በጣሊያን ስደተኛ አበሻ ላይ ቀልድ

Post Reply
User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

በጣሊያን ስደተኛ አበሻ ላይ ቀልድ

Unread post by selam » 08 Jan 2010 23:16

[center]በጣሊያን ስደተኛ አበሻ ላይ ቀልድ[/center]

ከምንወደውና ከሚናፍቀን ቤተሰብ መራቃችንና መለየታችን፣ የብቸኝነት ኑሮን ስለምንገፋ፣ የሩጫ ኑሮ ስለምንኖር፣ ኑሮው የማይደላ፣ እረፍት የሌለውና ለመንፈስ የማይሞላ በመሆኑ ድብርቱ እንዳለ እናውቀዋለን። በዚህም ምክንያት የሣቅ ችግር አለብን አይደል! ታዲያ ይህንን ድብርት ለማላቀቅ ባገኘነው ዘዴ በመጠቀም አንዳንዴም እንሣቅ እስቲ! ፈገግታ ጥሩ ነው። በስራና በትምህርት የተጨነቀን አዕምሮን አንዳንዴም ለማዝናናት ያህል ከማህደሬ ውስጥ ቆንጥሬ ያወጣኋቸውን ቀልዶች አንብቡና በእኔ ሞት እስቲ ሳቁልኝ:: ቀልዶቹ በሙሉ ጣሊያን ሀገር ያለነውን አበሻ ነው የምመልከተው

[center]Image[/center]

