ሳላፈቅር ፍቅር..

Love, Relationship, Habesha intimate, Ethiopian girls,
ፍቅር ፣ ጋብቻ :ጉዋደኝነት: እንተዋወቅ:
Forum rules
NO Rated R Pictures! please. :)
Post Reply
User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

ሳላፈቅር ፍቅር..

Unread post by selam » 29 Sep 2009 22:59

ሳላፈቕር ፍቕር

እድሜ ደርሶ ለፍቕር ሲደርስ

ሴት ማድነቕ ጀመርኩ እንደ ኣዲስ

ይደረጋል ብየ ወጣሁ ሴት ፍለጋ

ምንም ሳላገኝ ቀን ኣልቆ ለሊቱ ነጋ


ያየሁዋት ሴት ትማርከኛለች

ያቺን ያቺን ሲል ሲያቅበጠብጠኝ

ኣንድዋን ሳላናግር ግዜው ሄድብኝ

ገና ሳላፈቕር ፍቕር ማሰብ ገደለኝ


ኧረ ሰዎች መላ በሉኝ

ምኑን ላይ ነው የሳትኩት እስቲ ንገሩኝ

መንገዱ ነው ወይስ ኣቕጣጫዉ የጠፋኝ


እኔ ባላገኛት ፈልጌ ባጣት

እስዋስ ያላገኘችኝ ምን ይሆን የነካት

እያወቀች ትሆን የሴት ነገር ሆኖባት

ኣለሁልህ ማለት እየፈለገች ኣሳፍረዋት

በፍቅርዋ እየተሰቃየሁ እንዴት ኣስቻላት


ቀኑን ኣፋጥነው እባክህ የኔ ጌታ

ገፋ ቢል ለኣይኔ ሊያታ

መከራዮ ኣልቆ ላጣጥም ደስታ

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: ሳላፈቅር ፍቅር..

Unread post by selam » 27 Oct 2009 22:08

አባይ እንመለስ
---------------------
ከበየነ
ዳኛው ወንጀለኛ ይግባኝ ሰሚው ገዳይ፣
እኚህ ባስቻሉበት ይከሰሥ ወይ አባይ?
ይልቅስ! ስደቱ ቢያበቃ አባይ እንዲመለስ፣
እስቲ ልጠይቀው ወደ ጦቢያ እንዲፈስ።
አባዬ! የወንዞች አባት፣
የጦቢያችን ምጣጭ ላቦት፣
ለምስር ለኑቢያ ሕይወት፣
ከመነሻህ ቀጠና ስታደራ ከመድረሻህ
ሰብል ስታሞክት፣
እስከመቼ ነው አባዬ ባዕድ መንደር የምንሰነብት፣
መቼ ነው ለአርንት በጦቢያችን የምንካተት?
አባዬ! መሪ ጠፍቶን መሪ አዝለህ፣
ጨቅላ ሙሴን በቅርጫ አንቀልባ አንሳፈህ፤
ከምስር ከፈራኦን ባርነት፣
ወገኖቹን ይሁዶቹን እንዲያበቃ ለአርነት።
ለእኛ ግን ከግፋግፍ እንቁላል የተፈለፈለ
የወንጀል ጫጩት፣
በግድያ ደልቦ የደም ዝክር የሚጋት፣
ኑቢያ ሲጸዳዳ በደል ሲሸለት፣
በአንተ አካል በአንተው ጅረት፣
በቃ ልትለው ስትችል እንዲያቀላፋ ለዕረፍት
በድልድይህ አሸጋግረህ ምነው ላክብን ጠላት?
ለጦቢያችን ሰለባ ወያኔ ይሉት አጋንንት።
አባዬ ዳገት ዳገቱን ፍሰስ፣
የተፈጥሮን ሕግ አፋልስ፣

ወልዲያ
Posts: 4
Joined: 23 Aug 2009 12:12
Contact:

Re: ሳላፈቅር ፍቅር..

Unread post by ወልዲያ » 31 Oct 2009 23:10

selam wrote:ሳላፈቕር ፍቕር

እድሜ ደርሶ ለፍቕር ሲደርስ

ሴት ማድነቕ ጀመርኩ እንደ ኣዲስ

ይደረጋል ብየ ወጣሁ ሴት ፍለጋ

ምንም ሳላገኝ ቀን ኣልቆ ለሊቱ ነጋ


ያየሁዋት ሴት ትማርከኛለች

ያቺን ያቺን ሲል ሲያቅበጠብጠኝ

ኣንድዋን ሳላናግር ግዜው ሄድብኝ

ገና ሳላፈቕር ፍቕር ማሰብ ገደለኝ


ኧረ ሰዎች መላ በሉኝ

ምኑን ላይ ነው የሳትኩት እስቲ ንገሩኝ

መንገዱ ነው ወይስ ኣቕጣጫዉ የጠፋኝ


እኔ ባላገኛት ፈልጌ ባጣት

እስዋስ ያላገኘችኝ ምን ይሆን የነካት

እያወቀች ትሆን የሴት ነገር ሆኖባት

ኣለሁልህ ማለት እየፈለገች ኣሳፍረዋት

በፍቅርዋ እየተሰቃየሁ እንዴት ኣስቻላት


ቀኑን ኣፋጥነው እባክህ የኔ ጌታ

ገፋ ቢል ለኣይኔ ሊያታ

መከራዮ ኣልቆ ላጣጥም ደስታ
ሠላም Selam!

አልገባኝም። ማብራሪያ ሳልፈልግ አልቀርም። :shock:
ፍቅር ጀባ

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: ሳላፈቅር ፍቅር..

Unread post by selam » 01 Nov 2009 17:10

ወንድም ወልዲያ ሰላም ነክ.
1-የግጥሙ ትርጉም እንደተረዳውት ማፍቀር ይፈልጋል ግን ማንን የሚለው ላይ መወሰን ያቃተው ይመስላል(ዉሉ አማረሽን ገበያ አትውጣት )ነገር ሆኖበታል.
2-ደግሞ ፈላጊ ና ተፈላጊ አለመገጣጠምም ያለ ይመስላል. :)
ምን ይመስልካል.. :?:
ሰላም ሁን.

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: ሳላፈቅር ፍቅር..

Unread post by selam » 02 Nov 2009 21:07

I crave for knowledge.

I envy tolerant, peaceful folks.

I am frightened by ignorance.

I loathe violence.
Image
Treating unhealable wounds

Nursing stunted plants

Straightening other folks’ lives

Never have I lived for myself
Image
Image

Post Reply

Return to “Ethio Love ...ኢትዮ ፍቅር”