎ ሲላቸው፣ ሁለቱም ተቃቅፈው፣ ተላቅሰው፣ ‘ይቅር! ይቅር ለግዚሄር!’ ተባብለው ተሳሳሙ።
ወድያውም ቡናው ተፈልቶ፣ የማሽላ ቆሎ ፍንድሻ ተፈንድቶ፣ Aብረው Eያወሩና Eየተጫወቱ Eኽል ውሃ ብለው ታረቁ። ከዚያ ቀን ጀምሮ፤ ‘Aሁኑኑ Eገድለዋለሁ! በቀለን ካለበት ውለዱ፣ የታለ?’ Eያለ ሲፎክር የነበረው Aቶ ስንዱም ቂሙና ቁጣውን Eርግፍ Aድርጎ ረሳው።
በሁለቱም ቤት መካከል ሰላም ወረደ። መታረቃቸውም በሰፈሩ ሁሉ በይፋ ታወቀ። ከዚያማ ወድያ Aቶ ስንዱ ዋና ቤተኛና ዘመድ ሆኖ Aባ ጃሌውን ዘወትር Eየተመላለሰ ይጠይቃቸው ነበር። Eንግዴህ Aባ ጀሌው
በቀለ ሊጠይቃቸው ሲመጣ Aንዲት ጊደር ወይ መሲና ብጤ Aስይዘው ከAቶ ስንዱ ቤት ሄዶ ይቅርታ Eንዲጠይቅ ይልኩታል። ከዚያም ወድያ የቂሙ ጉዳይ Aበቃ፣ ተከተተ ማለት ነው። ለጥፋት ታጥቆ የመሚጣውን ጠላት ተቀብሎ ወዳጅ ማድረግ ረቂቅ ጥበብና ዘዴ የሚጠይቅ ነው።

መደምደሚያ፦
በተፈጥሮ Eጅግ ከሚደንቁ ረቂቅ ነገሮች Aንዱ፤ ዘወትር Aካላታችንን ለመጉዳትና ለማጥቃት፣ ከሆነላቸውም ለማጥፋት የሚችሉ ብዙ ዓይነት ጠንቀ-ኅዋሳት ወደ ውስጣችን ይገባሉ። ሰውነታችንም ሁሌ ሲዋጋቸው ይኖራል። የሚጎዱትንና የማይጠቅሙትን ጠንቀ-ኅዋሳት በብዙ ዘዴዎች Aንጥሮና Aበጥሮ Eየለየ በብጉር፣ በላብ፣ በሽንትና በEዳሪ መልክ ውጭ Aውጥቶ ሲጥል፣ Aንዳንዶቹን ግን በልዩ ዘዴ Aባብሎ በመያዝ በተለያዩ ብልቶች ውስጥ በማስቀመጥ በብዙ Aገልግሎት ላይ ያውላቸዋል።
በጨጓራችንና በሌላውም መላው የሰውነታችን ክፍሎች ከሚኖሩት ብዙ ዓይነት ጠንቀ-ኅዋሳት ጋር፣ በሰውነታችንና በኅዋሳቱ መካከል ግሩምና ረቂቅ የሆነ ስምምነትና መግባባት በመፈጠሩ፣ ካለ Eነርሱ ልንኖር ቀርቶ፣ ለደቂቃም ቆመን ልንሄድና ልንተነፍስም Aንችልም። ጠንቀ-ኅዋሳቱ ለEኛ የሚጠቅሙ ልዩ-ልዩ ተግባሮችን Eየሠሩ ሲያገለግሉን፣ Eኛም የምግብ ምንጭ፣ መኖሪያ፣ መጠጊያና ከለላም ሆነናቸው በስምምነት Eንኖራለን።
ለመጉዳት የሚመጣውን ጠላት Aባብሎና Aግባብቶ የልብ ወዳጅ ማድረግ ጥልቅ Aስተዋይነትና ዘዴ ሲጠይቅ፣ በዓለም ላይ ከዚያ የበለጠ ጥበብ Aለ ብሎ ለማለት ያዳግታል። ይህን ጥበብ የዓለም መሪዎች በሥራ ላይ ቢያውሉት ኖሮ ምድር ገነት በሆነች ነበር።
Aባ ጃሌው ፊዴል ያልቆጠሩ መሃይም ናቸው፣ ግን ተፈጥሮ ባደላቸው ብሩህና Aስተዋይ AEምሮ ይህንን ጥልቅ የተፈጥሮ ጥብበ ደርሰውበታል። በሕይወታቸው ዘመንም ዘዴውን ደጋግመው በሥራ ላይ Aውለውታል።
ገ/I. ጐርፉ።
*የAባ ጃሌው ታሪክ በEውነተኛ ሰው ሕይወት የተመሰረተ Eንጂ ልብ-ወለድ Aይደለም። የታሪኩ ኮከብ የሆኑትም ሰው ከመቶ ዓመት በላይ ኖረው ከጥቂት ዓመታት በፊት ከዚህ ዓለም በሰላም Aልፈዋል።

Post Reply

Return to “Ethio Love ...ኢትዮ ፍቅር”