[center]ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.)
***********************************************************************
.[/center] [justify]ታዲያ እንዲሁ ሡርቶ ራሱን ለማስተዳደርና ድሃ ቤተሰቦቹን ለመርዳት ይጓጓ የነበረ ወጣት አበሻ ጸሎቱ ሰምሮ እዚሁ ጣሊያን ይመጣል:: ለመስራት ካለው ጉጉት የተነሳ ጣሊያንን ከረገጠበት ቀን ጀምሮ በተለያዩ ከተሞች እየሄደ ሥራ ማፈላለጉን ተያያዘው:: ዕድሉ አልቀና ብሎት ለረዥም ግዜ ያለሥራ መቀመጥ በመገደዱ ይጨነቅ ጀመር::[/justify] [justify]ይህንን ጭንቀቱን ያየ አንድ ጣሊያናዊ ለጎብኚዎች መዝናኛ ተብሎ የተሠራ የዱር አራዊት የሚገኙበት ቦታ (zoo) ሄዶ ሥራ እንዲያገኝና እንዲሞክር ይነግረውና እዚሁ ጣሊያን ሀገር በምትገኘው pistoia የምትባለው ከተማ ይሄዳል:: "zoo di pistoia" ውስጥ ገብቶም ሥራ አላችሁ ወይ ብሎ ይጠይቃል:: በአጋጣሚም ምንም የሥራ ልምድ የማይጠይቅ የግማሽ ሰዓት ሥልጠና ብቻ የሚያስፈልገው ሥራ ያገኛል::[/justify] [justify]ሥራውም የዱር አራዊት ምስል ማስኬራ (maschera) አጥልቆ በብረት አጥር ውስጥ ገብቶ እንደተመደበበት እንሰሳ መሆን ነው:: አጅሬም በአጋጣሚ የተመደበው እንደ ጎሬላ ዝንጀሮ ሆኖ እንዲሠራ ነበርና የተሰጠውን የ30 ደቂቃ ስልጠና በብቃት አጠናቆ እንደ ዝንጀሮ መንጎማለል፣ መጮህ፣ መፈናጠር፣ ብቻ ምን አለፋችሁ ሁሉን መሆን ችሎ ወደ ሥራው ተሰማራ:: ጠዋት ሄዶ እስከ ማታ በብረት አጥር ውስጥ ሲንጎማለል ውሎ ማታ ወደ ሰውነቱም ወደቤቱም ይመለሳል:: ረዥም ሰዓት ስለሚሠራና ክፍያውም ጥሩ ስለሆነ በአጭር ግዜ ውስጥ ይጓጓለት የነበረውን ሁሉ በእጁ ማስገባት በመቻሉ ጭንቀቱ ወደ ፈጹም ደስታ ተለውጠ:: ሥራውንም ተላመደው::[/justify] [justify]ታዲያ መቼም በየቀኑ ለ12 ሰዓት ከአራዊት መንጋ ጋር መዋል ቀላል አይደለም:: ከዚያ አለቃውም ጉብዝናውን አይቶ ስለተደሰተ ብር ጨምሮ ሰጠው። ይህቺን ሰርቼ ብር ከተጨመረልኝማ ሌላም ነገር ሰርቼ የበለጠ አገኛለሁ አለና በማግስቱ መገለባበጥ ጀመረ። አጅሬውም ሲገለባበጥ ሳያስበው አንበሶች ያሉበት ወስጥ ተገልብጦ ገባ። አንበሶቹን እንዳያቸው ደንግጦ "እመ ብርሀን ከዚህ ጉድ አውጪኝ አለቀልኝ" እያለ በልቡ ሲያወራ ወዲያው የውስጡ ሠራተኞች የሆኑት ቶሎ ብለው ገብተው ወዲያው ይለያይዋቸዋል።[/justify] [justify]ታዲያ አራዊት ያው አራዊት ነውና ሳት ብሎ የሾለከ ቀን አያድርስ ነው:: አጅሬም ያው እንደገና የፈራው አልቀረም አንድ ቀን በአንበሳውና በሱ መካከል ያለው በር ሳይዘጋ ተረስቶ ኖሮ አያ አንበሴ ጎልመም ጎልመም እያለ ወደ እሱ መጣበት። አጅሬም ዝንጀሮነቱን እረስቶ "ወይኔ ጉዴ ወይኔ ምነው በቀረብኝ" እያለ በጭንቀት የሚገባበት ጠፍቶት አንዱ ጥግ ብረት ላይ ይለጠፋል:: አፉን አውጥቶ እንዳይጮህ ጎብኝዎች ስላሉ ተቸግሮ በጭንቅ ውስጥ እንዳለ ሳያስበው "ገብርኤል አውጣኝ" ሲል አንበሳው አማርኛ ሲናገር ጊዜ ቆም ብሎ "እንዴ! አበሻ ነህ እንዴ? "ብሎት እርፍ:: አንበሳ ከመቼ ጀምሮ ያወራል ብሎ ሲደነግጥ ለካስ አያ አንበሴዎቹም የኛው ሰዎች ነበሩ::
- ድሮስ ለአንበስነቱ ማን ብሎን!!
- ዝንጀሮነቱም ቢሆን የእንእጀራ ነገር ሆኖ እንጂ::[/justify] [center].[/center] [center]ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.) ***********************************************************************[/center] [center].[/center] [justify]አንድ ሚላኖ የሚኖር አበሻ ነው እናትና አባቱን ካገርቤት አስምጥቶ ከተማውን እያዞረ ያሳያቸው ጀመረ:: ታዲያ ወደ የግድግዳዉ ብቻ ጠጋ እያለ በbancomat ይኼንን euro ከግድግዳው ሲያስፈተልክ ያዩታል:: አባትዬው ግድግዳው ሁሉ ገንዘብ ሲተፋ አይተው በጣም ተገርመውና ተደንቀው ይሰነብታሉ:: ሳምንታት ያህል ቆዩና ወደ አገርቤት የመመለሻቸው ቀን ደረሰና እሳቸውን በመሸኘት ላይ እንዳለ ከአንዱ ግድግዳ ተጠጋና 500 euro አውጥቶ "ይህንን ለኪስዎ ብዬ ነው" ብሎ ይሰጣቸዋል::[/justify] [justify]አባትየውም በጣም አዝነው "ምነዉ ልጄ ዝም ብሎ ከየግድግዳው ዝም ብሎ ለሚብዋተተዉ ነፈግ ነፈግ የምታደርገው ለማን አስበህ ነዉ?" አሉ ይባላል::[/justify] [center].
ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.) ***********************************************************************
.[/center] [justify]"እግዜር ሆይ!! እንደው ምናለበት totocalcio እንዳሸንፍ ወይም ሎተሪ እንኳን እንዲደርሰኝ ብታደርግ" እያለ ሁልግዜ በማማረር የሚጸልይ አበሻ ነበር:: ቤተክርስቲያን አንድም ቀን ሳያቋርጥ እየደጋገመ በመሄድ ፀሎቱን እያለቀሰ ተያያዘው:: ታዲያ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማልቀስ የተለመደ አይደለም:: እናም የቤተክርስቲያኑ parrocco ሁልጊዜ ማልቀሱን አይተው ያሳዝናቸውና እግዜርን... "ይህ ሰው ሁልግዜ እየመጣ ይጸልያል:: ስምህንም እየጠራ ያለቅሳል:: ታዲያ ምን አለበት ጸሎቱን ብትሰማለት? ምኞቱን ብታሳካለት?" ይላሉ:: እግዜርም መልሱን ሲሰጣቸው "ሁልግዜ እየመጣ እንደሚጸልይ አውቃለሁ:: ታዲያ እኔ ምንላድርገው? መጀመሪያ totcalcioውን ይጫወታ!!!" አላቸው ይባላል::[/justify] [center].
ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.) ***********************************************************************
