የዛሬ ሐሙስ ጳጉሜ 1/2010 አበይት ዜናዎች - Wazema Radio News

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 606
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

የዛሬ ሐሙስ ጳጉሜ 1/2010 አበይት ዜናዎች - Wazema Radio News

Unread post by selam sew » 06 Sep 2018 12:27

ለቸኮለ የዛሬ ሐሙስ ጳጉሜ 1/2010 አበይት ዜናዎች Wazema Radio News

1. የሕዳሴ ግድብ የግንባታ ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ስመኘው በቀለን (ኢንጂነር) አሟሟት በተመለከተ ዛሬ ከቀትር በኋላ ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ለሁለተኛ ጊዜ ተዘዋወረ፡፡ ነሐሴ 25/2010 ሊሰጥ የነበረውና ለዛሬ ጳጉሜን 1/2010 የተላለፈው የመንግስት መግለጫ አሁንም ላልታወቀ ጊዜ ተራዝሟል ተብሏል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴር ለመራዘሙ በምክንያትነት የጠቀሰው “ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ተደራራቢ ስብሰባዎች ስላጋጠማቸው” የሚል ነው፡፡ በዛሬው ፕሮግራም የሰኔ 16ቱ የመስቀል አደባባይ የቦምብ ፍንዳታን በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ነበር፡፡

2. በአማራ ክልል፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን፤ ደዋ ጨፋ ወረዳ በታጠቁ ሰዎችና በጸጥታ አካላት በተካሄደ ግጭት የሰው ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡ በኢንቨስትመንት የተያዘ መሬት በአግባቡ ልማት ላይ አልዋለም በሚል ቅሬታ ግጭቱ ነሐሴ 25 እና 26 ቀን 2010 ዓም መከሰቱን ነው የወረዳው ጸጥታ ኃላፊ የተናገሩት፤ በድርጊቱ ተሳታፊ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

3. የበጎ አድራጎት ድርጀቶችና ማሕበራት አዋጅን ለማሻሻል የተመደበው አጥኚ ቡድን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ማጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ ‘የሲቪክ ማሕበራት አዋጅ’ በሚል ስያሜ የተዘጋጀው ማሻሻያ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀጣይ ሂደቱ ተጠናቆ፡ ፓርላማው ወደ ሥራ እንደተመለሰ እንዲያጸድቀው ይመራለታል፡፡ በተካሄደው ጥናት ከ50 በላይ አንቀጾች በድክመት ተለይተው ማሻሻያ እንደተደረገባቸው ተጠቁሟል፡፡ ማሻሻያው የመደራጀት መብትን የሚያረጋግጥ፣ ቀልጣፋ የምዝገባ ሥርዓትን የሚያመቻች፣ ደረጃውን የጠበቀ ገደቦች ያሉትና የራስ በራስ አስገዳጅ ቁጥጥርና ተጠያቂነት ባሟላ መልኩ የሚዘጋጅ ነው ተብሏል፡፡ ጠበቃና የሕግ ጉዳይ አማካሪ ወንድሙ ኢብሳ “ከምርጫ 97 ማግስት ሕዝብ በገዢው ፓርቲ ላይ ያሳየውን ቁጣ ለማዳፈን እንደ ጸረ ሽብር ሕጉ፣ የሕግ ሥርዓቱን ሳያገናዝብ የወጣ አዋጅ ነው” ሲሉ ተችተዋል፡፡

4. የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ ዛሬ ጳጉሜን 1/2010 ዓ.ም ኢትዮጵያ ገብቷል፡፡ “ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ” መስራቹ ኦባንግ ከ15 የንቅናቄው አባላት ጋር ነው ወደ ሀገር ያመራው፡፡ ኦባንግና ተቋሙ በተለያዩ ሀገራት በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ችግር ሲገጥማቸው ፈጥኖ በመድረስና የሕግ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ይታወቃል፤ በሀገር ውስጥ ተንሰራፍቶ የነበረው አፈና እንዲወገድ በዓለም አቀፍ መድረኮች ድምጹን ሲያሰማ ቆይቷል፡፡ ኦባንግ ከመንግስት ባለሥልጣናት ጋር ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

5. የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ሊቋቋም ነው፡፡ ወደ ሀገር የሚመለሱ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለማገልገል ዝግጁነታቸዉን እየገለጹ በመሆኑ፣ የሚቋቋመው ኤጀንሲ ይሕንን ሂደት ያስተባብራል፡፡ ተጠሪነቱ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚሆነው የኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ፣ እንዳስፈላጊነቱ በተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች አደረጃጀት ይኖረዋል፡፡

6. ቻይና ለኢትዮ ጂቡቲ ባቡር መሰረተ ልማት ያበደረችውን ገንዘብ መክፈያ ጊዜ ከአስር ወደ ሠላሳ ዓመት ማራዘሟ ተገለጸ፡፡ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ የቻይናና ኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ በሰጡት መግለጫ ነው ይሕን ያረጋገጡት፡፡ “በቻይና በነበረን ቆይታ በተለየ ሁኔታ በአንዳንድ ብድሮች ላይ መጠነኛ ማስተካከያዎችን ለማድረግ ዕድል አግኝተናል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በተለይ የአዲስ አበባ ጂቡቲ የምድር ባቡርን በሚመለከት በአስር ዓመት ይከፈል የነበረው ወደ ሠላሳ ዓመት እንዲሸጋገር እና የእፎይታ ጊዜው ሠፋ እንዲል ዕድል ተገኝቷል” ብለዋል፡፡

7. ኤርትራና ጂቡቲን ለማሸማገል እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማሊያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጉዳዩ ዙሪያ ከጂቡቲ ባለሥልጣናት ጋር ለመመከር ዛሬ ጂቡቲ ገብተዋል፡፡ የሁለቱን ሀገራት የድንበር ውዝግብ በሠላም የመፍታት ጥረቱ እንዲጀመር የተደረገው ትናንት በአስመራ ከተማ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ እና ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ (ፎርማጆ) በጋራ ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡ ሶሶቱ መሪዎች በስብሰባው ማጠናቀቂያ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ይሕ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ለ20 ዓመት ተዘግቶ የቆየውን በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ ጧት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ለሌሎችም ያጋሩ SHARE SHARE

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”