ለቸኮለ ከዋዜማ ራዲዮ የዛሬ ስኞ ሐምሌ 23/2010 አበይት ዜናዎች

Daily Ethiopian News, አዳዲስ ዜናዎች።
Forum rules
** When you post a News please include the Source link.
For More Ethiopian News please visit the Home Page
http://ethiopiaforums.com/
selam sew
Leader
Leader
Posts: 604
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ለቸኮለ ከዋዜማ ራዲዮ የዛሬ ስኞ ሐምሌ 23/2010 አበይት ዜናዎች

Unread post by selam sew » 30 Jul 2018 12:04

ለቸኮለ ከዋዜማ ራዲዮ የዛሬ ስኞ ሐምሌ 23/2010 አበይት ዜናዎች

1. ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ አስቸኳይ ጉባዔው በውጪ በሚገኘው ሲኖዶስ ላይ አሳልፏቸው የነበሩ ውግዘቶችን አነሳ፡፡ ሲኖዶሱ በውጪ በሚገኙ አባቶች ላይ ውግዘቶችን ያስተላለፈው በ1985 እና በ1999 ዓ.ም ነበር፡፡ በአሜሪካ የሚገኘው ሲኖዶስ ባለፈው ቅዳሜ ተመሳሳይ አቋም ወስዷል፡፡ በሁለት ተከፍለው የቆየቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ መምጣታቸውን ተከትሎ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ከጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ጋር ወደ አዲስ አበባ ይመለሳሉ፡፡ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ለእሳቸውና ወደ ሀገር ለሚመለሱ ለሌሎች አባቶች ማረፊያ ተዘጋጅቷል፡፡

2. ከኢትዮ ቴሌኮም 13 ኃላፊዎች መታገዳቸው በደብዳቤ ተገለጸላቸው፡፡ ደብዳቤው ከደረሳቸው መሐል የኢንተርፕራይዝ ዲቪዥን የፐብሊክ ሠርቪስ ኢንተርፕራይዝ ኃላፊ፣ የአውቶሜሽን ዘርፍ ኃላፊ፣ የመሰረተ ልማትና የሴኩሪቲ ዘርፍ ኃላፊ ይገኙበታል፡፡ ለመታገዳቸው ምክንያቱ ያልተጠቀሰ ሲሆን፣ ደብዳቤው ተፈርሞ የወጣው በተሰናባቹ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዷለም አድማሴ (ዶ/ር) ፊርማ ነው፡፡ አንዷለም ኃላፊዎቹን ካሰናበቱ አንድ ሳምንት በኋላ በጠ/ሚኒስትሩ ውሳኔ ከቦታቸው ተነስተዋል፡፡ በፍሬሕይወት ታምሩ የተተኩት አንዷለም ከቴሌኮም ከተነሱ በኋላ የከፍተኛ ትምሕርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዳይሬክተርነት ተመድበዋል፡፡

3. የቃሊቲ፣ ቂሊንጦ፣ ሸዋሮቢትና ድሬዳዋ ማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ተሰናበቱ፡፡ እስር ቤቶቹ ከፍተኛ የመብት ረገጣ የሚፈጸምባቸው፣ ኃላፊዎቹም ከማዕከላዊ መርማሪ ፖሊሶች ጋር እየተባበሩ በእስረኞች ላይ ስቅይት ያደርሱ እንደነበር አቤቱታና ስሞታ ሲሰማባቸው ቆይቷል፡፡ ከኃላፊነት የተባረሩት የአራቱ ማረሚያ ቤቶች ኃላፊዎች (በቅደም ተከተል) ገብረየሱስ ገብረእግዚአብሔር፣ አሰፋ ኪዳኔ፣ የማነ አስፋው እና መኮንን ደለሳ ናቸው፡፡ የተሾሙት ተክሉ ለታ (ኮማንደር)፣ ጫላ ጸጋ (ኮማንደር)፣ እንዳሻው ማሙዬ (ኮማንደር) እና ወንድሙ ደበሌ ናቸው፡፡

4. ሜቴክ የሕዳሴው ግድብ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ኮንትራት ሥራን ለቻይናው CGGC ኩባንያ ተሻገረ፡፡ በሳሊኒ አማካይነት እየተካሄደ ያለው የግድቡ የሲቪል ሥራ በመልካም ሂደት ላይ ቢገኝም፣ ከሠባት ዓመት በፊት ሜቴክ የተረከበው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራ በ2017 ይጠናቀቃል ቢባልም በዲዛይን ለውጥና በተለያዩ ሠበቦች ዛሬም ድረስ ሥራው ፈቀቅ አላለም፡፡ በሜቴክ እጅግ ደካማ ክንውን የተነሳ ሥራው ተርባይኑን ላመረተው ኩባንያ ይሰጣል ተብሎ ነበር፡፡

5. የሕዳሴው ግድብ ሥራ አስኪያጅ ስመኘው በቀለን (ኢንጂነር) የቀብር ሥነ ሥርዓት እንዳንከታተል ተደርጓል በሚል በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ፈንድቃ ከተማ “ሥርዓተ ቀብሩን እንዳንከታተል ሆን ብሎ መብራት እንዲጠፋብን ተደርጓል” በሚል በተቀሰቀሰ ቁጣና ሀከት የሶስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡

6. ሀዋሳ ከተማ አዲስ ከንቲባ አግኝታለች፡፡ የከተማዪቱ ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ሱካሬ ሺዳ ዳንጊሶን በምክትል ከንቲባነት ማዕረግ ከንቲባ አድርጎ መርጧል፡፡ የደኢሕዴን አባል የሆኑት ሱካሬ ሺዳ የከተማ ምክር ቤት አባል ባለመሆናቸው በምክትል ከንቲባነት መንበሩን እንዲረከቡ ተደርጓል፡፡ በሀዋሳ ከተቀሰቀሰ ሁከትና ግጭት ጋር በተያያዘ ኃላፊነታቸውን ለቀዋል የተባሉት የቀድሞው ከንቲባ ቴዎድሮስ ገቢባ ወደ ክልል ተዛውረው እንዲሰሩ ተመድበዋል፡፡

7. ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አዲስ መጽሔት እና የኢንተርኔት ቴሌቪዥን መክፈት የሚያስችለውን የሚዲያ ቢሮ ከፈተ፡፡ በአክስዮን በሳተላይት የሚሰራጭ የቴሌቪዥን ጣቢያ መክፈት የሚያስችለውን ጥናት አስጀምሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሠራተኛ ምልመላና ከመንግስት ፈቃድ ለማግኘት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ እስክንድር ከጋዜጠኝነት ሙያው ጋር በተያያዘ ለዘጠኝ ጊዜያት ታስሯል፡፡

ለሌሎች ያጋሩ SHARE SHARE SHARE

Post Reply

Return to “Ethiopian Daily News .. ኢትዮ ዜናዎች”