.[/center] [justify]ሁለት carabinieri አንዱን አበሻ መንገድ ላይ ያስቆሙትና documento አሳየን ቢሉት[/justify] [justify]- አበሻው - "የለኝም"[/justify] [justify]- soggiornoህን አውጣ ሲሉት[/justify] [justify]- አበሻው - "እሱም የለኝም"[/justify] [justify]- "ፓስፖርትህን አሳየን"[/justify] [justify]- አበሻው - "እሱም የለኝም"[/justify] [justify]carabiniereው እንዴት አርጎ እዚህ አገር ያለመረጃ ሊኖር ይችላል ብሎ ያው CPT ክመወሰዱ በፊት ልምርመራ ቀርቦ እንዲጠየቅ ተድረገ።[/justify] [justify]carabinieri - "እድሜህ ስንት ነው?"[/justify] [justify]አበሻ - "28" ይላል::[/justify] [justify]carabinieri - "እርግጠኛ ነህ?"[/justify] [justify]አበሻ - "ቆይ ላስብበት" ይልና ቆይቶ " 28 አይደለም ተሳስቼ ነው። 24 ማለቴ ነበር" ይላል::[/justify] [justify]carabinieri - "ግን እርግጠኛ መሆን አለብህ" ሲባል[/justify] [justify]አበሻ - "አሁንም ላስብ ጊዜ ስጡኝ" ይልና "20" ይላል:: እንዲህ እያለ እየወረደ ቢያስቸግራቸው አንዱ ከሳሽ carabinieriው ብድግ ይልና "ክቡር giudice ሆይ! እኔ የምጠይቀው ነገር ቢኖር ይሄ ሰውዬ ተመልሶ ወደ እናቱ ማህጸን ከመግባቱ በፊት ያለው እድሜ ይመዝገብልኝ" አለ ይባላል::[/justify] [center].
ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.) ***********************************************************************
.[/center] [justify]እዚህ ይኖር የነበረ አበሻ ለሁለት ዓመት ሶጆርኖ ጠብቆ ስላላገኘ ትንሽ በአእምሮ በጨጭ አርጎት ጓደኞቹ ግንዝብ አዋጥተው ውደ ሀገር ቤት ይልኩታል። ከእዚህ ከላኩት ጓደኞች አንዱ ከወራት በኋላ ወደ ቤተሰቦቹ ጤንነቱን ለማወቅ ብሎ ስልክ ይደውልና ከእናቱ ጋር ሲያወራ ...[/justify] [justify]ስልክ ደዋይ - "ተሻለው ወይ?"[/justify] [justify]እናትዮው - "እድሜ ለእናንተ ጓደኞቹ:: ተጋግዛችሁ ባትልኩልኝ ኖሮ ልጄ በስው ሀገር ሞቶ ይቀር ነበር"[/justify] [justify]ስልክ ደዋይ - "አይ! እዚህ እኮ መተዛዘን መረዳዳት የተለመደ ነው:: እንኳን ይሄ ቀርቶ ሌላም ይደረጋል"[/justify] [justify]እናትዬው - "ግን እኮ ወዲያው እንዳመመው ብትልኩልኝ ኖሮ በጣም ይድን ነበር" ሲሉት ጊዜ[/justify] [justify]ስልክ ደዋይ - "አይ እማማ ወዲያው እንደታመመ ይላክ ከተባለማ ጣሊያን ውስጥ ያለው አበሻ ሁሉ ይላክ ነበር" አላቸው::[/justify] [center].[/center] [center]ለመሣቅ (ከአብራሃም ዘ.) ***********************************************************************.
.
ሮማ ከተማ ለgay matrimonio ድጋፍ በወጡ በብዙ ሺህ በሚቆጠሩ ግብረሰዶሞች መሐከል አንዱ ሀበሻ የሀገራችንን ባንዲራ ከፍ አርጎ ይዞ እያውለበለበ ከፊት ረድፍ ሆኖ ሰልፉን ይመራል:: በዚህም ብቻ ሳይወሰን አጅሬው ሌሎቹ የሚሉትን መፈክር ቀደም ቀደም እያለ ድምጹን ከፍ አርጎ ያስተጋባል። ይህንን የአዩና የተበሳጩ አበሾች "ይህ የኛው ጉድ አይደል" ብለው ...[/center] [justify]"አንተ ስማ! እንዴት የአገራችንን ባንዲራ ይዘህ ከomosesuale ጋር ሰላማዊ ሰልፍ ተወጣለህ? ቢሉት ...[/justify] [justify]"ሞኛችሁን ፈልጉ! ለgay መጋባት ከተፈቀድላቸው ደስታዬን አልችለውም" ...[/justify] [justify]"ታዲያ እነሱ ስለተጋቡ አንተን ይህን ያህል ያስደስተሃል እንዴ?" ...[/justify] [justify]"እንዴታ!! እኔም ወንድሜን አግብቼ ከኢትዮጵያ አስመጣው ነበር" ... ብሏቸው አረፈው::[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************[/justify] [justify].
ሴትየዋ ልጆቻቸውን ለመጠየቅ ጣሊያን ይመጡና በዚሁ ቀርተው ጣሊያን መኖር ከጀመሩ ዓመት አለፋቸው:: በጠና ይታመሙና ሆስፒታል ገብተው ትንሽ ጊዜ ብቻ እንደቀራቸው ሀኪሞች ቁርጡን ነገርዋቸው። ያው እንግዴ ከመሞታቸው በፊት አንድ ቀን ልጆቻቸው እንዲህ ብለው ይጠይቋቸዋል:: እማዬ ድንገት ከሞትሽ የት እንቅበርሽ? እዚሁ ጣሊያን ውይስ ኢትዮጲያ ይሻላል? ብለው ሲጠይቁቸው እናትዬውም "አይ ምነው ልጆቼ! ያው ስሞት ሶርፕሬሳ (sorpressa) ብታረጉኝ" አሉዋቸውና ቁጭ::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************[/justify] [justify].[/justify] [justify]እናት ከአዲስ አበባ በተዘዋዋሪ ስልክ ሚላኖ ለሚኖረው ልጃቸው ደውለው ሲያወሩ ቆይተው[/justify] [justify]ልጅም ለቤተሰቦቹ ጤንነት ጠይቆ ሲያበቃ "ምነው እማዬ በደህና ደወልሽ ወይ?" ብሎ ቢጠይቃቸው[/justify] [justify]እናት ፡-"አይ ልጄ ትንሽ ገንዘብ ቸግሮኝ ነው"[/justify] [justify]ልጅ ፡- እንዳልሰማ መስሎ "አይሰማኝም ስልኩ ብልሽት አለው መሰለኝ" ብሎ ሲመልስ[/justify] [justify]ኦፐሬተሯ ፡- በመሃል ገብታ "ገንዘብ ላክልኝ ነው የሚሉህ" ብትለው[/justify] [justify]ልጅ ፡-"ዝም በይ! ደደብ! ታዲያ ገንዘብ አንቺ ካለሽ ስጫት" ብሎ ስልኩን ዘጋው::[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
እናት ከሀገር ቤት በስልክ ጣሊያን ለምትኖረው ልጃቸዉ "እዚያ እናንተ ጋ erboristeria የሚባል ሱቅ ውስጥ ወጣት የሚያደርግ መድሀኒት አላቸው ይባላል:: እንዲያዉ ፈልገሽ ላኪልኝ" ብለዉ ሲያስጨንቋት ጊዜ ፈልጋ ፈልጋ በ pillola መልክ የሚዋጠውን ገዛችላቸውና ላከችላቸው:: በኋላም ስልክ ደዉላ "እማዬ ያልሽዉን ልኬልሻለሁ:: አወሳስዱም በቀን አንድ ብቻ ነዉ:: በምንም አይነት መንገድ ከአንድ በላይ እንዳትወስጂ" mi raccomando ብላ ታስጠነቅቃቸዋለች:: እንደተባሉትም መጠቀም ይጀምራሉ:: መድሀኒቱ እየሰራ የእናትየውን ወዝ እንደገና ሲመጣ ያዩት አባት "እኔም ይህን ኪኒን ካልዋጥኩ" ብለዉ ያስቸግሩ ጀመር:: እናት አወሳሰዱን አስረድተዉ አባትም ከመድሀኒቱ መዉሰድ ይጀምራሉ:: ከዓመታት በኋላ ልጃቸው ሀገር ቤት ስትመጣ ኤርፖርት ሊቀበልዋት ከመጡት ሰዎች መሀል እናትዋ የሀያ አመት ወጣት መስለዉና ልጅ አዝለው ጠበቋት:: የመድሀኒቱ መስራት እየገረማት እናትዋን ከሳመች በሁዋላ "አባዬስ?" ብላ ጠየቀች:: እናትም "አይይ እሱማ የላክሽልን ኪኒን አንድ አንድ ብቻ ነዉ የሚወሰደዉ ብዬ ብነግረዉ አልሰማ ብሎ አራት አራት እየዋጠልሽ ይኸዉ አዝዬዉ መጥቻለሁ" ብለዉ ያዘሉትን ማሙሽ አሳይዋት::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************[/justify] [justify].[/justify] [justify]አንድ በችግር ላይ ያለ ሰው በጣሊያን ካለው ዘመዱ እርዳታ ፈልጎ ደብዳቤ በተደጋጋሚ ቢጽፍ መልስ አያገኝም:: በኋላም የሚለኝን ከቃሉ ለስማ ብሎ እንደምንም ብሎ ገንዘብ ተበድሮ ስልክ ይደውልለታል። በስልክ እንዳገኘውም ችግሩን ዘርዝሮ ነግሮ የሚለብሰው ሱሪ እንኳን ከቂጡ የተቀደደ መሆኑ ቢነግረው "ሱሪህ መቀደዱን ለምን ዞር ብለህ ታያለህ" አለው ይባላል::[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************[/justify] [justify].
