የዛሬ ሰኞ ነሐሴ 21/2010 አበይት ዜናዎች

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 618
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

የዛሬ ሰኞ ነሐሴ 21/2010 አበይት ዜናዎች

Unread post by selam sew » 27 Aug 2018 11:52

ለቸኮለ የዛሬ ሰኞ ነሐሴ 21/2010 አበይት ዜናዎች

1. የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ግዛት “በቋራ” ወረዳ “ነፍስ ገበያ” በተባለው አካባቢ ሰፍሯል ያለው የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ለቆ እንዲወጣ ጠየቀ። “ለጋራ የጸጥታ ማስከበር ስራ ይጠቅማል” በሚል ስምምነት በቦታው የሰፈረው የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ከያዘው ይዞታ ለቆ አለመውጣቱ ተገቢ እንዳልሆነ ያብራራው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ “በፍጥነት ከይዞታችን ለቆ እንዲወጣ” ብሏል። በተጠቀሰው አካባቢ የሰፈረው የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ይዞታ እያስፋፋና ቋሚ የጦር ሰፈር እየገነባ፣ ከያዘው ጊዜያዊ ይዞታ ሳይለቅ መቆየቱ ተገቢ አለመሆኑንም ብአዴን ገልጿል፡፡

2. የኢትዮጵያ ግዛት ከሆነችው ዛላምበሳና አካባቢዋ የተውጣጡ የሃይማኖት መሪዎች፣ የማሕበረሰብ ተወካዮች፣ አዛውንቶችና ወጣቶች ወደ ኤርትራዋ ሠንአፌ ከተማ አመሩ፤ አርባ ሠዎች የተካተቱበት ጉዞ በሁለቱ ሀገራት መሐል ዕርቀ ሠላም መውረዱን ተከትሎ የተካሄደ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት አካል ነው፡፡

3. የአዲስ አበባ ድጋፍ ሠጪ ታክሲዎች ዛሬ ሥራ ማቆም አድማ አደረጉ፡፡ ከመንግስት የተሰጣቸው ስምሪት ፍትሐዊ ባለመሆኑ አድማውን ማድረጋቸውን ባለመኪናዎችና ሾፌሮች አስረድተዋል፤ አንዳንድ መስመሮች በሕገ ወጥ መንገድ ለተወሰኑ ግለሰቦች እንደሚለሰጥ፣ ለመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ተቆጣጣሪዎች የሚሰጡት ጉቦ እጅግ ስላስመረራቸው አድማ በማድረግ ተቃውሞ ለማሰማት መውጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች ለመንግስት ሚዲያዎች በሰጡት ማብራሪያ …በአንዳንድ ቦታ አድማ ቢደረግም የትራንስፖርት እጥረት እንዳላስከተለ፣ በሸገር ባስ ጉድለቱን መሸፈናቸውን ነው የተናገሩት።

4. አብዲ መሐመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) ዛሬ አዲስ አበባ፣ አትላስ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡ አብዲ የሶማሌ ክልልን ከ10 ዓመት በላይ በጸጥታ ኃላፊነትና ርዕሰ መስተዳድርነት መርተዋል፡፡ አብዲ ኢሌን በሕግ ጥላ ስር እንዲውሉ ካደረጓቸው የወንጀል ተግባራት መካከል የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የብሔር ግጭት ማነሳሳት፣ በሃይማኖት መካከል ግጭት እንዲፈጠር ማድረግ የሚሉትን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጠቅሷል፤ የእሳቸው ተባባሪ ናቸው የተባሉ በፖሊስ እየተያዙ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የአብዲ ቤት ሲፈተሽ አራት ሽጉጥና አምስት ክላሽ መገኘቱ ተገልጿል።

AddisMedia youtube
Addis Media Youtube Channel ትናንት በሶማሌ ክልል በተካሄደ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ ከአብዲ ኢሌ ጋር ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳ 6 ሰዎች አብዲጀማል ቀሎንቢ (የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ)፣ ራህማ ማሕሙድ (የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ)፣ ኢብራሂም መሀድ (የትምህርት ቢሮ ኃላፊ)፣ ዴቅ አብዱላሂ (የውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ)፣ ኢብራሂም ማሕሙድ ሙባረክ (የጅግጅጋ ከንቲባ) እና ዑመር አብዲ (የኢሶህዴፓ ፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ) ናቸው፡፡

5. የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በዛሬው ዕለት የሥራ ማቆም አድማ ጀመሩ። የሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ኃላፊ በአድማው ምክንያት የተስተጓገለ በረራ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎቹ ከአድማው አስቀድመው “በተደጋጋሚ ላነሳነው የሙያ ዕውቅና፣ የደሞዝና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ አላገኘንም” ሲሉ ምክንያታቸውን አስረድተዋል፤ በማሕበራቸው አማካይነት ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ባስገቡት ደብዳቤ ለጥያቄያቸው ምላሽ ካላገኙ ከዛሬ ጀምሮ በረራዎችን እንደማያስተናግዱ አስጠንቀቀዋል፤ ከአምቡላንስ፣ ቪአይፒ እና ወታደራዊ በረራዎች ውጪ እንደማያስተናግዱ ገልጸዋል፡፡ የዛሬውን አድማ የመቱት በቦሌ፣ በባህርዳር እና መቀሌ በሚገኙ አየር ማረፊያዎች ያሉ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ናቸው፡፡

6. በግብጽ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚህ ሹክሪ እና የደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ አባስ ከማል የሚመራ ልዑካን ቡድን ዛሬ ነሀሴ 21/2010 አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ ቡድኑ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የተላከ መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ያደርሳል፡፡ ባለስልጣናቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በሚኖራቸው ቆይታ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ባለፈው ሰኔ ወር የተስማሙበት ለመሰረተ ልማት በሚውል ገንዘብ የማሰባሰብ ዕቅድ ዙሪያ ይመክራሉ፡፡

7. “የአማራ ምሁራን ጥምረት” ምስረታ ጉባዔ በባሕርዳር ተካሄደ፡፡ በጉባዔው ከ700 በላይ የክልሉ ተወላጅ ምሁራን ተሳትፈዋል፡፡ “የአማራ ምሁራን ጥምረት” ምስረታ ማጠቃለያ ላይ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው “አማራ እንዲፈሩት የሚጥር ሳይሆን ፍትህ እና ሠላም የሚሰብክ ነው፤ አማራነት ዝቅ ማለት አይደለም፤ ራስን መሆን ነው፤ አማራ መሆን ከክብር መውረድ አይደለም ማንነት ነው፡፡ ሕብረ ብሄራዊነት ነው” ብለዋል፡፡ ጉባዔው ዛሬ ከቀትር በኋላ ሲጠናቀቅ ዶ/ር ገበያው ጥሩነህ የአማራ ምሁራን መማክርት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

ለሌሎች ያጋሩ SHARE SHARE SHARE

Source: Wazema Radio Facebook Page

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”