funny....

User avatar
selam
Leader
Leader
Posts: 175
Joined: 25 Aug 2009 01:59
Contact:

funny....

Unread post by selam » 15 Dec 2009 20:09

ሃሎ ይሰማኛል፡፡
- ሃሎ.... እንግዲህ ክቡር ሚኒስትር ላስቸግረዎት... ሰውየው ለእናቴ እና ለቤተሰቤ ለአውደ ዓመት የሚሰጥ ገንዘብ ይሰጥዎታልና እንድትቀበሉት፡፡ ወዲያው ይስጡልኝ፡፡ እናቴ ወይም እህቴ ይመጣሉ፡፡ ይቅርታ ሌላ ወዳጅ የለኝም ካለ እርስዎ፡፡

- እንዴ ችግር የለም፡፡ ምን ችግር አለ? ተቀብሎ መስጠት ምን አለበት? ላከውና እኔ ወዲያውኑ ለእትየ ስርጉት እሰጣቸዋለሁ፡፡
- አመሰግናለሁ፡፡ እንግዲህ በትክክል እንድትጠቀምበት ይንገርዋት፡፡ በአሁኑ ጊዜ የዶላር ምንዛሪ ጨምሯል፡፡ እንደዱሮው በስምንትና በዘጠኝ ብር የሚመነዘር እንዳይመስላት፡፡ ከአሥራ ሦስት ብር በላይ ነው፡፡ ለበግ ለዶሮ ብቻ ሳይሆን ቤቱንም በሙሉ ታድስበት፡፡ ይንገርዋት፡፡
- እሺ እሺ እነግራቸዋለሁ፡፡
- አመሰግናለሁ፡፡ አምስት መቶ ዶላር ነው የምልከው ክቡር ሚኒስትር፡፡ ለሁሉም ጉዳይ ይበቃታል፡፡
- እሺ እሺ ላክ፡፡ ቤተሰብክን መርዳትህ ጥሩ ነው፡፡ ቻው፡፡
- እሺ ደህና ይሁኑ ክቡር ሚኒስትር፡፡
(ከአሜሪካ የተደወለላቸውን ስልክ ዘግተው ወደ ሳሎን ሲመለሱ የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የስልኩን ንግግር ያዳምጡ ነበርና ጠየቁ)
- ማን ነው?
- የእትየ ስርጉት ልጅ ነው፡፡
- ምን ፈልጎ ነው?
- ለእናቱ ለገና በዓል ገንዘብ ሊልክ ፈልጎ ተቀብለህ ስጥልኝ ብሎኛል፡፡
- ጥሩ አደረገ፡፡ ቁም ነገረኛ ነው፡፡
- ሰውዬው ሲያመጣ ለእትየ ስርጉት እንድንሰጣቸው አስታውሽኝ፡፡ እባክሽን እንዳልረሳ፡፡ ለበግና ለዶሮ ብቻ አታድርጊው ብለህ ንገርልኝ ብሏል፡፡
- ታዲያ ሌላ ለምን ይሆናል?
- ቤቱን በሙሉ ታድስበት፣ ሰርቪስ ትስራበት፣ ቧንቧውን ትቀይረውና በአጠቃላይ ቀለም ይቀባ ብሏል፡፡
- ስንት ሺህ ዶላር ነው የላከው?
- የምን ሺህ ነው? አምስት መቶ ዶላር ብቻ ነው፡፡
- እና በአምስት መቶ በግና ዶሮ ተገዝቶ ሰርቪስ ተሰርቶ፣ ቀለም ተቀብቶ.. ወይ አለማወቅ፡፡
- ምን ሆንሽ ረጋ በይ እንጂ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የዶላር ምንዛሬ ሰማይ እንደወጣ ማወቅ አብሽ፡፡
- የዶላር ምንዛሪ ሰማይ እንደወጣ እንጂ የኑሮ ውድነቱ ሰማይ እንደወጣ አይታያችሁም፡፡
- ምን አገናኘው?
- ቀለም ይቀባ ከተባለ ቀለም ሊገዛ አይደለም? የቀለም ዋጋ ሰማይ እንደተሰቀለ ታውቃለህ? ሰርቪስ ሲታደስ አሸዋ፣ ሲሚንቶ፣ ብረት ቀለም ሲገዛ አምስት መቶ ዶላር ምንድናት?