አባት ገጠር ሆነው ጣሊያን ካለው ልጃቸው ጋር በስልክ እያወሩ ነበር:: ግን ልጃቸው የአባቱን ድምጽ መስማት ተስኖት ስለነበር "አባዬ ድምጽህ አይሰማም ምንድነው ስልኩ ችግር አለው?" ብሎ ቢጠይቅ አባትም "አይ ልጄ! እንደዉ በሽታ ቢጤ ቢይዘኝ ነጭ ሽንኩርት በላሁና አፌ እንዳይሸትህ ብዬ ተሸፋፍኜ ነው የማናግርህ" ብለው ቁጭ::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
እኛ አፍሪካውያን እንዴት እንደምንኖር አንዳንድ ጣሊያኖች በደንብ አያውቁም። እናም አንድ ጣሊያናዊ አንዱን አበሻ ይተዋወቅና እንዲህ ብሎ ጠየቀው::[/justify] [justify]ጣሊያናዊ :- አፍሪካ ውስጥ እናንተ የምትኖሩት በዛፍ ላይ ነው አይደል? ብሎ ጠየቀው::[/justify] [justify]አበሻውም በንዴት "አዎ" አለው::[/justify] [justify]ጣሊያናዊ :- እንዴት ነው ዛፉ ላይ የምትወጡት?[/justify] [justify]አበሻውም :- "በ ascensore" አለው ይባላል::[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ሴት ልጃቸውን ለመጠየቅ የመጡ እናት ናቸው አሉ:: ታዲያ ማታማታ ሲተኙ ከልጃቸው እና ከባለቤቱዋ መኝታ ቤት ውስጥ የሚሰሙት የማቃሰት ድምጽ ያሳስባቸዋል:: ታዲያ አንድ ቀን ምን ሰይጣን ነው እንዲህ የሚያረጋቸው ብለው ለማረጋገጥ ፈራ ተባ እያሉ ወደ ልጃቸው ምኝታ ቤት በዝግታ ይጠጋሉ በሩ በደንብ አልተዘጋም:: በቀዳዳ ያያሉ:: ደነገጡ :: ወደመኝታቸው ተመለሱና በማግስቱ ጠዋት ወዲያው ወደአገር ቤት ስልክ ደወሉ::[/justify] [justify]እናት - ሀሎ ደህና ሰነበታችሁ[/justify] [justify]ስልክ መላሽ - ደህና ነኝ[/justify] [justify]እናት - ሁሉን ስመጣ እናወራለን::[/justify] [justify]ስልክ መላሽ - ምኑን?[/justify] [justify]እናት - እረ ተውኝ::[/justify] [justify]ስልክ መላሽ - ምን ተፈጠረ?[/justify] [justify]እናት - አይ ይ ይ ይ!!!! "ልጄ ጥጃ ሁናለች" አሉ ይባላል።[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ሴትየዋ ጣሊያን ብዙ ጊዜ ከርመው አገር ቤት በተመለሱ በሳምንቱ እድርተኛቸው የሆነ ሰው ስለሞተ ቀብር ለመድረስ ተቻኩለው ሰራተኛቸውን "ማነሽ እስቲ! ከበቡሽ! " ያንን ነጠላ አቀብይኝ እባክሽ![/justify] [justify]ከበቡሽም ንጠላውን ስትፈልግ ስትዘገየችባቸው ጊዜ[/justify] [justify]ሴትዮዋ ይናደዱና አንቺ ልጅ ያንን cazzo ነጠላ አምጪልኝ ለቅሶ ደርሼ ልምጣ ቶሎ በይ ብዬሻለሁ።[/justify] [justify]አሁንም ስትዘገይብቸው ግዜ ይቺ ባፋንኩሎ ሶርዳ " ያሉትን የሰማ አለ?[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አበበ ቢቂላ እዚሁ ጣሊያን ሮማ ውስጥ ባለው stadio olimpico ውስጥ በባዶ እግሩ ማራቶን ያሸነፈ ጊዜ አንድ የተሸነፈ ሯጭ "ለምን በባዶ እግሩ እንዲሮጥ ፈቀዳችሁለት?" "እሱ እኮ ያሸነፈው ሸክም ስለቀለለት ነው" ብሎ ክስ በማቅረብ ዳኞቹን ሲጠይቃቸው ጊዜ ምን ብለው መለሱለት መሰላችሁ? "አንተም ሸክም እንዲቅልልህ ከፈለግህ ለምን ራቁትህን ሮጠህ አታሸንፍም ነበር?" ብለው መለሱለት ይባላል::[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንዱ እዚሁ ጣሊያን ሀገር ሆኖ እጮኛው ከሀግር ቤት ደብዳቤ ጻፈችለት:: "ከእንግዲህ ብኋላ የኔና ያንተ ነገር እዚሁ ላይ ቢያበቃ ይሻላል:: ከሌላ ልጅም ፍቅር ይዞኛል:: ደግሞም እስከዛሬ ድረስ የላኩልህን ፎቶግራፎቼን ቶሎ መልስልኝ" አለችው:: እሱም በጣም ይናደድና ወደ ጓደኞቹ ሄዶ እነሱ የማይፈልጓቸውን የሴት ፎቶግራፎች ሰብስቦ "መልክሽ ስለጠፋኝ ከነዚህ ፎቶግራፍ መሀል ምረጪና የራስሽን ወስደሽ ሌሎቹን እንድትመልሽልኝ አደራሽን" ብሎ ጻፈላት::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ሚላኖ የሚቀመጥ ለቤተሰቦቹ ስልክ እንኳን ደውሎ የማያውቅ ከብዙ ዓመት በኋላ ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ አገር ቤት ሄደ። ቦሌ ኤርፖርት ሲደርስ አሽከር ተቀበለው። ከአሽከሩም ጋር እንደተገናኙ ስለቤተሰቦቹ ይጠይቀው ጀመረ።[/justify] [justify]አሽከርየውም "ሁሉ ደህና ናቸው ብቻ ..." ብሎ ዝም አለ።[/justify] [justify]ልጅዬውም "ምነው ምን ተፈጠረ?"[/justify] [justify]አሽከር "ትልቁ ውሻ ሞተ"[/justify] [justify]ልጁ - "ምን ሆኖ?"[/justify] [justify]አሽከር - "እሱማ የትልቁን በሬ አንጀት ሲጎትት ታንቆ ሞት"[/justify] [justify]ልጅ - "በሬውን ምን ነካው?[/justify] [justify]አሽከር - "በሬውማ ለእሜቴ አርባ ታረደ እኮ!"[/justify] [justify]ልጅ - በጣም ይደነግጥና "እማዬ ምን ሆና ሞተች?"[/justify] [justify]አሽከር "እሳቸውማ በጌቶች ሞት አዝነው ሞቱ" ብሎ ቁርጡን ነገረው።[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************[/justify] [justify].
ባላገር የሚኖሩ አባት ሮም የሚኖረውን ልጃቸውን ለመጠየቅ እዚህ ከፉሚቺኖ aeroporto እየወጡ እያለ እቺ ጠጋ ሲሏት የምትከፈት የመስታውት በር ታጋጥመዋለች:: ሻንጣውን ቁጭ ያደርጉና ሊከፍቱ ጠጋ ሲሉ ክፍት ይላል:: እሰይ ብሎ ሻንጣ ሊያነሱ በሚመለሱበት ጊዜ ተመልሶ ይዘጋባቸዋል:: አሁንም ለመክፈት ሲመጡ እራሱ ይከፈታል:: ወደ ሻንጣው ሲመለሱ አሁንም ዝግት ሲልባቸው በንዴት ወደ ስዉ ይዞሩና "ጎበዝ ይሄ ምን ይቀልዳል?" ብለው ጠይቀው ነበር ይባላል::[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ጋሼ ከበደ ቡና ቤት ሲገባ ሁል ጊዜ 3 ቢራ በአንድ ጊዜ እያዘዘ ነው የሚጠጣው:: እንደጨረሰም እንደገና በሌላ ዙር 3 ቢራ ያዝና ይጠጣል። መጠጥ ቀጂውም "ለምንድነው 1 ቢራ ከማዘዝ 3 ቢራ በአንድ ጊዜ የምታዘው?" ብሎ ሲጠይቀው ጋሼ ከበደም "አይ! ሁለት ጓደኞቼ ወደ ውጪ ሀገር ስለሄዱና ስለተለያየን ያው መጠጥ ስንጠጣ ለሶስተችንም እያዘዝን እንድንጠጣ ቃል ስለተገባባን ለዚህ ነው በየዙሩ 3 የማዘው" አለው:: እነሱም መጠጥ ሲያዙ እንደዚሁ ነው። ጋሼ ከበደም ብዙ ጊዜ እየተመላለሰ ደንበኛ ሆነ:: ታዲያ አንድ ቀን ወደ ቡና ቤት ይገባና 2 ቢራና 1 ለስላሳ ያዛል:: መጠጥ ቀጂውም "ምነው ዛሬ ቀየርክ?" ቢለው እሱም መልሶ "እኔ መጠጥ ትቻለሁ" አለው:: menomale ለስላሳ ማዘዙ! almeno ሁለተኛ ዙር ብሎ አይደግምም። እነዚያ የተከፈቱት 2ቱ ቢራዎች ግን አያሳዝኑም!! ይታያችሁ እንግዲህ!! ያው ወደ ጋሼ ከበደ ጠጋ ማለት ሳያዋጣ አይቀርም
