አልሞትም! በእውቀቱ ስዩም

ግጥሞች፣ታሪኮች፣ፎቶዎች፣ሙዚቃዎች
Poems,Short stories, graphics,pictures,musics,Technology
selam sew
Leader
Leader
Posts: 601
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

አልሞትም! በእውቀቱ ስዩም

Unread post by selam sew » 27 Feb 2018 10:26

አልሞትም!
(በእውቀቱ ስዩም)

ስሚ!

እኔ በዚህ ዐለም፣ ብዙ ብሰቃይም፣
አንድ ሀሙስ የቀረው፣ መስየ ብታይም፣
አምሮቴን ሳላገኝ፣ ሱሴን ሳላከትም፣
በመሬት ከርስ ውስጥ፣ ገላየን አልከትም።

አልሞትም!

ማንም ባልደፈረው፣ መንገድ ሳልገሰግስ፣
እንደ ንጉስ አይዙር፣ ግማሽ ቀን ሳልነግስ፣
በጠገበው ሳልስቅ፣ ለራበው ሳልደግስ፣

አልሞትም!

ዝማሜን ሳላወልቅ፣ ያንድበቴን ግድብ፣
ዙፋን ላይ ሳልሸና፣ ጌቶቼን ሳልሰድብ፣
ከድሃ ሳላብር፣ ከገባር ሳልወግን፣
ከምድር በረከት፤?፣ ድርሻየን ሳልዘግን፣

አልሞትም!

ስሚ!

ልቤ እንደምኞቱ፣ ቢያገኝ እንደምርጫው፣
ያላማየ ማብቂያ፣ አንቺ ነሽ መቁዋጫው!
እና
አገሬን ለቅቄ፣ ልብሽህ ላይ ሳልከትም፣
በውብ ከንፈርሽ ላይ፣ ከንፈሬን ሳላትም፣
አልሞትም!

Post Reply

Return to “Ethio Art and Culture..ኢትዮ ጥበብ ፤ስነ ጽሁፍ ፤”