ለሴት ልጅ ፍቅርን እንዴት ማሳየት ትችላለህ?

User avatar
zeru
Leader
Leader
Posts: 952
Joined: 19 Aug 2009 17:01
Contact:

ለሴት ልጅ ፍቅርን እንዴት ማሳየት ትችላለህ?

Unread post by zeru » 07 Aug 2014 16:57

*ለሴት ልጅ ፍቅርን እንዴት ማሳየት ትችላለህ?*

በነገራችን ላይ ፒያሳ አካባቢ ያሉ ነጋዴዎች ማንኛውንም ዕቃ በከፍተኛ ዋጋ እንደሚገዙ ታውቃለህ? ያው
ለጠቅላላ እውቀት ከፈለክ ብዬ ነው lol.

ወደ ዋናው ጉዳይ ልግባ! ለሴት ልጅ
ፍቅርን እንዴት ማሳየት ትችላለህ? አንድ ቀን surprise አደርግሻለሁ በልና
ቅጠራት:: በዛውም ቆንጆ የእራት ልብስና ሙሉ ጌጣጌጧን አድርጋ እንድትመጣ
ንገራት!
ከዚያም በሚያምር ፈገግታ ተቀብለህ በነፃነት ወደምትጫወቱበት ቦታ
ውሰዳትና "ወይን" እዘዝ::
ወይን እየጠጣችሁ በእጅህ እቅፍ አድርጋት; ቀስ ብለህም እጆቿን ማሻሸት
ጀምር::

አንገቷንና ደረቷን ቀስ እያልክ ሳማት:: አንገቷን ስትስማት እንዳያስቸግርህ
ያደረገችውን ሐብል አውልቀውና ጠረቤዛ ላይ አስቀምጠው!
ወደ ጆሮዋ ጠጋ በልና እንደምትወዳት በሹክሹክታ ንገራት:: ጆርዋን ለመሳም
እንዲያመችህም የጆሮ ጌጧን አውልቀህ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጥ::
እጆቿንም ለመሳም እንቅፋት እንዳይሆን አምባርና ብራስሌቷን አውልቀህ
ጠረጴዛው ላይ አኑር::
ሞባይሏንም እንዲሁ ወደጠረጴዛው!
ከዚያም ቀስ ብለህ ጆሮዋን ንከሳት...(አንተ'ኮ ጅል ነህ ንከሳት ስልህ ደግሞ
እንደ "ሱዋሬዝ" በጥርስህ ዘንጥለህ እንዳታስለቅሳት) ቀስ አድርገህ ንክስ!
በትንፋሽህ አሙቃት...አገጭዋን ከንፈሯንና ግንባሯን ከዚያም አንገቷን ቀስ
አርገህ በፍቅር ሳማትና ከዛ...
"Surprise ላደርግሽ ነው" ብለህ አይኗን አስጨፍናት:: ልክ አይኗን
እንደጨፈነች ቅድም ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጥካቸውን ሞባይል; የጆሮጌጥ;
አምባር; ብራስሌትና የአንገት ሐብል ይዘህ በሩጫ ጥፋ! .
.
.
.
.
የፒያሳ ነጋዴዎች እየጠበቁህ ነው

source: facebook by
Jo Hannes BuNa Saf


Post Reply

Return to “Jokes and Funny stuff ...ቀልዶች እና አዝናኝ ርዕሶች”