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንዷ አበሻ ለቢሮ ሥራ ለመቀጠር ወደ አንድ cooperativa ትሄድና ከሥራ ቀጣሪው ጋር ስለሥራው እየተነጋገረችና ጥያቄ እየተደረገላት ነበር...[/justify] [justify]ቀጣሪው - "ደሞዝ ስንስት ቢከፈልሽ ጥሩ ነው?"[/justify] [justify]ተቀጣሪዋ - "2000 ኤውሮ" አለች::[/justify] [justify]ቀጣሪው - "እንደውም 3000 ኤውሮ እናደርግልሻለን፣ ደግሞም አንድ ወር የዓመት ፈቃድ ከአዲስ መኪና ጋር ቢስጥሽ ምን ይመስልሻል?" አላት::[/justify] [justify]ተቀጣሪዋ - ደንግጣ "ቀልድዎን ነው አይደል?" ብትለው[/justify] [justify]ቀጣሪው - "አይ! ቀልዱን እኮ የጀመርሽው አንቺ ነሽ" አላት::[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ጣሊያን ሀገር የሚኖር ዜግነቱን ግን ወደ ጣሊያናዊነት የለወጠ አበሻ ከ fiumicino ተነስቶ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ከሻንጣ ፈታሾቹ ጋር አለመግባባት ይፈጥርና በሚሠሩት ስዎች ላይ ስለ ውጭ አገር ዜጋነቱ ይደነፋል:: ታዲያ ምን እንዳደረጉ ታውቃላችሁ? ዝም አሉና ልጁ የሚያርፍበትን አድራሻ ተቀብለው በሰላም ሸኙት:: ከዚያም እቤቱ ሄደው "በል በኢትዮጵያ ህግ መሰረት አንድ የውጭ ዜጋ ሌላ ሰው ቤት ማረፍ አይችልም":: ይህም ለውጪ ሀገር ዜጎች የተለየ ጥበቃና protection ደግሞም ለአንተ security ሲባል ከጸጥታ አንጻር ችግር እንዳይገጥምህ ተብሎ ነው:: ከዛ በኋላማ ምናለፋችሁ ጊዜውን በሙሉ ......[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ጋሼ ከበደ እድላቸው ሆኖ አሜሪካ ገቡና ኑሮን ሲኖሩ sex ሳያደርጉ ብዙ ጊዜ ሆኗቸው ነበር:: ታዲያ አንድ ቀን አንድ ሁለት ተባብልው ይሳካላቸውና አንዷን አበሻ ይዘው እቤታቸው ይዘዋት ይመጣሉ:: ወደ አልጋ ይሄዳሉ ...[/justify] [justify]ታድያ ጋሼ ከበደ አሷን ከላይ አርገው አሳቸው ከታች ሆነው ፍቅር እየሠሩ ነበር:: ልጀትዋም ከላያቸው ሆና ጸጉርዋንም ስትሠራው ነበር:: ጋሼ ከቤም የምታደርገውን አዩና ከልባቸው ተበሳጭተው ..."ምን አያደርግሽ ነው?" ብለው ሲጠይቋት አሷም ስትመልስ "አሜሪካ እኮ ሁለት ሥራ ካልተሠራ መኖር አይቻለም" አለቻቸው ይባላል::[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንድ ሰውዬ ለስራ ጉዳይ ወደ ውጭ ሲሄድ ለቅርብ ጓደኛው የሚስቴን ነገር አደራ:: ችግር ካለም ፃፍልኝ ብሎት ሄደ:: ከትንሽ ሳምንት በኋላ እንዲ ብሎ ፃፈለት[/justify] [justify]ውድ ወንድሜ :-[/justify] [justify]1ኛ ) በጣልክብኝ አደራ መሠረት ባለቤትህን በየጊዜው እጠይቃታለሁ። በጣም ደህና ናት::[/justify] [justify]2ኛ ) ከብዙ ወንዶች ጋር ተዋውቃለች። እናም ሲያወጧት አይቻለሁ::[/justify] [justify]3ኛ ) እኔንም አሳስታኝ አውጥቻታለሁ::[/justify] [justify]4ኝ ) ስለ 3ኛው ጉዳይ ምን አስተያየት አለህ ?[/justify] [justify]ባልየውም ይህ ደብዳቤ እንደደርሰው እንዲህ ብሎ መለሰለት[/justify] [justify]ውድ ጓደኛዬ :-[/justify] [justify]1ኛ ) ደብዳቤህ ደርሶኛል አመሰግናለው::[/justify] [justify]2ኛ ) ባለቤቴን ብዙ ወንዶች እና አንተም እንዳወጣሀት ገልፅህልኛል::[/justify] [justify]3ኛ ) ባለቤቴ ግን የሚጋባ በሽታ አለባት::[/justify] [justify]4ኛ ) አንተስ ስለ 3ኛው ጉዳይ ምን ትላለህ ?[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
የፈረንጅ ባህል ይዞ የተምታታበት አበሻ አገርቤት ለእረፍት ሄዶ ሳለ አንድ ቀን የታመመ ዘመድ ከጠየቀ በኋላ ሊሰናበት ሲል "በሉ እንግዲህ ወደሩቅ አገር ስለምሄድ ለቀብር አይመቸኝም" የሞተ እንደሆነ እናንተንም እግዚአብሔር ያጽናችሁ አላቸው ይባላል
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ብዙ ዓመት እዚህ የተቀመጠ አበሻ ሀገር ቤት እየሄደ ሚስት በማግባት ከአንዴም ሁለቴም ሶስስቴም እዚህ አስመጥቷል:: ነገር ግን ያመጣቸው ሚስቶች ትንሽ ወሮች ተቀምጠው ጥለውት ስለሚሄዱ በቃ ያለሚስት ተቀምጧል:: እናም አንድ ይህንን ችግሩን ያልየ አበሻ "አንተ ለምንድነው ሚስት የማታገባው?" ሲለው እሱም "አንተ ይህን አታውቅም እንዴ? እዚህ የሀገራችን ሴት ሁሉም የተያዘ ነው:: ያለኝ ተስፋ ያ በየግዜው ሚስት ከሀገር ቤት የሚያስመጣውን ዘዴ እየተጠቀምኩ እኮ ነው። አሁን ደግሞ 4ኛ ሚስት ለማስመጣት በፕሮሰስ ላይ ነኝ" አለው ይባላል::[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ሶስት (3) ሰላዮች ይመረጡ ተባለና ኢትዮጲያዊ፣ ጣሊያናዊ፣ እንግሊዛዊ የዘመኑ ስላይ በመባል ተመረጡ። ከ እነሱም ውስጥ እስቲ ማነው የበልጠ ፈታንና ቀልጣፋ ተብሎ ፍየል አምጡ ተብለው ሲላኩ[/justify] [justify]እንግሊዛዊው - ወዲያው ከች አደረገ[/justify] [justify]ጣሊያናዊው - በንጋታው ከች አረገ[/justify] [justify]ኢትዮጲያዊው - ስድስት ቀን ቆይቶ አፍዋ ደም በደም የሆነች ውሻ ከች ሲያደርግ "ምንነካህ አንተ?" ሲባል አይ በቃ አምናለች እኮ አለ:: (ውሻዋን ደብድቦ ፍየል ነኝ ብላ አሳምኗታል)[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************[/justify] [justify].
አዛውንቱ ጣሊያን ሀገር ብዙ ነገር አይተዋል:: ካዩዋቸው ነገሮች በጣም የወደዱት ቢኖር ግን የባለጊውን ፊልም ነው:: ታዲያ አንድ ቀን ፊልሙን በጥሞና እየተክታሉ ሳለ አንዷ ትመጣና እንዴ! አባባ! እርስዎ ትልቅ ሰው አደሉ እንዴ? ይህን የባለጌ ፊልም ያያሉ? ስትላቸው ባአባባሏ የበሸቁት አዛውንት "ዝም በይ! ምላሰኛ! ምላስ እዚህ ስንት ቁም ነገር ይሠራበታል መሰለሽ:: አንቺ ግን ዝም ብለሽ ታወሪበታለሽ" አልዋት ይባላል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************[/justify] [justify].