- እንዴ?
- ምን እንዴ ትላለህ? ገበያ ላይ የምውለውኮ እኔ ነኝ፡፡ እናንተ ሁኔታው አበረታች ነው ትላላችሁ፤ እኛ ገበያ ስንሄድ ደግሞ የምንይዘው የምንጨብጠው እናጣለን፡፡ መታጠቢያ ቤቱን ላሰራው ብዬ ጀምሬ ተስፋ ቆርጨ እንደተውኩት አላወቅህም? ዱሮ አስራ አምስት ሺህ ብር ይበቃ የነበረው አሁን በሰባ ሺህም አይሰራውምና ተውኩት፡፡
- ምን አስጨነቀኝ? ገንዘቡ ከተሰጠኝ ለቤተሰቡ መስጠት ብቻ ነው ሥራዬ፡፡
- ደግሞ ለባልዬው እንዳትሰጥ ይጠጡበታል፡፡ ለእናትዬው ስጥ፡፡
- እሱም ያለው ለእናቴ ወይም ለእህቴ ነው፡፡ ለነገሩ ከሰውየው ጋር ብዙም አንስማማም፡፡ ሃይለኛ ናቸው፡፡
- በቀደም ስትጨቃጨቁ ነበር፡፡
- እንዴ ብርቱካን ሚዴቅሳን ካልፈታህ ብሎ አሣሬን አሳየኝ፡፡
- አይመለከተኝም አትለውም፡፡
- አልኩትኮ፡፡ በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ እኔ እንደማልችልና እንደሚከለክሉኝ ነገርኩት፡፡
- ምንድነው በተዘዋዋሪ ማለት?
- ፍታት ሲሉኝ ..እሷን ከመፍታት ሚስቴን መፍታት.. ይቀለኛል አልኩት፡፡
- የከተማው ቀልድ አንተም ጋ ደረሰ፡፡ ሆሆ መቀለጃ አደረግከኝ አይደል? በል በል ልተኛበት፡፡
(ጧት ቢሮ እንደገቡ በሚኒስትር መሥሪያ ቤታቸው የሚገኘውን የፕሮጀክት ኮሚቴን ሰበሰቡ)
- እንግዲህ በእቅዳችን መሰረት ፕሮጀክቱን መጀመር አለብን፡፡
- አንዳንድ ነገሮች እንደገና ማየት አለብን ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ለምን? ፕሮጀክት ጠየቅን፣ ባጀት ጠየቅን ተፈቀደ፡፡ አሁን ሥራ ላይ ማዋል ብቻ ነው፡፡
- እኮ ፕሮጀክቱንና የተፈቀደውን ባጀት እንደገና ትንሽ እንየው ማለቴ ነው፡፡
- የፕሮጀክቱ ኤክስፐርት የምትባለው አንተ፣ ባጀቱን የጠየቅከው አንተ፡፡ በጠየቅከው መሠረት ተፈቀደ፡፡ አሁን ለምን ቅሌን ጨርቄን ትላለህ?
- ጨርቄን ቅሌን አይደለም ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ምንድነው ታዲያ? እስቲ አስረዳኝ፡፡
- ፕሮጀክቱን ካስፈቀድንበት እስካሁን ድረስ እንዲያውም ባጀቱ ከተፈቀደ እስካሁን ድረስ የማቴሪያሎቹ ዋጋ 400 ፐርሰንት ጨምሯል፡፡
- እና?
- እናማ ክቡር ሚኒስትር ባጀቱ ያሰብነው ፕሮጀክት አንድ አራተኛውንም አያሠራንም፡፡
- ማን ነው የዋጋውን ዝርዝር የሰጣችሁ?
- ኮንትራክተሩ፡፡
- አንድ አጭበርባሪ ኮንትራክተር ዋጋ ጨመረ ብለህ የመንግሥት የልማት አቅጣጫ ልታስተጓጉል ትፈልጋለህ?
- እንደዚያ አይደለም ክቡር ሚኒስትር፡፡ ገበያው ላይ እንዳረጋገጥነውና እንዳጠናነውም የዋጋ ጭማሪው እውነት ነው፡፡
