መዝገበ ቃላት ወ ዘመኑ

selam sew
Leader
Leader
Posts: 692
Joined: 08 Feb 2011 11:14
Contact:

መዝገበ ቃላት ወ ዘመኑ

Unread post by selam sew »

መዝገበ ቃላት ወ ዘመኑ

1.የኛ ቡድን----አርሰናል/ ሊቨርፑል/ ቸልሲ/ባርሴሎና
2.በጭቅ ----ብር ስጠኝ
3.አስበኧዋል----ኮረዳዎቻችን በየመሃሉ ጣል የሚያደርጓት አዝማች
4.ፖዝ አረገ----ፈዞ ቀረ
5.በካ----በቃ
6.ንካው----ሂድ
7.አይገርምክም----አይገርምህም
8.ሰርፕራይዝ----ህልመ ምዕራባዊያን የሆኑ እንስቶች ልብ የሚያደርቁበት ቃል
9.ሰጠኝ----“F” እና “D” ያመጣ ተማሪ አገኘሁ ላለማለት የሚጠቀምበት
10.ሜንጫ----ፌስቡክ ላይ ያሉ ሰነፎች የሚያስፈራሩበት ጉም
11.አንቺ----ለወንድም ሆነ ለሴት እንደየሁኔታው የሚያገለግል (የምታገለግል) መጠሪያ
12.አይ እሷ----አውሮፓ ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ ኳስ ተጫዋቾች የሚቆላመጡበት
13.ሼ ነው----ያሳፍራል
14.ፐብሊክ አድርገው----አታሾክሹክ
15.የኛ አስታዲዬም (በኛ ሜዳ)----ፍላይ ኢምሬትስ/ ኦልድ ትራ ፎርድ/ ሳንቲያጎ በርናባው
16.ዩ ኖው----የአይዶል ዳኞች ዘፋኙን ሊያወዛግቡ ሲሉ የሚጠቀሙበት መግቢያ
17.ላሞ----ሎል የፋራ ነው የሚሉ ቆየት ያሉ ፌስቡከኞች ስቂያለው ለማለት የሚጠቀሙበት
18.በተረፈ ሰላም ነው----ደዋይ ቻው ለማለት ሲከብደው የሚጠቀምበት ቻይንኛ
19.እስፖንዳ----የሴት ልጅ መቀመጫ
20.እስፖኪዮ----ፊት (በተለይ የሴት)
21.ብትጠራው አይሰማህም---- አንድ ሰው በጣም ሃብታም ነው ለማለት
22.ቀዩን ተጫነው----ስልኩን ዝጋው/ከፊቴ ዞር በል
23.እህ ገባ/ ኧረ ገባ ወይ----እያንቀላፉ ያሉወጣቶች ምግባቸውን (ጫትን) በጉጉት የሚጠባበቁበት የጠራራ ፀሃይ ጥያቄ
24.ፒን እንውጋ----አረቄ እንጠጣ
25.እንያዝበት----እንቃም
26.የገባው/የገባት----ጫት የሚቅም/የምትቅም የሚጠጣ/የምትጠጣ የሚዳራ/የምትዳራ
27.ገገማ----ከገባው/ከገባት በቃራኒ ያሉ
28.እርዝራዥ----የማይፈለገው/ የቀድሞው/ የተጣለው አባል/አካል
29.ዶክተር ኢንጅነር----የንግድ ስም
30.ሸኖ እንበርግድ----ሽንት እንሽና
31.ቫይበር የለህም?----ላንተ ገንዘብ አውጥቼ አልደውልም የሚለው አረፍተ ነገር ምትክ
32.ሻወር እንብላ----ገላችንን እንታጠብ
33.ኮካ----ኮተታም ካድሬ
34.አሸባሪ---- ጋዜጠኛ፣ብሎገር/ጦማሪ፣የሃይማኖት/የፖለቲካ መሪ
35.ዋው፣ላላ፣ስቲል እስካሁን፣አይ ስዌር፣አሜዚንግ፣ፕሊስ፣ታንኪው፣ፓራዶክስ፣ሪሊ፣ኦኬ፣ኦ ማይ ጋድ----ዲያስፖራና ትምህርት ቀመስ ላሜቦራዎች የሚጠቀሙት ሳውንድ ትራክ

ምንጭ: ፌስቡክ
Post Reply

Return to “Jokes and Funny stuff ...ቀልዶች እና አዝናኝ ርዕሶች”