ቀልዶች.....

sara
Starter
Starter
Posts: 16
Joined: 30 Oct 2009 19:07
Contact:

ቀልዶች.....

Unread post by sara » 16 Nov 2009 21:21

:lol: አለቃ እንዲሁ ሴት ጋር ያድሩና ጠዋት ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ይከለከላሉ እንዳይገቡ ያያቸው ሰው ስለነበር። እናማ በሴቶች በር በኩል ሄደው ዛሬ ሴቶች አይገቡም እዚህ ከገርገራው ውጪ ሆናችሁ ጸልዩ ብለው ሴቱን ሁሉ ከልክለው ካህናቱ ገርሟቸዋል አንድም ሴት ሳያዩ በመቅረታቸው። «ምን ሆነው ነው?» ሲሉ አንድ ያለቃን ስራ ያየ ካህን «አለቃ ከልክለው ነው ሴቶች እንዳይገቡ» ብሎ ያስረዳል።አለቃም ተጠርተው ሲጠየቁ «እኔ ለነካሁት ከተከለከልኩ እነሱ ይዘው እንዴት ይግቡ» ብዬ ነው አሉ :lol: :lol:ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው

አለቃ አንድ ቀን መንገድ መሽቶባቸው አንዲት ሴትዮ ቤት እንድታሳድራቸው ለምነው ቤት ለእንግዳ ብላ አስገባቻቸው። አለቃ ያው እንደሚተረከው ቅንዝራም ቢጤ ናቸው። እራት በልተው ከጨረሱ በኋላ በሉ እኔ መደብ ላይ እርሶ መሬት ላይ ተኙ ብላቸው ተኙ። ከዚያ ጨለማን ተገን በማድረግ ሴትየዋ መደብ ላይ ዘፍ ብላው መዳሰስ ይጀምራሉ። ሴትየዋም በድንጋጤ ነቅታ እንዴ ምን እየሰሩ ነው ስትላቸው ከአልጋ ላይ ወድቄ ነው አሏት። እንዴት መሬት ተኝተው ስትላቸው እኔንስ የገረመኝ እሱ አይደል አሏት ይባላል :lol: :lol:

ጠረር አርገሽ ቅጂው

አለቃ አንድ ቤት በእንግድነት ሄደው ሳለ ጠላ ይጋበዛሉ። ጋባዥ የነበረችው ሴትዮም ጠላውን ልትደግማቸው ጎንበስ ብላ ስትቅዳ ንፋስ ፈሷ ያመልጣታል። አለቃም ሰምተው እንዳልሰማ ይሆናሉ። የቀረበላቸውን ሲጨርሱ ሴትዮዋ እንደገና መጥታ «አለቃ ልድገሞት» ትላለች። አለቃም «ልድገም ብለሽ ነው? በይ እስቲ እንደቅድሙ ጠረር አርገሽ ቅጂው» ብለው መፍሳቷን እንዳወቁ በዘዴ ተናገሩ። :lol: :lol:


ገብርኤልና ሚካኤል ተታኮሱ
ወይዘሮ ማዘንጊያ ይፈሱና «ውይ ገብርኤልየ» ይላሉ። ይቆዩና እንደገና ይፈሳሉ «ውይ ሚካኤልየ» ይላሉ ከዛ ድንገት ዞር ሲሉ አለቃ ገብረሀናን በመስኮት ቆመው ያዩዋቸዋል። ድንግጥ ይሉና «እርሶ ደግሞ እዛ ቆመው ምን ያረጋሉ?» ብለው ይጠይቋቸዋል።አለቃ ገብረሀና ደግሞ «እን..ዴ.. ገብርኤልና ሚካኤል ሲታኮሱ እያየሁ ነዋ!» አሏቸው ይባላል። :lol: :lol:


ደርቆ ተንጣጣ

አንድ ሰሞን አለቃ በጣም ቆንጆ ልጅ ያገባሉ። ከዚያም ያው እንደ ባህል ወጉ ልጂቱ እሳቸው ጋ ልታድር ቤታቸው ትሄዳለች። እናም ቀኑ ተገባዶ ማታ ላይ አለቃ ቆጥ ላይ ወጥተው ሲጠብቋት እሷ ማታ ወደ ቤተሰቦቿ ከድታ ልትሮጥ ከቤት ስትወጣ ውጪው እንደአጋጣሚ ዝናባማ ስለነበር አድልጧት ትወድቅና ተመልሳ ቤት ትገባለች። ቤት ገብታም ምድጃ ዙሪያ ተቀምጣ ልብሷን ስታደርቅ ሳት ይላትና ጡጥ ታደርጋለች። ይህን የሰሙት አለቃ «አንቺ አትተኝም?» ይሏታል። እሷም «እስኪ ይቆዩ ልብሴ ምጥጥ ምጥጥ ይበልልኝ» ትላለች። እሳቸውም እሺ ብለም ዝም ሲሉ ልጂቱ አሁንም ደግማ ዛጥ ታደርጋለች።በሁኔታው የተቆጡት አለቃ በስጨት ብለው «አንቺ አትተኝም?» ሲሏት። እሷ «እስኪ ይቆዩ...ልብሴ ይድረቅ ትላለች።» ከዚያም አለቃ ቀጥለው «ኧረ ...ኤዲያ ...ልብስሽ ደርቆማ እየተንጣጣ» ብለው ባሽሙር ጠቅ አረጓት ይባላል። :lol: :lol:
ሁለቱ እብዶች

ሁለት እብዶች ከአማኑኤል ሆስፒታል ዘበኛውን አታልለው ለማምለጥ ይመካከራሉ። በምክራቸው መሰረት ወደመግቢያው ሲያመሩ ዘበኛው በአካባቢው የለም። በመጥፋት ፋንታ እቅዳቸው እንደተበላሸ በማሰብ ወደነበሩበት ተመለሱ

Post Reply

Return to “Jokes and Funny stuff ...ቀልዶች እና አዝናኝ ርዕሶች”