- መጀመሪያውኑ የዋጋ ለውጥ አይፈቅድም፡፡ ልዩነት ቢኖረውም ልዩነቱን መንግሥት አይሸፍንም ብለን ለምን አልተዋዋልንም? ያንተ ጥፋት ነው፡፡
- ክቡር ሚኒስትር አድርገናል፡፡ እንደዚያ ባናደርግ ኖሮ ስንት ተጨማሪ ሚልዮን በተጠየቅን ነበር፡፡ የጎማ ዋጋ ጨምሯል፣ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል፡፡ ይህ ሁሉ ኮንትራክተሩ የሚሰራበት ነው፡፡ አሁን የምንጨምረው እኛ ራሳችን ገዝተን እናቀርባለን ባልነውና ዋጋ ቢቀየር ይሸፈናል ባልነው መሠረት ነው፡፡
- ወይ ጣጣ..
- ጣጣ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
- እስቲ ዛሬ ሳይቱ ጋ ሂድና ምን ማድረግ እንደሚቻል አጥንተህ አቅርብልኝ፡፡
- እሺ፡፡ ለጠቅላላ አገልግሎት ይንገሩልኝ፡፡
- በወር አንድ ሺህ ብር ብቻ ይጨርስ የነበረ መኪና አሁን ሁለት ሺህ አይበቃውም፡፡ ጠቅላላ አገልግሎት ሚኒስትሩ ካልፈቀዱ አልሰጥም ብሎናል፡፡
- ሆ...ሆ..፡፡ በል እሺ፡፡ ይህን እኔ አሳውቀዋለሁ፡፡ እኔም አንተም በሚቀጥለው ወር ሕንድ አገር ለስብሰባ ስለምንሄድ እስከ ነገ ጨርስ፡፡
- እሺ ክቡር ሚኒስትር፡፡ ነገር ግን አንድ ያልሰሙት ኢንፎርሜሽን ያለ መሰለኝ፡፡
- ምን ኢንፎርሜሽን?
- የሕንዱ ስብሰባኮ ተሰርዟል፡፡
- መቼ ሰረዙት?
- ባለፈው ሣምንት፡፡
- ለምን?
- ስፖንሰር ጠፋ፡፡
- እንዴት ጠፋ?
- የኢኮኖሚ ቀውስ.. የኑሮ ውድነት..
- ጣጣ... ለካ እውነትዋን ነው፡፡
- ማን? ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ባለቤቴ ስለኑሮ ውድነት ስታወራ እውነት አይመስለኝም ነበር፡፡
- እኔ የሆንኩትን ብነግርዎት ያዝኑልኛል፡፡
- ምን ሆንክ ደግሞ?
- ይኸውልዎት ትናንት ቅዳሜ ቃል የገባሁላቸውን ልጆቼን ይዤ ወደ ሱፐር ማርኬት ሄድኩ፡፡ መጫዎቻና ልብስ ልገዛላቸው፡፡
- እሺ፡፡
- ይዤው የሄድኩት ገንዘብ ለመጫወቻው አልበቃኝም፡፡
- ለምን?
- የኑሮ ውድነቱ..
(የዕለቱ ሥራቸውን ጨርሰው ከቢሯቸው ሲወጡ ፀሐፊያቸውን አነጋገሯት)
- እንኳን ደስ አለሽ፡፡
- ምን አገኘሁ ክቡር ሚኒስትር?
- ሕንድ አገር ስለምሄድ በሠርግሽ አልገኝም ብዬ ነበር፡፡ አሁን የሕንዱን ስብሰባ ስለተሰረዘ ሠርግሽ ላይ እገኛለሁ፡፡ ለዚህ ነው እንኳን ደስ አለሽ ያልኩሽ፡፡ የራስሽን አስተካክለሽ የእኔን አደናቀፍሽ፡፡
(በጣም ሣቀች)
- ምንድነው እንዲህ የሚያስቅሽ?
- ክቡር ሚኒስትር ሕንድ አገር ቢሄዱ ይሻለኝ ነበር፡፡
- ለምን?
- ሠርጌን እኮ ሰረዝኩት
- ለምን?
- አልተቻለም፡፡ ጓደኞቼ ሲያገቡ ከነበረው አንፃር አሁን ወጪው በአስር እጥፍ ጨመረ፡፡
- እና?
- እናማ በቃ አንደግስም፡፡ ዝም ብለን እንደባልና ሚስት መርቁን ብለናል፡፡
