ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
ሆስፒታላችን ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ
አመልካቾችን ለሆስፒታላችን ሜዲካል ዳይሬክተርነት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል!
1. ኮብል ስቶን የሰራ/ች
2. በማንኛውም ጥቃቅን እና አነስተኛ ስራዎች ተደራጅቶ የሚያውቅ
3. 10/90,20/80 ወይም 40/60 የኮንዶሚኒየም ቁጠባ ደብተር ማሳየት የሚችል
4. ቢያንስ ለ15 አመታት ETV ያለማቋረጥ ማየቱን ከቀበሌ መረጃ ማቅረብ የሚችል
5. ቢያንስ በአንድ ሊግ (የሴቶች ሊግ:የወጣቶች ሊግ:ፕሪሚየር ሊግ) የታቀፈ/ች
6. ስለ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጥንፍፍ ያለ ጥልቅ እውቀት ያለው
7. ግንቦት ሰባትን ጨምሮ ሁሉንም ጸረ ሰላም ሃይሎችን ለመዋጋት ቁርጠኝነት ያለው
8. በምርጫ 97 ቅንጅትን እንዳልመረጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
9.በህገ መንግስቱ፣በአንቀጽ 39፣በኤርትራ መገንጠል እንዲሁም ኮኮብ ባለው ባንዲራ የሚያምን
10.የአቶ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ጊዜ ስቅስቅ ብሎ ማልቀሱን ከቀበሌ ማጻፍ የሚችል
ማሳሰቢያ!
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ብታሟሉም ሆስፒታላችን ከመቀሌ የመጡ አመልካቾችን ካገኘ እናንተን ያለመቅጠር መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው!
የጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል
source © አለቃ ገብረ ኃና ልዩ የመዝናኛ ፔጅ! facebook
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
-
- Leader
- Posts: 692
- Joined: 08 Feb 2011 11:14
- Contact: