ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 599
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

Unread post by selam sew » 01 Nov 2018 08:50

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ
***************************************************

Image

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ናቸው ተሿሚዋን ተሰናባቹን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዳኜ መላኩ ተክተው እንዲሰሩ በእጩነት ያቀረቧቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወ/ሮ መዓዛ ባላቸው የዳበረ ልምድ ምክንያት የአገሪቱን የፍትህ ስርዓት ወደፊት ያራምዱታል በሚል በእጩነት እንዳቀረቧቸው ለምክር ቤቱ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ይሁንታውን ሰጥቷቸዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በህግ የዳበረ ልምድ ያላቸው ፣ በተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ከፍተኛ ተቋማት ውስጥ በማገልገል አንቱታን አትርፈዋል፡፡
ከህገ መንግስት አርቃቂ ከሚሽን አባልነት በግላቸው ለሴቶች ከለላ የሚሆን ድርጅት እስከማቋቋምም ደረሰዋል፡፡

በመሆኑም በዛሬው ዕለት የተሰጣቸው የጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዝዳንትነት ሹመት በፍርድ ቤቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ያደርጋቸዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊም ቃለ መሃላ ፈፅመው በህዝብና በመንግስት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡

ምንጭ: ኢቢሲ

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”