- ባልሽ (እጮኛሽ) ተስማማ?
- ወዶ ነው?
- ሠርግም እስከዚህ ድረስ ውድ ሆኗል በይኛ?
- እንዴ ክቡር ሚኒስትር እስኪ እንሞክረው ብለን ለተነሳነው እኛ በፕሮግራም ለያዙት ሰውዬም እየከበደ ሳይሄድ አልቀረም፡፡
- ሃ...ሃ...ሃ ተጫዋች ነሽ፡፡ ጥሩ ነው፡፡ ትክክለኛ ውሳኔ ነው፡፡
- አመሰግናለሁ፡፡
- ቻው፡፡
(ወደ ቤታቸው ለመሄድ መኪናቸው ውስጥ ገቡ፡፡ ሾፌራቸው ፈራ ተባ እያለ ጠየቀ)
- ክቡር ሚኒስትር ለሶስት ለአራት ቀን ፈቃድ ፈልጌ ነበር፡፡
- ለምን?
- እናቴን ሸንኮራ ልወስዳት፡፡
- ሸንኮራ ምን አለ?
- ታማብኝ ለጠበል ልወስዳት ፈልጌ ነው፡፡ እኔ አድርሼያት እህቶቼ ያስጠምቋታል፡፡
- ሐኪም ቤትስ?
- ሐኪም ቤትማ ወስጃት ነበር፡፡ እሱ ስላልተሳካ ነው፡፡
- ለምን አልተሳካም?
- ክቡር ሚኒስትር በአንድ ማሽን ልትታይ ሦስት ሺህ ብር አሉን፡፡ ሦስቴ ታይታ ንብረታችንን ሸጠን አስር ሺህ ብር ያህል ከፈልን፡፡
- ውድ ሆነ?
- ክቡር ሚኒስትር ውድ የሚለው ቃል አይገልፀውም፤ ዝርፊያ ነው እንጂ፡፡
- እና?
- እናማ ሆስፒታል ሄዶ መታከም ከእኛ አጀንዳና ከእኛ ራዳር ውጭ ነው፡፡
- ለምን?
- ውድነቱ፡፡
- እሺ ሂድ፡፡ ለአራት ቀን ተፈቅዶልሃል፡፡ ካልበቃህም አትጨነቅ፡፡ ለእናትህ በቂ ጊዜ ስጣቸው፡፡
- ሌላው ሁሉ ሲወደድ ርካሽ ነገር ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የቀረችው እሷ ብቻ ናት፡፡
- ምን?
- ጊዜ..
- አንተ ትቀልዳለህ፡፡
(ቤት ገቡ ክቡር ሚኒስትር፡፡ ልጆቻቸው ለፈተና እንደሚያጠኑ ገምተው ልብሳቸውን ቀይረው ቴሌቪዢን ለማየት ሳሎን ተቀመጡ፡፡ ጭር ሲልባቸው ተጣሩ፡፡ ሠራተኛዋ መጣች)
- ልጆቹ እያጠኑ ናቸው?
- እያጠኑ አይደለም፡፡ አሟቸዋል መሰለኝ መኝታ ቤት ናቸው፡፡
- ጥሪያቸው (ልጆቹ መጡ)
- እናንተ ነገ ፈተና ትጀምሩ የለም ወይ? አታጠኑም?
- አንፈተንም፡፡
- ለምን አትፈተኑም?
- የሁለተኛው ተርም ክፍያ ስላልተከፈለ አትፈተኑም አሉን፡፡
- ማን ነው እንዲህ ያላችሁ?
- ትምህርት ቤቱ ያልከፈላችሁ እንድትወጡ አሉን፡፡ የመጨረሻ የመክፈያ ጊዜ ዛሬ ዕድል ሰጥተውናል፡፡
- በቃ ችግር የለም እንከፍላለን፡፡ ነገ ጧት እንከፍላለን፡፡ ካስፈለገ ደረሰኙን ጧት ታሳያላችሁ፡፡
- ገንዘብ ይዘሃል ዳዲ?
- አሁን በስልክ አሟላለሁ፡፡ ስለገንዘቡ አታስቡ፡፡
- ምንድነው እንደዱሮው እንዳይመስልህ፡፡
- የሚከፈለው ገንዘብ?
- ለሁለታችሁ ለአንድ ተርም ስምንት ሺህ ነው አይደል?
- ነበረ አሁን ግን በተርም አስራ ሁለት ሺህ አድርገውታል፡፡
- ምን..

Post Reply

Return to “Jokes and Funny stuff ...ቀልዶች እና አዝናኝ ርዕሶች”