ሰባተኛ ፎቅ

selam sew
Leader
Leader
Posts: 692
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

ሰባተኛ ፎቅ

Unread post by selam sew »

ሰውየው ሰባተኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ሆኖ ንፋስ ይቀበላል። አካባቢውን እየቃኘ እያለ አንድ ሰው ምድር ላይ ሆኖ እጁን ሲያውለበልብለት ይመለከታል።
በድምፅ መደማመጥ ስላልቻሉ ምድር ያለው ሰውዬ ሰባተኛ ፎቅ ላይ ያለውን ሰውዬ በምልክት 'ና' ይለዋል።
ሰባተኛ ፎቅ ላይ የነበረው ሰውዬ ስለሰውዬው ማንነትና ስለፈለገው ነገር እያሰበ ከፎቁ ይወርዳል። የምድሩ ሰውዬ ጋር እንደደረሰም:
ፎቅ ላይ የነበረው: "አቤት ወንድሜ ምን ፈልገህ ነው?"
ምድር ላይ ያለው: ፊቱን አሳዛኝ ካደረገ በኋላ "ይቅርታ ጌታዬ አለፋሁዎት አይደል? ለማኝ ነኝ። እስኪ ስለ እግዚአብሔር ብለው ያለዎትን ይመፅውቱኝ"
ሲለው ሰውየው ከሰባት ፎቅ ድረስ በቁም ነገር ወርዶ በሰማው ነገር እጅግ ስለተበሳጨ ለማኙን ካልገደልኩ ብሎ አስቸገረ።
ትርምሱ በአገላጋዮች ከረገበ በኋላ ለማኙ ላይ እየዛተ ወደነበረበት ፎቅ ይመለሳል።
እየተመለሰ እያለ ግን ለማኙ የምሩን ተቸግሮስ ቢሆን እያለ እያሰበ ነበር።
መጀመሪያ የነበረበት ሰባተኛ ፎቅ ላይ ደርሶ ወደታች ሲመለከት ለማኙ አሁንም አንጋጦ ሲመለከተው ያያል።
ተስፋ ቆርጦ በረጅሙ ከተነፈሰ በኋላ ያፏጭና ለማኙን ይጠራዋል።
ለማኙ በደስታ እየተፍነከነከና የሰውዬውን ልብ ያራራለትን አምላክ እያመሰገነ ሰባተኛ ፎቅ ከወጣ በኋላ:
ምድር የነበረው (ለማኙ): እየተቅለሰለሰ "አቤት የኔ ጌታ?" ቢለው
ፎቅ ላይ ያለው (ተለማኝ): "እግዚአብሔር ይስጥልኝ!!!" ብሎት እርፍ!!!
*******


Source:Facebook
Post Reply

Return to “Jokes and Funny stuff ...ቀልዶች እና አዝናኝ ርዕሶች”