ሮማ ውስጥ ካሪታስ የሚመገቡ ሁለት ጓደኛሞች ሁልግዜ ምግብ ለመብላት በተራ በተራ ነው። የሚሄዱት እና ቀድሞ የበላው ምን እደሆነ የሚነግረው በምልክት ነው።[/justify] [justify]ያልበላው ፡- ምን ነበር ዛሬ?[/justify] [justify]በልቶ የመጣው ፡- "ዳ" ነው ይለዋል።[/justify] [justify]ያልበላው ፡- አሀ ዳቦ ነው ማለት ነው ይልና እሱም ሊበላ ይሄዳል።[/justify] [justify]በሌላ ቀን ያልበላው ፡- ዛሬስ ይለዋል[/justify] [justify]በልቶ የመጣው ፡- "ፓ" ነው ይለዋል[/justify] [justify]ያልበላው ፡- ፓስታ ማለት ነው። ብሎ ሊበላ ይሄዳል[/justify] [justify]በሶስተኛው ቀን ያልበላው ዛሬስ ሲለው[/justify] [justify]በልቶ የመጣው ፡-"ዝ" ነው ይለዋል[/justify] [justify]ያልበላው ፡- ደንግጦ ዝልዝል ተደርጎም አይታወቅም ብሎ ሲሮጥ ይሄዳል እዛም ሲደርስ ዝግ ነው ለካስ። "ዝ" ያለው ዝግ ማለቱ ነው[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንድ አባት ልጃቸውን ለመጠየቅ ጣሊያን ይመጣሉ:: ከዚያም ልጃቸው ሁሉግዜ ማታ ማታ ጥላቸው ወደ ውጭ እያመሸሽ ትመጣለች::[/justify] [justify]ይህንን ያዩ እና በሁኔታው የተቆጡ አባት "ልጄ ሆይ! ምነው ማታ ማታ ልክ እንደሀገሬ ሰካራም ሰው እያመሸሽ ትገቢያለሽ ጥሩ እኮ አይደለም" ሲሏት[/justify] [justify]ልጃቸውም "አባዬ ይህ እኮ አውሮፓ ነው:: ልትቆጣጠረኝ አትችልም" አለቻቸው::[/justify] [justify]ይህንን የሰሙ አባት እምምምም... ብለው ልጃቸውን ከጠየቁ ከወር በኋላ ወደ አዲስአበባ ተመለሱ:: ከዚያም ከአንድ ዓመት ብኋላ ደግሞ ልጃቸው ወደ ኢትዮጲያ ትሄዳለች:: ማታ ማታ ዙረት የለምደች ልጅ አምሽታ ቤት ስትገባ አባቷ ልክ እንደገባች በጥፊ ያልሷታል:: ከዚያም ጥፊ የቀመሰችው ልጅ አባቷን ምነው አባዬ ምን አደርኩ በጥፊ መታሃኝ ስትላቸው አባትም "ይሄ እኮ ኢትዮጲያ ነው" አሏት ይባላል::[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
ልጆቻቸውን ለመጥየቅ ሮማ የመጡ ሁለት እናቶች አውቶቢስ ፌርማታ ጋ ይገናኛሉ:: አንዷ 5 ቁጥር አውቶቢስ ስትሆን ወደቤት የምትወስዳቸው የአንድኛዋ ደግሞ 8 ቁጥር አውቶቢስ ነበር የምትወስዳቸው:: እና አጋጣሚ ሆኖ 58 ቁጥር አውቶቢስ ትመጣለች:: ሴቶቹ አቤት መታደል ሁለታችን የምትወስድ አውቶቢስ በአንድ መጣችልን ይሉና ተሳፍረው ጥፍት አሉ:: ያው ቀኑን ሙሉ ብዛው አውቶቡስ እየዞሩ እያለ ያቺ አምስት ቁጥር የምትጠብቀዋ ረዥም ፎቅ አይታ ፎቁን ትቆጥር ጀመር:: 1 - 2 - 3 - 4 ... ሲቆጥሩ የሰማ አንድ ጩልሌ መጣና "ስንት ቆጠሩ?" ብሎ ጠየቃት:: "15" ብላ መለሰች:: ጩልሌው ሂሳብ አወራረደና 2 ኤውሮ ላንድ ፎቅ! 15 ፎቅ ስለቆጠሩ ሰላሳ ኤውሮ ይክፈሉ!" ብሎ ዓይኑን አጉረጠረጠባቸው:: እሷም "እሺ እሺ ብላ ከፍላ ተገላገልችው:: በኋላ ጓደኛዋን "ሸወደኩት እኮ!" አለቻት:: ጓደኛዋ "እንዴት?" ብላ ስትጠይቃት እሷም "25 ፎቅ ነበር የቆጠርኩት"
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.[/justify] [justify]ኢትዮጲያ ውስጥ ገጠር ትኖር የነበረች አንዲት ልጅ ጣሊያን ሀገር መጣችና አንድ ቀን አስቤዛ ለማድረግ ወደሱፐር ማርኬት ወጣ አለች። ከዚያም ገባችና የምትፈልገውን ነገሮች መፈለግ ጀመረች። ይህች ሰው በአይምሮዋ ያለውን ነገር ፈልጋ ማግኘት አልቻለችም ነበር። ከዚያም ገራ ተጋብታ ሳለ አንዱ ሠራተኛ ምን እያደረገች እንድሆነ ግራ ተጋብቶ ሲጠይቃት የምትፈልገውን እቃ በጣሊያንኛ ቋንቋ ማውቅ ስላልቻለች እጁን ጎትታ ወስዳ እንቁላሉን በእጇ ይዛ "dove la madre di questo uovo?" ብላ ቁጭ።[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************[/justify] [justify].
አንዱ ገና ከአገርቤት እዚህ ጣሊያን እንደመጣ ለጭፈራ ከጓደኞቹ ጋር ወጥቶ "እባካችው እኔ ፈረንጅ መቅመስ እፈልጋለሁ እንደምንም አገናኙኝ" አላቸው:: እነሱም "እራስህ ሞክር አትፍራ" አሉት:: እሱም ፍለጋውን ተያይዞ ከአይናችው ተሰውሮ ያገኘውን ይዞ ሄድዋል:: ስሟም ሮዛ (Rosa) ነበር የምትባለው:: ታዲያ አልጋ ላይ ይዝዋት በሆድዋ ተኛችበት:: ከዛ እሱም ስራውን ይቀጥላል:: መብራት አጥፍቶ ስለነበር ሆድዋን እይዛለው ብሎ ከፊት ያለውን እቃዋን ይይዛል:: ከዛ ደንግጦ "ሮዚ በሳሁሽ ወይኔ በሳሁሽ" ማለት ለካስ ሮዚ ወንድ ኖርዋል::
.
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************
.
አንዱ በቅርቡ ጣሊያን ህገር ይመጣና ልክ በ1ወሩ 100 ኤውሮ ወደ አገርቤት ላከና አባቱን በል አባዬ ወደ ኢትዮ ብር ሲለወጥ 1000 ብር ይሆናልና አንድ ነገር አድርግበት አላቸው:: በ3ኛ ወሩ ሲደውል አባቱ ምነው ልጄ የት ጠፋህሳ?[/justify] [justify]አባዬ እኔ ያለሁበት ከተማ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ ስለደረሰ ነው ይጠፋሁት።[/justify] [justify]አባትዬውም እህ የሞተና የተጎዳ ሰውስ አለ?[/justify] [justify]ልጃችውም አዎ 100 የሚሆኑ ሞተዋል[/justify] [justify]አባትዬውም ስለዚህ ወደእኛ ሲቀየር 1000 ሰው ሞቷል ማለት ነው?[/justify] [justify].
ለመሣቅ (ከአብራሃም.ዘ)
******************************************[/justify] [justify].
ዘበርጋ ማይክል ክሚባል ጛደኛው ጋር አሪዞና ውስጥ የሚገኘውን የግራንድ ካንየን ሽለቆ ለመጎብኘት ይሂዳል። ታድያ ሽለቆዉን በመጎብኘት ላይ እንዳሉ ማይክልን እየውልህ እንግዲህ አሁን ድምጺ ከፍ አድርገ ስሜን ብጣራ የገደል ማሚቶው ስሜን 10 ጊዜ ይደጋግመዋል ይለዋል ለዘበርጋ:: እንዳለውም ጮክ ብሎ ማይክል ሲል ሸለቆዎም ተከትሎ .. ማይክል.. ማይክል.. ማይክል.. አለ:: ይህን የተገነዝበ ዘበርጋም ለምን ታድያ እኒም አልሞክርም ይልና እሱም በተራው ጮሆ ዘበርጋ ብሎ ሲጮህ ግራንድ ካንየኑ ምን ብሎ መለሰለት መሰላችሁ "I beg your pardon?" ብሎ መለሰለት::[/justify][/JUSTIFY]

User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

Re: በጣሊያን ስደተኛ አበሻ ላይ ቀልድ

Unread post by zeru » 13 Jan 2010 16:15

I love it I love it . Thanks Selam u made my day. :D

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

Re: በጣሊያን ስደተኛ አበሻ ላይ ቀልድ

Unread post by selam » 22 Jun 2010 19:47

[center]በኢሜልና በኮሜንት ከደረሱን ውስጥ[/center]
[center]Image[/center]

[center]ክዚህ በታች ያለው ፅሁፍ በየጊዜው በኢሜል እና በኮሜንት የደረሱንን አሰባስበን እና መርጠን ያወጣናቸው ቀልዶች ናቸው። ለገፁ ቅንብብር እንዲያመቸን በማለት በፅሁፋችሁ ላይ የነበሩትን ተጨማሪ መልዕክቶችና ሰላምታችሁን ከውስጡ በመለያየት ቀልዶቹን ብቻ እንዲወጡ አድርገናል። ለወደፊትም አስፈላጊውን ብቻ ከጽሁፉ ውስጥ በመምረጥ ከስማችሁ ጋር እንዲወጣ ይሆናል። [/center]
አገር ቤት ውስጥ የፈረንችና የሀበሻ ዶሮ ይጣላሉ። ጥላቸው የተጀመረው ከፈረንጇ ዶሮ ነው። የፈረንጇ ዶሮ የእኔ እንቁላል ትልቅ ስለሆነ በ 50ሳ ይሸጣል ያንቺ ግን ትንሽ ስለሆነ በ 40ሣ ይሸጣል እያሉ ሲከራረሩ ሀበሻዋ ዶሮ ትናደድና
"እኔ ለ 10ሣንቲም ብዬ ቂጤን አላሰፋም?" አለች ይባላል
ዮናስ (ቦሎኛ)


አንዱ አበሻ ልጅ ዋና ለመማር piscina ይሄድና ሲዋኝ ይሰምጥና መውጣት ያቅተዋል። ከዚያ እዚያው ውሀ ውስጥ እየተንፈራገጠ በአጠገቡ ሰው እንዳለ ሲመለከት አንድ ጠና ያሉ ሰውዬ በpiscinaው አጠገብ ሲያልፉ ያያል። የሰጠመውም ልጅ "አባባ aiutare! ... Io morire! ... እያለ ሲጮህ ሰውዬው ደግሞ ዞር አሉና እንዲህ አሉት " ጣሊያንኛ ከመማርህ በፊት ዋና አትማርም ነበር?" አሉት።
Endale T/Mariam (Roma)


3 ሆነው ባጠፉት ከባድ ወንጀል መሰረት ሶስቱም የሞት ፍርድ ይፈረድባቸዋል አሉ:: እናም በምን መንገድ እንደሚሞቱ የመምረጥ እድሉ ይሰጣቸዋል:: በመርዝ፣ በጋዝ ታፍኖ፣ በስቅላት፣ በጥይት፣ በኤድስ ቫይረስ መወጋት፣
1ኛው "በስቅላት" አለ።
2ኛው "በጥይት" አለ።
3ኛው "በኤድስ ቫይረስ መወጋት" አለ።
ታዲያ ፍርዱ አልቆ ከተከናወነ በኋላ ይሄው 3ኛው ቫይረሱ የተወጋበትን ቂጡን እያሻሸ ምን አለ መሰላቹ ...
"ሸወድኩዋቸው እኮ!" አለ።
እንዴት? ሲሉት ጊዜ
"ኮንደም አድርጌያለሁ"
አብራሃም (ቦሎኛ)


በሽተኛው ዓይን ዶክተር ጋ ይሄዳል:: ዶክተሩ ከመረመረው በሁዋላ ዓይኑ መቀየር እንዳለበት አምኖ ለጊዜው የተገኘው የድመት ዓይን ስለነበረ በዚሁ ይቀይርለታል::
ዶክተር :- "እህ አሁንስ በደንብ ታያለህ ? ንገረኝ ..." ማለት
በሽተኛ :- "በሚገባ ዶክተር:: አያለሁ ብሎ መመለስ"
ዶክተር :- "ምን ይታይሃል?" ሌላ ጥያቄ
በሽተኛ :- "ዓይጥ ነዋ::" ብሎ ዕርፍ
ከቤ


3ት እብዶች ከአማኑኤል ሆስፒታል ሸውደው ለማምለጥ ወስነው መውጫው በር ሲደርሱ በአጋጣሚ ዘበኞቹ የሉም ነበር። በቃ ዘበኞቹ የሉም ማንን እንሸውዳለን? ብለው ወደ ውስጥ ተመለሱ::
Ted 85


ተማሪ :- ባልሰራሁት ስራ ይቀጡኛል ይገርፉኛል?"
ቲቸር :- "እረ እኔቴ እንዴት ሰው ባልሰራው ስራ ይቀጣል? … ይህማ የማይሆን ነገር ነው አልገርፍህም!"
ተማሪ :- "ይምሉልኛል?"
ቲቸር :- "ሙ ት ልጄ! አልመታህም! መድሀኒያለምን! ባልሰራኸው ስራ በፍፁም አትመታም! እንዴ!!!"
ተማሪ :- "እንግዲያውስ ቲቸር አመሰግናለው ዛሬ homework አልሰራሁም"
ከቤ


ሁለት እብዶች ናቸው እየሄዱ ይጨዋወታሉ። አንዱ እብድ አንድ በጣም ትልቅ ተራራ አየና ያንን ተራራ እንግፋው አለው። ለሌላኛው እሱም እሺ ብሎ ላት ላት እስኪላቸው ድረስ ጃኬታቸውን አውልቀው ይገፋሉ። እንደአጋጣሚ አንዱ ሞጭላፋ አይቶቸው በልቡ እየሳቀባቸው ጃኬታቸውን ሞጨለፈው። ትንሽ ቆይተው አንዱ እብድ ዞር ሲል ጃኬታቸው የለም።
"አንተ ጃኬታችንስ?" ቢለው
ያኛው ደሞ ትንሽ የባሰበት ስለነበር "እንዴ አንተ ደሞ በጣም ብዙ እየገፋን በጣም ርቀን ሰለሄድንኮ ነው ማየት ያልቻልነው" አለው ይባላል
ከቤ


ባል ሊሞት ሲያጣጥር ሚስቱን ይጠራና እኔ ስሞት ብዙ ማዘን የለብሽም:: ያለባልም መቅረት የለብሽም:: እንዲያውም ጎረቤታችንን ዘነበን አግቢ:: አደራ ይላታል:: ሚስትም መለስ አድርጋ እንዴት እንዲህ ትለኛለህ? እኔ ፍቅር እንጂ የወንድ ቃር የያዘኝ መስሎሀል? ደግሞ ባገባስ እንዴት ዘነበን አገባለሁ እሱ ስንት ዘመን ሊገልህ የሚፈልግ ጠላትህ አይደል? ብላ ታፈጥበታለች:: ባልም እያቃሰተ ጥላቴማ መሆኑን መች አጣሁት እንደኔው ጥብስ እድርግርሽ እንድትገይልኝ ነበር እንጂ ብሏት እርፍ::
ቅጣው ሀ/ማሪያም (German)


ሁለት እብዶች ተገናኝተው በመንገድ እየተጫወቱ ሲሄዱ አንድ ነገር ተቆልሎ ይመለከታሉ:: እነሱም ሁኔታው ገርሟቸው አጎንብሰው ሲመራመሩ ሁኔታውን ለመረዳት ስላልቻሉ ሁለቱም በጣታቸው ደንቁለው ቀመሱት። ወደ አፍንጫቸው ጠጋ አድርገው ሲያሸቱት አር መሆኑን ሲያውቁ ጊዜ "እፍ እፍ እፍ እፍ እንኳን በእግራችን ያልረገጥነው" አሉ ይባላል።
ዝናሽ


ሁለት ጓደኛማቾች ቁጭ ብለው ጫት እየቃሙ ብው ብለው መርቅነዋል::
አንደኛው በድንገት ብድግ አለና "በዓለም ላይ ያለውን ወርቅ በሙሉ ልገዛው ነው" ሲል
ቀበል አድርጎ "አይ አልሸጥም" አለው::
አብራሃም (ቦሎኛ)

Post Reply

Return to “Jokes and Funny stuff ...ቀልዶች እና አዝናኝ ርዕሶች”